ልጥፎች

ከማርች 28, 2021 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጭምቱ ለሁሉም አልጋው አማራ።

ምስል
  ማዕዶተ ሰባዕዊነት ለዛውም በሰንበት። ዕለተ ሰንበት ማዕዶተ ርትህ ሰባዕዊነት። በከበቡሽ የቁራሽ እንጀራ ብራና በቢሆነኝ የተብራራ ብራ በሰብለ ህይወት አዝመራ ለራህብ የሚራራ።   „ የሰው ልብ መንገድን ያዘጋጃል እግዚአብሔር ግን አካሄዱን ያቃናለታል። " ( ምሳሌ 16 ቁጥር 9) • ጭምቱ ለሁሉም አልጋው አማራ። ዘመን - ተዘመን፤ ወቅት - ተወቅት፤ ሂደት - ከሂደት፤ ታሪክ - ከታሪክ፤ ትውፊት - ተትውፊት፤ ዓመት - ከዓመት፤ ወራት - ተወራት፤ ሳምንት - ተሰማንት፤ ቀን - ተቀን አንድም ዕለት ወቀሳ አብርቶለት የማያውቀው የአማራ ህዝብ መከራውን ተሸክሞ ኢትዮጵያንም ከእነመከራዋ ተሸከሞ አለ እንዳለ። ትናንትም ዛሬም። በአማራ ሥም የተደራጁት ሁሉ የሚታገሉት ለኢትዮጵያኒዝም ነው።   በኦሮሞ፤ በአፋር፤ በትግሬ ወዘተ … ሥም የተደራጁት ደግሞ ለራሳቸው ማህበረሰብ ነው። ጠቀመም ጎዳም። አማራ ሲደራጅ ኡኡ ! ተባለ። የተደራጀበትን ዓላም ግብ አይደለም መከራውን ማስታገስ ሳይችል የኢትዮጵያን መከራ ለመሸከመ ቆረጥ ቆረበበትም። ጎዳናውን በዛ ጠረገ። የኦሮሙማ አስተዳደር ተቀምጦ „ ኢትዮጵያን አትንኳት ? “ ከአማራ ድርጅት የሚወጣ የወል ድምጽ ነው። ይህን ሚስጢር የሚያነብ፤ የሚተረጉም፤ የሚያመሳጥር አቅም ያለው ሙሴ እስኪመጣ ድረስ ድሉን አማራ አይገኝም። አማራን በልኩ የተረዳ ተቋም የለም።   አማራ አማራ ሆኖ መታገሉን እራሱ ፈጽሞ አላወቀበትም። አልገባውም የተደራጀበት ዓላማ እና ...