ልጥፎች

ተጠዬቂ እስኪ አንቺ መከረኛ!

ምስል
መርዝ እዬተዘራ መርዝን ማምከን አይቻልም። „ነገር ግን ወረተኛ ለጥቂት ቀን የሚሆን ወዳጅ አለና በመከራህም  ጊዜ ካንተ ጋር መከራህን ከአንተ ጋር አይታገሥም እና  ፈጽመህ አትመነው“ ምዕራፍ ፮ ቁጥር  ፲ ከሥርጉተ© ሥላሴ 15.08.2018  ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ሰው መሆን ሰው ሆኖ መፈጠር ብቻ አይደለም። ስለ ሰው መፈጠርም ዕውቀት ሊኖር ግድ ይላል። ሰው መሆን ቢያንስ ከእንሰሳ መለዬት ማለት ነው በቀላል ትርጉሙ። ሰውነት ለኢትዮጵውያን ከሁሉም በላይ የላቀ ሃይማኖታዊም ዶግማም ነበር። እግዚአብሄር ሰውን ቤተ መቅደሱ አድርጎ ፈጠረ ከሚል ሃይማኖታዊ ዶግማም ጋር የሚያያዝ „ ሰውን እንደ መልካችን በአምሳላችን አንፍጠር“ አሁን ግን እኔ ሰው አይደለሁም እያልን ነው። ሰው መሆን ስለሰው መጨነቅ መሆን ቀርቶ ስለሰው እንዴት እንደሚገደል፤ እንዴት እንደሚወገድ፤ እንዴት እንደሚገለል፤ እንዴት እንደሚታረድ፤ እንዴት አካሉ እንደሚጎድል፤ እንዴት ሥነ - ልቦናው እንደሚሸነሸን፤ እንዴት የውስጥ ሰላሙ እንደሚታወክ መራቀቅ ሆኗል ጀግንነቱ። ጀግንነት ሰብዕናን ሰው መሆንን ጥላህ ከወገብ በላይ ሰው ከወገብ በታች ጭካኔ፤ ወይንም ከወገብ በላይ እንሰሳ ከወገብ በታች ሰው ሆነህ በጥምር መንፈስ በደመ ነፍስ መነዳት ሆኗል። ሰው በራሱ ኢጎ ሠረገላ እዬገላበ ብቻ በቻቻታ እና በሁካት፤ በኳኳቴ እና በዲልቃ መንገድ ሆኗል የሰውነት ደረጃው። በአደባባይ ሰው ሰው መሆን አቅቶት፤ ስለሰው ሰብዕና ማሰብ ተስኖት ጭካኔን ት/ ቤት ከፍታችሁ ልጆቻችሁን አስተምሩ፤ አረመኔነት የልጆቻችሁ መለያ ምልክት የሰብዕናውም መፈጠሪያ አስኳል ይሁን እዬተባለ ነው፤ ለሽብርተኝነት ካሪክለም ይዘጋጅ እዬተባለ ነው፤ ማፍርስ፤ ማቃጠል እንደ ክብር እንደ ሞራል ልእ

