ልጥፎች

ከኦገስት 15, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የእቅፋት እንቅፋት፤

ምስል
በነገ እና በእኛ፤ በዛሬ እና  በእኛ መሃከል ምን ይደረግ? ደግሞስ ከቀናቶቹ ጋር ምን እና ምን ነን? „አቤቱ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ  እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።“ መዝመረ ዳዊት ምዕራፍ  ፶ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ  © ሥላሴ  15.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·       እ ፍታ። መንግሥት ህዝብን ቢጨፈጭፍ ይውርዳል። ህዝብ ህዝብን ቢጨፈጭፍ ግን እንዴት ይኮናል። አሁን ያለው እንዲህ ነው። አንዱ ህዝብ አቅም ካለው ሌላውን መጨፍጨፍ፤ ማፈናቀል። አፈናቃዩ ደጋፊው ክፉ ህሊና ነው።  በልጅነቴ ዝምተኛው አባቴ አበይ ነፍሱን ይማርልኝ እና ዝምታውን ጥሶ የሚያልፍ እንጉርጉሮ ነበረው „እናት አባት ሲሞት በአገር ይለቀሳል፤ እህት ወንድም ሲሞት በአገር ይለቀሳል፤ አክስት አጎት ሲሞት በአገር ይለቀሳል አገር የሞተ እንደሆ ወዴት ይደረሳል“ አሁን ያለው ጣምራ ዘመቻ የታቀደው የሽግግር መንግሥትን ወይንም የተጽዕኖ ፈጣሪዎች መንግሥት ስኬታማ የሚያደርግ እድምታ ነው ያለው። ተፎካካሪዎችም መሬት ላይ ሥራ ለመጀመር ያልፍለጉበትም ምክንያት ያ ነው። የሚጠብቁት ህልም ስላላቸው። በመሃል ግን ስለ እነሱም ህይወት ምን ያህል እርግጠኛ እንደሆኑ አይታወቅም?  ·       መ ህበረ ቤት።  አገር ማለት በሥርጉትሻ ዕይታ ዓለም አቀፍ  እውቅና ባለው መሬት   እና ካለካሰማ በሚኖር ሰማይ ሥር የሰዎች ማህበረ - ቤት ማለት ነው። ማህረ - ቤቱ ውስጥ የሚኖሩ አባልተኞች ከተጨራረሱ አገር የሚባለው ነገር አ...