ማለዳ።

አዱኛማ መቅድም።
„ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታምኝነትህ ብዙ ነው።“
ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፳፫

ከሥርጉተ©ሥላሴ
27.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።



  • መነሻዬ ሊንክ።

/ሚኒስትር / አብይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ልጆች ድጋፍ በተደረገበት ወቅት ያደረጉት ንግግር

 መነሻውን ያወቀ መደረሻውን ያሳካል። መቅድሙን ከመዝለቂያው ልብ ላይ የተካነ ግቡን ያሳካል። ሩቅ በማስብ ውስጥ ማግስት አለ። በማግስት ውስጥ ቀጣይነት አለ። በቀጣይነት ውስጥ ትውልድ አለ። በትውልድ ውስጥ አገር አለ። በአገር ወስጥ መኖር አለ። በመኖር ውስጥ አኗኗሪ ነፍስ አለ።

የአኗኗሪ ነፍስ የቀደመ - የተሰላ -  የተደራጀ - የተቀናጀ  - ቅናዊ - ቸራዊ እቅዳዊ ትልም ነው የማግሥት መዳረሻ። ከዚህ የተነሳ ትልም የፈለገ የፈተና ዓይነት ይከመርበት ይወጣዋል። ስለምን? ነገን ማሰብ ነው እና የዛሬ አኗኗሪ የነገ ተወዲያም ንጥረ ነገር ዋስተና ልእለ ጉልላት - እርስትም።

በማያልቅ የሃሳብ ውጣ ውረድ እና ጉግስ ውስጥ የከተመ ብልህ ሁልጊዜም አያልቅበትም። ፏፏቴ! የማያልቅበት ደግሞ ነገን ለማደራጀት መሳሪያው በእጁ ነው ያለው። ለመሳሪያው ውል ደግሞ ያሰቡትን ለማሳካት ቆርጦ መነሳትን ይጠይቃል። ኢትዮጵያን ቁም ነገር ያደረገ መሪ በገቢረ ክህሎቱ ክህንቱ ያጸደዬ ነውና።

በመኖር አኗኗር እና በአኗኗር መኖር መካከል ውስጥነት ካለ፤ ውስጥን ከውስጥ በማገናኘት ሃዲድ ለመዘርጋት ተፈላጊው ንጥረ ነገር እኛዊነትን በልባዊት በማጋባት፤ ማዕዳዊ ቤተኝነትን መፍጠር ነው። እኛዊነት በልባዊነት ሲጋባ ደግሞ የማግስት ተስፋ እድዮዊ ይሆናል። አድዮ እሸት ናት። አድዮ ማግሥት ናት። አድዮ የምሥራች ዜና ነጋሪ ናት። 

አድዮ አታዳላም። አድዮ አላዛሯ ኢትዮጵያ ላይ በእኩልነት ትገኛለች። ኤርትራም ታዳሚ ናት። ዛሬ ዛሬ መልካሙ ዘመን ሆነና ከኩርፌያችን እና ከጥርጣሪያችን ወጥተን ኤርትራንም በበጎ ማሰብ ጀማምርን። ለብልጠት ሳይሆን ለስብ የሚተጋ እውነተኛ ሙሴ አላዛሯ ኢትዮጵያ ስላገኘችልን። ተመስገን!

አላዛሯ ኢትዮጵያ ተስፋ እያጫት ነው። ተስፋው እጮኛዋ ሲሆን ደግሞ አማጪው ሙሴዋ ነው። ሙሴው የማግስትን ሙሽሮች የእኔ ማለትን አህዱ ሲል የብርሃን ጮራ ፈነጠቀ። አዎን መስከረም እዬሆነ ነው። እዮሃ አበባዬ …  የልጆች የተስፋ መቅጃ ነው ... 

የትውልዱን ነገር መሰረት ለማስያዝ ከተጀመሩት በጎ ጅምሮች ትናንት ያዬነው መልካም ነገር ደስታን በልክ መያዝ ቢገባም ባለቤት የሌለው ዘርፍ የጠ/ ሚር ቢሮ ማዕደኛ መሆኑን ቸር ተመኝ ቸር ታገኝ መንገድ መጀመሩን አህዱ ብሏል። "መባቻ" መቅድሙ ጹሁፌ ነበር እናም እዬተሳካልኝ ነው። ተመስገን!

የዚህ የመልካም ነገር ጅማሮ ልዑል እግዚአብሄርም „ህፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው“ ያለውን ቃለ ህይወት ያመሳጠረ ነው። ለዛውም ከዝቅተኛው ህብረተሰብ ላይ መነሳት የልቤ መሠረት ያሰኛል። እኔ እንደ ገና የተወለድኩ ያህል ይሰማኛል። ዕድሜዬ ወደ ወጣትነት የሚወሰድ ቢሆን የወረፋው ቀዳሚተሰላፊ እኔ በሆንኩኝ በነበር። ለነገሩ ዕድሜዬ ከመጋቢት 24 ቀን ጀምሮ ቢቆጠርልኝም ምርጫዬ ነው … እያንዳንዱ ማዕልት ያሳሳል፤ ይናፍቃልና … 

እንግዲህ የቤተ መንግሥት ጎረቤታማ ወጣቶችም አበባዬሆሽ ማለት ይፈቀድላቸው ይመስላል፤ መስቀልም ኮበሌዎች እንጎረጎባሹን ከልካይ የለባቸውም። ቤተ - መንግሥስቱ የህዝብ ልጆች መሆኑ አዲሰኛው የሰብዕዊነት አብዮት ብሥራቱ ሁለ አቀፍ፤ ሁለመና፤ ሁለገብም ስለመሆኑ ያመላክታል።