የጉድ ዘመን - የመርዝ ናፍቆት።

ምስል
እርጋሞት አለመባልህ ስለምን? „እዬሱስ ግን ህፃናትን ወደ እርሱ ጠርቶ፣ --- ህፃናት ወደ እኔ ይመጡ ዘንድ አትከልክሏቸው፤ የእግዚአብሄር መንግሥት እንደ እነዚህ ላሉት ናትና። እውነት እላችኋለሁ፤ የእግዚአብሄርን መንግሥት እንደ ሕፃን የማይቀባላት ሁሉ ከቶ አይገባባትም አለ።“   ሉቃስ ምዕራፍ  ፲፰ ከቁጥር ፲፮ እስከ ፲፯ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 15.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። ይድረስ ለአብን ባህርዳር። ·       መነ ሻ። https://youtuby.xyz/watch?v=FhDm_XoagSw ሄኖክ የሺጥላ ለጀዋር ወቅታዊ ንግግሮች የሰጠው መልስ አልፎ አልፎ ሰዎች ምን ያስባሉ ስል አንዳንድ ነገሮችን እከታተላለሁኝ። ዛሬ ያው አቶ ይቱብ አንድ ክሊፕ አመጣልኝ እና አዳምጠኩት። ስንት ግራሞት እንዳለ፤ ስንት ትከዜ እንዳለ፤ ስንት የውስጥ ሃዘን እንዳለ፤ ስንት ሰቀቀን እንዳለ ቤቱ ይቁጠረው። ደስታችን ከቅጽበት ያለፈበትን ጊዜ አላስታውሰውም። የሻሸመኔው ሰቀቀን እህል ውሃ ጋር አጣልቶን አይናችን እንዳፈጠጠ እያሰደረን፤ ደግሞ ቀጣዩ የት ቦታ ቃጣሎ፤ የት ቦታ መፈናቀል፤ የት ቦታ የሰው እርድ እናዳምጥ ይሆን እያልን ሌቱም ቀኑም ተደባልቆብን ጭንቅ የሚለን ስደተኞች አለን። የድምጽ አልባዎች እናቶች አጀንዳኛ። ሁለት ነገር ብቻ ላንሳ ወጣት አቶ ሄኖክ የሽጥላ ካነሳው። ግን የጤና ነው ለማለት በፍጹም አልደፍርም። አንደኛው የጎንደር ህብረትን በሚመለከት ነው እኔም የምስማማበት ነው። የማንነት ቀውስ እንደ ሳጅን በረከት ያለባቸው አማራን ደግሞ ሌላ 43 ዓመት ለመቀብር የተነሳ መንፈስ ነው። አሁን ወጣቱ ትውልድ በጅ የሚልም አይደለም ጥሏቸውም ሄዷልም። አንሱ እዛው የዛሬ 43 ዓመት ላይ እንደ ኩሬ ውሃ

በለው! አቶ ንጉሡ ጥላሁን ደግሞ ምን እያሉን ነው?

ምስል
የመፍንቅል መንፈስ ማህበርተኞች የመንትዮሹ መልዕከታት ውጥረት። „እኔም ተመለስሁ፣ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አዬሁ፤ እንሆም የተገፉት ሰዎች እንባ ነበር፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፏአቸው እጅ ሃይል ነበር፤ እንርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።" መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ  ፩ ቁጥር ፬ ከሥርጉተ ©ሥላሴ 13.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። ·          ቁጥር አንድ https://www.zehabesha.com/amharic/archives/93457 ምርቱን ከግርዱ እንለይ ! ኦቦ አዲሱ ረጋሳ August 9, 2018 | „ነፃነት፣ወንድማማችነትና እኩልነት ካለፈዉ ታሪክም ሆነ ከባንዲራ በላይ ነዉ !“ ለቁጥር አንድ መልስ በዚህ ሰጥቻለሁኝ። እርግጥ ነው እንደ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ባንዴራ ጨርቅ ነው ዓይነት አገላለጹን በሚመለከት አልነካካሁትም።  ሌላውን ጭብጥ ግን ትንሽ ሄጀባታለሁኝ። ለማያያዝ ነው ሊንኩን የለጥፈኩት የሁለቱ መንትዮሽ ፍንገጣ እና ጥሪያቸው መከተታል እኔ ቀደም ብዬ ስገልጻቸው ከቆዬሁት ይሁን አቶ ጃዋር መሃመድ ወደፊት እንዲመጡ የነበረውን ምኞቱ ጋር ሃዲዱን እንድታገነዝቡት ነው። በዚህ ሊንክ ለሁለቱ መንፈሶቹ ያለውን ዕይታ የገለጸበት ነው አቤቱ አቶ ጃዋር መሃመድ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/88248 „ ሕወሓት   ለማ   መገርሳን   ለጠቅላይ   ሚኒስተርነት   ለምን   አልፈለገችውም ?  –  ጀዋር   መሐመድ   ያብራራል  |  ከሳዲቅ   አህመድ   ጋር   ተወያይቷል “ ·       ቁጥር ሁለት። ምነው የጀመራችሁት የጃዋርውያን ንግሥና እና የአብይ ሌጋሲ የመንፍንቅለ