ልጥፎች

ከዲሴምበር 22, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የልጆች የውስጥ ቀለበትነት…እንደአብዩ ተደሞ!

ምስል
የአብዩ አፍቅሮተ - ልጆች ተደሞ። „የብልህ ሰው ጥበብ መንገዱን ያስተውል ዘንድ ነው“  ምሳሌ ፲፫ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  22.12.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ·        የ ፍቅራዊነት መንገድ በመሪነት ሲቆምስ። በቅድሚያ በዶር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ሉዑክ ተልኮውን አጣናቆ ኢትዮጵያ በሰላም መግባቱን አዳምጥኵኝ። ትልቅ ነገር ነው። በሰላም መግባት ትልቅ ዋጋ አለው - በእኔ ዘንድ። የሰው መኖር ነው አስፈላጊው ጉዳይ ሌላው ይደረስበታል። ተመስገን! እንዴት ናችሁ ቅኖቹ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? እስቲ ዛሬን በአዲስ አጀንዳ አብረን መጭ እንበል በሰላው መንገድ ... እንዲህ ... ዘንከትከት እንበልበት ...  ወላጆች ወይንም ኣሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚያከብርላቸውን ይወዳሉ። ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚወድላቸውን ይወዳሉ፤ ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚቀርብላቸውን ይወዳሉ። ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚፈቅርላቸውን ያፈቅራሉ። በዘመናት ሂደት አንድ ልዩ ክስተት ኢትዮጵያ ተከስቷል። ኢትዮጵያ ልጆችን የሚወድ፤ ልጆችን የሚያከብር፤ ልጆችን የሚያቀርብ፤ ልጆችን የሚያፈቅር መሪ  አላዛሯ ኢትዮጵያ አግኝታለች። ተመስገን! የኦሮሞ ጉዲፌቻ ባህል ትውፊት ነው ማለት የሚያስችል የኦሮሞ የፖለቲካ ሊቀ ሂቃን ቢኖሩ ዶር አብይ አህመድ ናቸው። በዚህ ታላቅ በሆነው የቀደምት የዕውነት ባህል ውስጥ  በአካልም፤ በመንፈስም ተገኝተዋል ጠ/ሚር አብይ አህመድ።  ዶር ለማ መገርሳም በልጆች ጉዳይ ላይ ባህርዳር ላይ ባደረጉት ...