ምክትል ከንቲባው አቶ ታከለ ኩማ እና ቲማቸው መልካምነትን ወስጣችን ብለውታል። አቶ ታከለ ኩማ የታቦቴ  ቅኔው ልዑል የብላቴ ሉሬት ጸጋዬ ቤተሰብ ጠረንኛ ናቸው። በሥጋ ይወልዱታል። ስለዚህም የመዲናችን መናህሪያ ጠረንኛው ኢትዮ አፍሪካኒዝም እንደሚሆን ልብ ልክ ነው። መቼም የዛ የታላቅ ሰው ደም ቅጂ ሆኖ ወዲህና ወዲያ ተዛንፍዮሽ የለበትም። ለዚህ ነው እኔ የሎሬቱ ዘመን ስል የባጀሁት።

እኔ የብላቴው ጠረን ግጥሜ ነው። ሲከፋኝ እምጽናናበት፤ ብቸኝነቴን እማስታግስበት፤ ተስፋዬ ቁልቁል ሲወርድ አይዞሽ የሚለኝ ታላቅ የመኖሬ ትርጉም ነው የሎሬቱ መንፈስ። ዛሬ አዲስ አበባም በዛ ታላቅ ኢትዮ አፍሪካዊ የመሆን ግሱ የኔታ ጸጋዬ ገ/መድህን አውደ ምህረት መዲናችን ስትቃኝ ደስታዬ ወደር የለውም።

እንሆ ዛሬ የዛ ሊቀ ሊቃውንት፤ የዚያ የኢትዮ አፍሪካዊ ነብይ ባለደራ ትንፋሽ ያገኘውን ዕድል ሳያሾልክ ትናንት በእሙሃይ አዱኛ ቤት እና በነገ የሎሬት ተስፋዎች ላይ ቀልቡን 
አሳርፏል።  ተመስገን!

                                            የሎሬቱ ተስፋዎች!

የመዲናዋ የአዲስዬ ቲሙ ሦስቱ ሥላሴ ነው አሉ። ሦስቱ እንደ አንድም፤ እንደ ሦስትም ሆነው የጀመሩትን መልካም ነገር ዋልታው ደግሞ አባ ቅንዬ ጠ/ ሚር አሜኑ ናቸው። አባ ቅንዬ አባ ጠ/ ሚስትሩ ደግም ብላቴ ውስጣቸው ነው። ይህ የግጥምጥሞሽ አይደለም። 

እኔ ሂደቶችን ሁሉ በሥጋዊ ነገር ከመነሻውም ተርጉሜው አላውቅም። ከገሃዱ ወይንም ቁሳዊ ዓለም በዘለለ እጅግ በተባ መንፈሳዊ ረድኤት ልዑል እንግዚአብሄር ኢትዮጵያን የጎበኘበት ዘመን አድርጌ ነው የማዬው፤ ለዚህም ነው እምሳሳለት። እምጨነቀልትም። መጨረሻው አጅግ አደርጎ ይናፍቀኛል። 

አዲስ ዓመት ከወትረዎ በተለዬ በተስፋ እና በምህረት፤ በይቅርታ እና በፍቅራዊነት ማሰብ፤ መጠበቅ በራሱ አዲስ መኖር ነው። ታድለን!

ከዚህ በተረፈ በውጭ አገር በቻይና ለከፍተኛ ትምህርት ለመሄድ የታደሉ ኢትዮጵውያንንም ሀገራዊ ሃላፊነት እና ዘመናዊነት በቅጡ ባገናዘበ መልኩ ብልሃታቸውን፤ ፓተንታቸውን ቀስሞ ነገን በማሰብ፤ አገርን ቁም ነገር የማድረግ ዓለማ እንዲሰንቁ ተጓዦችን የፍቅር አደራ ጠ/ ሚር አበይ አህመድ የህሊና ኪዳን አስገብተዋቸዋል። ቡራኬ ተስጥቷቸዋል በጠ/ ሚር አብይ አህመድ። 

ስፍለገው የሰነብትኩት አብይ ተገኝቶልኛል። ተመስገን!

ለጣምራው ሁለገብ ተልዕኮ ባለጠማራው ህሊና ማግስትን ለማበጀት እዬታተሩ ነው። ሰው መስራት ህሊናን በማበጀት እረገድ በ ኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ የተኘው የመንፈስ ለውጥ  ለእኔ የታምር ያህል ነው። ስለዚህም ቢያንስ አባ ቅንዬን በጸሎት እንገዛቸው።
  • ·       መዳረሻዬ ሊንክ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ነፃ የትምህርት እድል አግኝተው ወደ ቻይና የሚሄዱ ኢትዮጵያውያን አሸኛኘት ስነ ስርዓት ላይ ያስተላለፉት መልዕክት

  • ·       ስከኛ!

ለከፍተኛ ተማሪዎች ወደ ቻይና ተጓዦችም ሆነ ለመጀመሪያ ደረጃ የአገር ውስጥ  ተማሪዎችም መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆን  እመኛለሁኝ። በተጨማሪም መልካም የስኬት፤ የጥረት እና የውጤት ዘመን እንዲሆንም እጸልያለሁኝ!

በመጨረሻ ግን ፋና የሚቀርጻቸው የድምጽ ሆነ የምስል ጥራታቸው የልብ አድርስ ነው። አመሰግናቸዋለሁኝ።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
አራት ዓይናማው መንገዳችን የአብይን ሌጋሲ ማስቀጠል ነው!
የኔዎቹ ቅኖቹ አዱኛዎቼ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።