ልጥፎች

ከጁላይ 3, 2026 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ከማጣጣል ሂደቶችን በስክነት መከታተል ይበጃል - የአባ #ጠቅልልን የነገረ አጤ ሂደት - በማስተዋል። • የአቅም #ግኝት #ፍለጋው የሚያስተምረው ድርጁ ተመክሮ ስላለው።

  ከማጣጣል ሂደቶችን በስክነት መከታተል ይበጃል - የአባ #ጠቅልልን የነገረ አጤ ሂደት - በማስተዋል። • የአቅም #ግኝት #ፍለጋው የሚያስተምረው ድርጁ ተመክሮ ስላለው።   "የእግዚአብሄር ተራራ የለመለመ ተራራ ነው። የጸኑ ተራራወች ለምን ይነሳሉ? የእግዚአብሄር ይህን ተራራ ያድርበት ዘንድ ወደደው፤ በዕውነት እግዚአብሄር ለዘላለም ያድርበታል።" (መዝሙረ ዳዊት ፷፯ ከ ቁ ፲፭ - ፲፮።)    #ምዕራፍ ፲፱።   ሰሞኑን ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ፤ ከተወዳጁ ተጓዥ ጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም ጋር ውይይት ነበራቸው። የውይይቱ ፍሬ ነገር ሳይሆን #ገፊ ምክንያቱ ምንድን ነው የሚለውን ሳስበው ሰነበትኩኝ።   የሆቴል ሥራ #ብራንዱ የጀግና አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ ሥላሴ ነው። የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በኽረ ፕሮጀክታቸው ሆቴል መሥራት ነው።    ሌላው የጠቅላዩ የጫካ ፕሮጀክት ትኩረታቸው ነው። ሰፊውን ጊዜ የሚሰጡት። የደን ልማት ፕሮጀክትም አላቸው። የአባይ ግድብ አሻራ #ሁለት ሰብዕና ጎልተው ይወጡበት ነበር። የቀድሞው ጠቅላይ ሚር አቶ መለስ ዜናዊ እና ኢንጂነር ስመኜው በቀለ። በፕሮጀክቱ ግንባታ ልክ ሰብዕናቸውም ተገንብቶበታል።   የፕሮጀክቱ በአዲስ መሃንዲስ ተጠናቋል። በአባይ ግድብ ዙሪያ አጀንዳ ከኖረ የቀደሙት ሥሞች በማህበራዊ ሚዲያ ጎልተው ይወጣሉ። ይህ ባይፈቀድለትም ግን እየሆነ ያለ ዕውነት ነው።   ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ላጠናቀቁት ፕሮጀክት ፊድባኩ የሚነግረን መነሻ መሰረት የጣሉትን አክብሮ ይነሳል። ይህ ማለት በአባይ ግድብ ዙሪያ የነበረውን ቀደምት ዕውነት የህዝብ ህሊና ሴብ እንዳደረገው አስተውላለሁኝ። በነገራችን ላይ ስለ ጎርጎራ ፕሮጀክት ደርግ የሰራበት መዝ...

#የእምዩ ሲዊዝ ብሄራዊ ቡድን የአልጀርያን ብሄራዊ ቡድን ሁለት #ለምንም ሸኙ። #ሲዊዝ 2: #አልጀሪያ 0

ምስል
  #የእምዩ ሲዊዝ ብሄራዊ ቡድን የአልጀርያን ብሄራዊ ቡድን ሁለት #ለምንም ሸኙ።   #ሲዊዝ 2: #አልጀሪያ 0   "አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።     የፊፋው ፕሬዚዳንት በተገኙበት በአውሮፓውያኑ ሰዓት አቆጣጠር ከንጋቱ 11.00 ሰዓት በካናዳዋ አንኮበር ከተማ የተካሄደው ጨዋታ በሲዊዝ #አሸናፊነት በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ ውድድሩ ተጠናቋል።   የአልጀሪያ ቡድን እንደ ጣሊያን ቡድን #ጉልበት ቀመስ ነበር ማለት ልቻል። ሲዊዛውያኑ ደግሞ እንደሚታወቀው #ጨመት ያሉ ናቸው። ግፊያውን ችለው ጨዋታውን #በዲስፕሊን ከውነዋል። ልክ #በ10 ደቂቃው የገባችው ጎል ተጨማሪ ጎል አስከትላ ሲዊዝን ለቀጣዩ የዙር ጨዋታ #አብቅተዋል ። በዛሬው ጨዋታ የግል ጥረት እና የወል ጥረት የተዋህዱበት ነበር። አዲስ ተጫዋች ቁጥር 7 በጣም ቅንነት ያለው ነው። ዕድሎችን በማመቻቸት ረገድ ቅንነቱን አይቻለሁ። ፈጣንም ነው።   የሲዊዝ ቡድን ያሳየው #ጥንካሬ ገርሞኛል። በጣም ለውጥ አላቸው። ስጋቴ የነበረው ጎል ጠባቂው ከቦታው በጣም #ይርቅ ስለነበር ነበር። እንደ ፈረንሳይ፤ እስፔን ያሉ ቡድኖች እንዲህ ዓይነቱን ዕድል በጣም ይጠቀሙበታል። ስለዚህም የሲዊዝ ብሄራዊ የእግርኳስ ቲም በር ጠባቂ ብዙም ከጎሉ አካባቢ ባይርቅ ለቀጣዩ ጨዋታ ጥሩ ይመስለኛል። የአልጀሪያ ብሄራዊ የእግር ኳስ ቲም ጥሩ ተጫውተዋል። ብዙ ሞክረዋል።    ሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie. 03/07/026.   #ኳሲዝም ይለምልም። አሜን!