የመንፈስ እሰረኝነት አዲስ ዕወጃ በጄኒራል ዘይዱ ጀማል።

ነፃነት ታስሮ ነፃነት የለም!
„ከጉድጓድህ ውኃ ከምንጭህም የሚፈልቀውን ውኃ ጠጣ።“
( ምሳሌ ምዕራፍ 5 15)
ከሥርጉተ© ሥላሴ 14.07.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)


·        
      የመንፈስ እሰረኝነት አዲስ ዕወጃ በጄኒራል ዘይዱ ጀማል።

Ethiopia: የነገዉን የፕሬዘዳንት ኢሳየስ ቅበላ አስመልክቶ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በቂ ዝግጅት ማድረጉን አሳወቀ


ትናንት ማምሻ ላይ አንድ መግለጫ አዳምጥኩኝ። በደስታ ተቀበሉ ግን የወያኔ ሃርነትን ሰይጣናዊ መለያ ዓርማ ይዛችሁ በውስጥ ቁስለት፤ እርር ድምብን፤ ትክን፤ ኩፍትርትር ብላችሁ ውስጠችሁ ክፍት ብሎት መሆን አለበት የሚል ነበር። 

ለዚህ ቀን የተበቃው እኮ በቄሮ እና በአማራ ተጋድሎ እንጂ በወያኔ ሃርነት ትግራይ መልካም ፈቃድ እና ችሮታ አይደለም። ስለዚህ ለዚህ ቀን ያበቃው የነፃነት ዓውድ በፍጹም ሁኔታ ምንም ዓይነት ቅደመ ሁኔታ፤ ምንም ዓይነት እስር፤ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ ሊደረግበት አይገባም ነበር። የአማራ ተጋድሎ ደግሞ ልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ አርማው ነው … በቃ!  

ሰዉ ደስ የሚለውን፤ ዓርማዬ ነው አውደዋለሁ የሚለውን፤ ልብሱን ሰንደቁን ይዞ የመውጣት ሰንደቁን ሊነፈግ አይገባም የሞተበት፤ የታሠረበት፤ የተገደለበት፤ ጥፍሩ የወለቀበት፤ የተንኮላሸበት ነው፤ ግብዣ ጠርትህ ለብስ ወስነህ ወይንም ግማሽ ጭንቀላትህን ቤት ጥለህ ና አይነት ነው ጉዳዩ፤ ይህ ደግሞ የማይሆን ነው።

ኤርትራ ላይ ምንም እስር ስላልነበራቸው ያን ያህል ወስጣችን እስኪፈንድቅ ድረስ አቋማችን ሙሉ ለሙሉ እስኪቀይር ድረስ ፍቅራቸውን የለገሱን እንዳሻቸው ሆነው እንዲወጡ ስለተፈቀደላቸው ነበር። ነፃነት ይሄው ነው።

አሁን ነፃነቱን ያስገኘው መንፈስ ታስሮ ደስታው ለኢህአዴግ ካድሬዎች ተሸልሟል። እንቆቅልሽ። ግፍ አይሆንም ይሄ። ቦሌ ላይ የሚፈልጉትን አቀባባል ማድረግ ይችላሉ፤ የመንገድ ላይ አቀባበል ግን ህዝቡ ነፃነቱን ተቀምቶ መሆን አይገባውም ነበር። ለኢህአዴግ ካድሬዎች ደስታ ነው ወይ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ግንኙነት። ደስታው እኮ ለሁለቱ አገሮች ህዝቦች ነው።

ያ ከሆነ ደግሞ ህዝብ ደስታውን ለመግለጽ የሚመረጣው ምርጫ የራሱ እንጂ የመንግሥት ሊሆን ፈጽሞ አይገባም ነበር። ይሄ እኮ ነው ህዝብ እና መንግሥትን የሚለያዬው። የዶር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን በመጡ ጊዜ የማይቀበጣር ጉድ አልነበረም ህዳሴ ልማት ከፍታ ወዘተ ወዘተ። 

