በለው! አቶ ንጉሡ ጥላሁን ደግሞ ምን እያሉን ነው?
የመፍንቅል መንፈስ ማህበርተኞች የመንትዮሹ መልዕከታት ውጥረት።
„እኔም ተመለስሁ፣ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ
ሁሉ አዬሁ፤ እንሆም የተገፉት ሰዎች እንባ ነበር፤ የሚያጽናናቸውም አልነበረም፤ በሚገፏአቸው
እጅ ሃይል ነበር፤ እንርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።"
መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፬
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 13.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
ምርቱን ከግርዱ እንለይ! ኦቦ አዲሱ ረጋሳ
August
9, 2018 |
„ነፃነት፣ወንድማማችነትና እኩልነት ካለፈዉ ታሪክም ሆነ ከባንዲራ በላይ ነዉ!“
ለቁጥር
አንድ መልስ በዚህ ሰጥቻለሁኝ። እርግጥ ነው እንደ ሄሮድስ መለስ ዜናዊ ባንዴራ ጨርቅ ነው ዓይነት አገላለጹን በሚመለከት አልነካካሁትም።
ሌላውን ጭብጥ ግን ትንሽ ሄጀባታለሁኝ። ለማያያዝ ነው ሊንኩን የለጥፈኩት የሁለቱ መንትዮሽ ፍንገጣ እና ጥሪያቸው መከተታል እኔ
ቀደም ብዬ ስገልጻቸው ከቆዬሁት ይሁን አቶ ጃዋር መሃመድ ወደፊት እንዲመጡ የነበረውን ምኞቱ ጋር ሃዲዱን እንድታገነዝቡት ነው።
በዚህ
ሊንክ ለሁለቱ መንፈሶቹ ያለውን ዕይታ የገለጸበት ነው አቤቱ አቶ ጃዋር መሃመድ።
„ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም?
– ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል“
- · ቁጥር ሁለት።
ምነው የጀመራችሁት የጃዋርውያን ንግሥና እና የአብይ ሌጋሲ የመንፍንቅለ መንፈስ ኩዴታ ተቀለበሰ ወይ? ብቻ ጠርጥር
ነው።
መቼም የተጀመረው የግልበጣ ሴራ ከተቀለበሰ በእውነትም ኢትዮጵያን ኤልሻዳይ አምላክ ይወዳታል። ድንግልዬም አልረሳቻትም ልዕልት ኢትዮጵያን ማለት ነው።
እንዲህ
ይሉናል የኦነጋውያን የልባዊነት የከፍተኛ ባለማዕረግ እጮኛ ዳግሚ አባኮስትር ያልኳቸው አቶ ንጉሱ ጥላሁን።
መልዕክት ለክልላችን ወጣቶች (ንጉሱ ጥላሁን)
August 13, 2018
„ባለፉት ሁለት እና ሦስት አመታት ተኪ የሌለውን ህይወታችሁን ጭምር ከፍላችሁ እነሆ ዛሬ የነፃነት፣ የፍትህ እና የእኩልነት ድባብ እንድንጎናፀፍ አስችላችሁናል ፡ ፡ የአንድነት፣ የመከባበር እና የፍቅር እንዲሁም የይቅር ባይነት መንፈስ እና ተስፋ እንዲለመልም አስችላችኇል“ የ ኢትዮጵያ
መንግሥት የ አማራ ማንነት የህለውና ታገድሎ ለወጡን አመጣ ብሎ ያውቃለን? ብአዴንስ ደፍሮ ተናግሮታልን? አቅመ ቢስ ሰለሆናችሁ
ሁል ጊዜ ካሬታ ናችሁ።
- · በለው!
ለመሆኑ
ትዝ ብሏችሁ ያውቃልን የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ መስዋዕትነቱ እና ውጤቱ? ለመሆኑ ስለ መፈጠሩስ አስተውሳችሁት ታውቃላችሁን?
ለመሆኑ የአማራ ጀግኖች የት እንዳሉ ታውቃላችሁን? ለመሆኑ ስለ አማራ ማንነት ምን የምታውቁት ነገር አለ? ስለ አማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ጥልቅ ፍልስፍና እና ዘላቂ ተልዕኮስ የምታውቁት ነገር አለን?
ይህን
ያህል በውጭም በአገር ውስጥም፤ በሊሃቃኑም በሁሉም ሲገለለ፤ ተጋድሎው
ሲገፈተር የአማራ የማንነት የህልውና ታገድሎ
ማለት ሃጢያት ሆኖ እንደ አልባሌ ማበሻ ጨርቅ ሲወረውር፤ ጠያቂና ባለቤት አልባ ሲሆን፤ ዕውቅና ሲነፈገው ለመሆን
የትኛው ፕላኔት ላይ ይሆን እናንተ ያለችሁት?
