ልጥፎች

ከጁን 18, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

#እርፍ። እልልልልል……… የዓመቱ ብርቅ ዜና። ተመስገን። «አሜሪካ #በህወሓት #መሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ #የቪዛ #ማዕቀብ ጣለች»

ምስል
  • #እርፍ ። እልልልልል……… የዓመቱ ብርቅ ዜና። ተመስገን።   • «አሜሪካ #በህወሓት #መሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ #የቪዛ #ማዕቀብ ጣለች»   https://www.bbc.com/amharic/articles/cy4ek8z92z3o   "አቤቱ ንጹህ ልብን ፍጠርልኝ፤ የቀናውን መንፈስ በውስጤ አድስ።"   (መዝ ፶፩፤፲።)   ይህ #ሰማያዊ #ስጦታ ነው። የፈጣሪም ሥራ ገሃድ የሆነበት ዕንቁ ዜና። #የእናትነት ዕንባ #አፈራ ። በየቀኑ የህወሃት ዕውቅና ብሪፊንግ በነጩ ቤተ - መንግሥት ቀርቶ እዚህ ተደረሰ። ተመስገን ነው። ለዚህም ነው የዘመኑን የፖለቲካ ባህሬ ዕወቁት ስል የባጀሁት። ዓለም እንደ ትናንትናው #አትቀጥልም ። ዘመን በሂደት ውስጥ በዚህ መልክም ባህሬውን ይከሰታል። ለህወሃት ይህ ውሳኔ #አፍ ያለው መቃብር ነው። ተስፋቸውን ቅርጥምጥም አድርጎ መቅኖውን ፍስስ የሚያደርግ።    ለቀኑ ቀን ሲሰጠው #አናርኪዝም እንዲህ #ያሟሟል ። ከህግ በላይነት ትርፋ #የተመለመለ ግንድነት ነው። "ወጣቶች ተውን፤ እንኑሩበት፤ እናግባ እንውለድ። አወን #ፈሪ ትውልድ ነን። ተውን አሉ ዕንባ እየተናነቃቸው ተማጽነዋል። እናቶች ትቢያ ለብሰው አፈር ለአፈር ተንበርክከው ለምነዋል። #ሰሚ ጠፋ። ኮንፊደንስ #ጣሪያ ነካ። ተለጠጠ። ግን ሟሸሸ።   አሁን ኢትዮጵያም #ወህ ትላለች። ተመስገን። ሁልጊዜ ማመስ፤ ማወክ። እሽ አይዋ #ጥምዶስ ምን ታስብ ይሆን???? የህወሃት የዲፕሎማሲ አቅም እንዲህ ቅስሙ እንኩት ሲል??? በዝልቀት እሰቡት።   ቸር አስበን፤ ቸር እንሁን። አሜን። ቅን አስበን፤ ቀና እንሁን። አሜን። ኑሩልኝ ማህበረ - ቅንነት። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን።   ሥር...