ደግነቱ የዛ ሰሞን ፕሮፖጋንዳ አቧራ ለብሶ ቀርቶሏል። ዛሬ ደግሞ ያን የሰይጣን መለያ ይዛችሁ ካልመወጣችሁ አትምጡብን ነበር ጉዳዩ፤ እናም እኔ የማየት ሁሉ ፍላጎቱ ስልለነበረኝ የቦሌው አዬሁኝ በሰላም ገብተዋል። ያዬሁትም ሰላሙ ስለሚጨንቀኝ ብቻ ነው። እርግጥ ነው አቀባባሉ ትንሽ ፈጣን ያለ ይመስለኛል። የደህነነቱ ገዳይ መሰለኝ። አሁን እኮ የአብይ መንፈስ ጦር ሜዳ ላይ ነው ያለው። 

ይልቅ ጥበቃው የተጠናከረ ነበር። ይህ የተገባ ነው። ከእንግዲህ ጦርነቱ የሁለት መንግሥታት ነው፤ የትግራይ ሥርዕዎ ምንግሥት እና የአዲስ አባባው በዛ ላይ ሦስተኛ መንግሥት ነኝ ብለው አቶ ዳውድ ኢብሳም አውጀዋል፤ አራተኛም ባዶ እጁን ታቅፎ የቀረው የኔቱ ጦርነት አለ ስለዚህ በዚህ መልክ የተጠናከረ ጥበቃ መኖሩ እጅግ አስፈላጊና በ100 ቀናት በክፈት የቆዬ ጉዳይ ዛሬ ቁርጥ ያለ ዕልባት እንደተሰጠው ታውቋል። መሪዎችን እንዲህ የሚያደርገው እራሱ ሁኔታው ነው። …

ሌላው „ላም እረኛ ቢቆጣ ምሳው እራቱ“ ይሆናል እንዲሉ ዶር ደብረጽዮን ገብረሚኬኤል ቦሌ አቀባባል ላይ አይቻቸዋለሁኝ። ኤርትራ መሬት ላይ በክብር እንዲገኙ ተፈልጎ ሳይገኙ ቀርተው ነበር። መቼም አንገት አይችለው የለም አንገታቸውን ችለው መቆማቸው እራሱ ይገርማል። 

በሳቸው ዘመን ከተራ ግድያ እስከ ህዝብ ጭፍጨፋ፤ ከግለሰብ መፈናቀል እስከ መሪ እና ሙሉ ካቢኔ የግድያ ሙከራ፤ እስከ ተናጠል መፈናቀል የምልዕት ህዝብ መፈናቀል ያልተሰማ ያልተደመጠ የጉድ ጅራት የለም … ብቻ መፈንቀለ መንግሥቱ ከሽፏል።

የሆነ ሆኖ እንግዳችን የእኛ ብቻ እንጂ የእናንተ አይደለም ተብሎ መገደቡ ግን አጀብ አሰኝቶኛል። ድባቡም የመንገድ ላዩ እጅግ ደባሪ እና ቀዝቃዛ ነው ለእኔ ስሜት። ይህን ያደረገው የማታው የፖሊስ ኮሚሸሩ አፋኝ መግለጫ ነበር። አዬሩን ሙሉ ለሙሉ እንደበርደው አድርጎታል ... 

ይህ ለምን ሆነ? የጠ/ ሚር ቢሮ መልስ ይስጥበት። ራሱን ጠ/ ሚር ቢሮ ይህን የህዝብን የነፃነት መንፈስ እዬተጫነ ከመጣ ቀጣይ እጣ ፈንታው ይወድቃል። በቃ። ድርድር የለም። እኔ እራሱ ለማዬት ድብር አድርጎኝ ዝግት አድርጌ ወደ ኮንፒተሬ ገባሁኝ። ምንም ሳይባል ህዝብ የፈለገውን ለብሶ፤ እንደ ፈለገው ሆኖ ቢወጣ ምን በነበረ … እንግዲህ አዋሳ ላይ ደግሞ መሰሉ ተግባር ይከውንበታል … የህዝብን ሳቅ፤ ደስታ፤ ፍቅር ለመቀማት ማን ብሏቸው የሰይጣን ኮከብ አምላኪዎችን …
የካድሬው ሰልፍማ ተኖረበት እኮ 27 ዓመት።

እኛ ምናችንም አይደለም። አይደለም እዛ እኔ የነፃነት፤ የለውጥ ሐዋርያ ነን በሚባለው የካድሬ ስብሰባ እዚህ ስልችት ብሎኝ ካቆምኩት ከሁለት ዓመት በላይ ሆነኝ። እንግዲያወስ ሰንደቅ ዓላማው አለ፤ ግን አዬሩ እእ …  ከዛም ካድሬ ከዚህም ካድሬ። ተበጠበጥን። ፈጣሪ ሆይ! ይህን የካድሬ ዘመን የማናይበትን ዘመን እባክህን አምጣልን።

ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂን ካድሬ ብቻ ተቀበሉ ነበር የትናንቱ ዕወጃ። ያው እናንተው ተቀበሉ እናንተው ደስ ይበላችሁ። እኔ ኤርትራ ላይ ይህን ባለኮከብ ሰንደቅ ይኑር አይኑር ሳለዬው፤ ትዝም ሳይለኝ የኤርትራውያን ፍቅር ብቻ አጥግቦ አሰከረኝ። ስለዚህ ከቁብ ሳልቆጠረው የሰይጣኑን ዓርማ የኤርትራውን ልባዊ ንጹህ መሰናዶ የደስታው ታዳሚ ሆንኩኝ። ከፍሰሃዬ ብዛት የተነሳም በርከት ያሉ ዘገባዎችን ማቅረቤ ብቻ ሳይሆን እፎይ አልኩኝ።

የአዲስ አባባው ደግሞ የኤርትራው ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳይስ አፈወርቂ ወደ ኢትዮጵያ መምጣት ለኢህዴግ ካድሬዎች ብቻ ነው ከተባለ ስለምን ሰው ይደክማል። አርፎ መደበኛ ሥራውን ይስራ ፍቅር ንግድ አይደለም። ወይንም ፍቅር ሸቀጥ አይደለም። ይህን መርዛቸውን በዬተገኘበት ሁኔታ በመርጨት ልብን ለማሸፈት የሚሹ የኢህአዴግ ካድሬዎችን ፈጣሪ አምላክ ብን ትን አድርጎ ያብንንልን አሜን …

ሌላው ቀርቶ ለእኔ ብሄራዊ መዝመሩ ሲዘመር ስሜት ሰጥቶኝ አያውቅም። የእኔ አድርጌ ከቁጥር አስገብቼውም አላውቅም፤ ለዛውም የሥነ - ግጥም መምህሬ የደረሰው ነው። እንዲያውም እኔ ከዛ እያለሁኝ ይሻላልል ተብሎ በፊደላት፤ በሥንኛት በቁጥር ተገድበው እኔ ሁሉ አንድ ድረስት ጽፌ ነበር ለውድድርም ቀርቦ ነበር፤ ረቂቁ ከእጄም ይገኛል። አልተሻሸለም በዛው ነበር የቀጠለው። 

ይሄ ወያኔያዊ መዝሙር ተብዬው ግን ግጥሜ አይደለም። አዲስ ብሄራዊ መዝሙር ዘላቂ ሊሆን፤ ሥርዓት በመጣ ቁጥር የማይቀያዬር ፍቅር፤ ምህረት፤ ሰናይ መንፈስ የሆነ አዲስ መዝሙር  የጠ/ ሚር ቢሮ ቢያስበው መልካም ነው።
  
በተረፈ የኤርትራ መንግሥት ለሰጠን ፍቅር እና ሞገስ ለላፈው ሳምንት ቅዱስ ሰንብት ዕለት ደስታ እና ሐሴት አመስግናለሁኝ። 

ለዛሬው ግን ህዝቤ ታስሮ የተከወነ ስለሆነ ብዙም አልደነቀኝም አልደመቀኝም። ስለምን ጥሪው እኛን ስለማይመከት፤ እኛን የሚወክሉ ምልክቶች ስሌለበት፤ የወያኔ ሃርነት የመንፈስ ሎሌዎች ብቻ ነው መንገድ ላይ በአቀባባሉ እንዲገኙ የተፈቀደላቸው። 

ስለዚህ ለእኛ ደስታው ፍቅሩ ባዕዳችን እንዲሆን ታውጆበታል ማለት ነው፤ ጉጉታችን የቀበረው ደግሞ የፖሊስ ኮሚሸነሩ ጄኒራል ዘይዱ ጀማል እውር መግለጫ ነበር … ነፃነታችን የቀበሩ አዲሱ የወያኔ ሃርነት አፈ ቀላጤ ናቸው …  ይሄው ነው።

„እንከባባር!“

የኔዎቹ ኑሩልኝ ማለፊያ ቀን። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።