ልጥፎች

ከዲሴምበር 24, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

"የደርሶ መልስ ፊልም" በሚመለከት የእኔ ዕይታ።

ምስል
„የደርሶ መልስ“ ልቅና! በእኔአቅም ልቅም ቅኝት። „ጥበብ   ቤትዋን ሠራች፣ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች   ”   ( ምሳሌ ፱ ቊጥር ፩ )  ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 23.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                                                           ቅኔያዊት! ·          እ ፍታ። እንዴት ናችሁ ውዶቼ ክብረቶቼ። „ደርሶ መልስ“ በሚል እርዕስ በሁለት ምዕራፍ ወደ 28 ክፍሎች በፋና ቴሌቪዥን የቀረበ ተከታታይ የቴሌቪዥን ፊልም ነበር። ፊልሙ ከተለመወደው ወጣ ያለ ጭብጥን በምናዊ ርቀት በቅጡ የቃኜ ሆነው አግኝቻለሁኝ እኔ በግሌ። ሙሉውን ወደ ሦስት ጊዜ በጥሞና አይቸዋለሁኝ። እርግጥ ነው ለመዝንኛ ብቻ ልታይ ከተባለ፤ ወይንም ወጣ ገባ እያሉ ለማዬት ከታሰበ፤ ስለ ነፃነት ህሊናዊነት ካልተሰነቀ ጭብጡ መከበድ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ ፊልሙን የማዬት ሃሞትም ፈሰስ ይልና መንፈስ ባክኖ ይቀራል። እኔ ግን ከዚህኛው ጎራ ስላልሆንኩኝ ለፈረንጆች የልደት ቀን ጸጥታ በርጋታ ስለሚሆን በዬዘመኑ ይህ ቀን ሲመጣ የመጻህፍት እርማት ሰሞናቴን አቅድ ዘንድሮ አስተላልፌ  የ2018 የመሸኛ ሰሞናትን ለ4ኛ ጊዜ እኔ በፈቀድኩት፤ በወደድኩት የሥያሜ ምርጫ „ራስመሳማን“ በተደሞ እዘልቃዋለሁኝ … ተቀጣጠርን። ቀጠሮም ሰዓትም ለዛውም በፍጽምና አክባሪ ስለሆንኩኝም ዝንፍ፤ ወትልፍ ሳልል እንገናኛለን፤ ደግመን እንተያዬአለን። የነገ ሰው ይበለን አማልካችን እኔና አቤቶ የቤት ውስጥ ዘንከትክት ብሎ ፊት ለፊት ጉብ ያለውን ደመ ግቡ ቴሌቪዥኔ ጋር። አይቀሬ ነው መደገሙ .. ለአርባዕቱነት … ·         ም