ነፃነት ታስሮ ነፃነት የለም! „ከጉድጓድህ ውኃ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ።“ ( ምሳሌ ምዕራፍ 5 15) ከሥርጉተ© ሥላሴ 14.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ) · የመ ንፈስ እሰረኝነት አዲስ ዕወጃ በጄኒራል ዘይዱ ጀማል። https://www.youtube.com/watch?v=Mm9DjkQADp0 Ethiopia: የነገዉን የፕሬዘዳንት ኢሳየስ ቅበላ አስመልክቶ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳወቀ ትናንት ማምሻ ላይ አንድ መግለጫ አዳምጥኩኝ። በደስታ ተቀበሉ ግን የወያኔ ሃርነትን ሰይጣናዊ መለያ ዓርማ ይዛችሁ በውስጥ ቁስለት፤ እርር ድምብን፤ ትክን፤ ኩፍትርትር ብላችሁ ውስጠችሁ ክፍት ብሎት መሆን አለበት የሚል ነበር። ለዚህ ቀን የተበቃው እኮ በቄሮ እና በአማራ ተጋድሎ እንጂ በወያኔ ሃርነት ትግራይ መልካም ፈቃድ እና ችሮታ አይደለም። ስለዚህ ለዚህ ቀን ያበቃው የነፃነት ዓውድ በፍጹም ሁኔታ ምንም ዓይነት ቅደመ ሁኔታ፤ ምንም ዓይነት እስር፤ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ ሊደረግበት አይገባም ነበር። የአማራ ተጋድሎ ደግሞ ልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማው ነው … በቃ! ሰዉ ደስ የሚለውን፤ ዓርማዬ ነው አውደዋለሁ የሚለውን፤ ልብሱን ሰንደቁን ይዞ የመውጣት ሰንደቁን ሊነፈግ አይገባም የሞተበት፤ የታሠረበት፤ የተገደለበት፤ ጥፍሩ የወለቀበት፤ የተንኮላሸበት ነው፤ ግብዣ ጠርትህ ለብስ ወስነህ ወይንም ግማሽ ጭንቀላትህን ቤት ጥለህ ና አይነት ነው ጉዳዩ፤ ይህ ደግሞ የማይሆን ነው። ኤርትራ ላይ ምንም እስር ስላልነ...