የአማራ የህልውና
ተጋድሎ ኮከቦቹ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ቢሯችሁ ጋብዛችሁ በምን አጀንዳ አወያያችሁ? ማደኝነታቸው ቀርቶባቸው ማለት ነው። ክብር አላችሁን ለእነሱ እነሱም እኮ ዜጎች ናቸው።
ለቄሮ ጀግናችን ስትሉ አማራ ተጋድሎ የምትለውን ቃሏን አውጥታችሁ ተናግራችሁ ታውቃለችሁን? ታሪካችሁ ነበር እኮ፤ እምትኮሩበት እኮል እምትሆኑበት አፈሰሳችሁት እንጂ።
የትሜና ልክ እንደ ማበሻ ጨርቅ የጣላችሁት
የዘመናት መከራ ነቃይ አብዮት እና ታጋዮቹን መሰረታችሁን ጥላችሁ አሁን መንፈስ ልመና ገባችሁ? እንኳን ለዚህ አበቃን ነው መቼም?
ከቄሮ
ተራራ ዝቅ ብላችሁ ከዝብርቁ የማንነት ቀውስም ወጥታችሁ ለአማራ ወጣት ተማህጽኖ ማቅረበችሁ ከተጋድሎው የታሪክ ምዕራፍ ዝርዝር
ውስጥ ይገባል።
እናንተን
ለዚህ ክብር ግርማ እና ሞገስ ያበቃው እኮ ያ ተዘርዝሮ የማያልቀውን ግፍ እና መከራ የተቀበለው የአማራ ህዝብ ነው። ልጁን ገብሮ
፤ ትዳሩን ፈትቶ፤ ከሥራው ተፈናቅሎ፤ ተገሎ እና ተቀጥቅጦ አካሉን አጥቶና አጉድሎ። ለመሆኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ትዝ ብሎዎት ያውቃልን
አማራነት? አያሳፍርም!
ሌላም
የሰሞናቱ ጭብጥ ይገለጥ አሁን እነኛ ብፅዕን አባቶች ከ27 ዓመት ስደት በኋዋላ አገር ሲገቡ ሂዳችሁ ለመቀበል አቅም አጣችሁን?
ለኦነጋውያን ግን ከሚሊዬነም አዳራሽ እስከ ባህርደር ተነጠፋችሁ ዝቅ ብላችሁም ሰገዳችሁ። ማፈሪያ!
የአማራ
ወጣት ዛሬ ሳይሆን ነገን አስቦ ሁሉመናውን በአቅም በብልህንት በስልት እና በጥበብ ከያዘው ከማንም እና ከምንም ጥገኝተን የማያስኬደው
የእኔ የሚለው የመንፈስ አቅም አለው። እሚፈራውም ለዚህ ነው። አማራ ሰዋዊም ተፈጥሯዊም ነው እኔ የማውቀው አማራ።
ይህን
ታውቁታላችሁ እናንተም። ስለምን ይሆን አማራ መሬት ላይ የሁለም መንፈስ ሰፍ የሚለው? ስለምን ሌሎች ክልሎች አቀባበል አይኖርም?
ስለምን ነው አማራ ለ66ቱ የማርክሲስት ሌሊኒንስት ብልዝ እና ስርዝ
አይዲዮሎጂ ቅጥቅጣ ዳግም በተለያዬ አቅጣጫ መንፈሱ እየታወከ በራሱ ጉዳይ ላይ አንዳያተኩር መሰናክል የምትፈጥሩት። ስለምንስ ነው የጉሮሮ አጥንት የሆናችሁት።
ለነገሩ
አሁን ደግሞ ቀጥሎ አማራ ግንቦታውያን ነበር ብላችሁ ደግሞ አቀባባል አዘጋጁ እና ለወያኔ ሃርነት ትግራይ መህተሙን ቅረጹለት። እናንተም ነበር ብላችሁ ፈርሙ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ያሰርከው፤ ጥፍር ያወለቅከው፤ ያንኮላሸኸው በትክክለኛው ሰነድ ነው ብላችሁ አማራን አሰልፋችሁ ለራሱ መካራ ራሱ መስካሪ እንዲሆን አድርጉት። እዬሰማንላችሁ ነው ገማናችሁን።
መቼም
ልብ እሚባልስ አልፈጠረላችሁም። ጎንደርም እንኳን በሌለህበት የልጆች ዘር ማፍሪያ ተንኮላሸ ብላችሁ አቀባባል ውጣ እና አረግርግ
በሉት። መቼም ማፈሪያ የላችሁም እና። ጎንደር በ አውሮፕላን መጨፍጨፍ ነበርብህ የግንቦት 7 ደጋፊ ስለነበርክ ብላችሁ ቀይ ጃኖ አስልብሳችሁ አቀባባሉን አስኪዱት። ምን አለ ጎንደር መመኮሪያ ጣቢያ ነው ለሚመጣውም ለሚሄደውም።
ጎንደር
አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ሊገድል ነበር ስለተባለውም ዜና እልልል ብላችሁ አሽኮኮ አድርጉትን ፈርሙለት። ፋሲል ግንብም አብርህ ገዳይ ስለመባልህ
ተጎብኝ በሉት። ምን ሲቸግር? ጥቃትን አድግድጎ አሰልፎ ቀይ ጃኖ አስልብሶ መቀበል። ጠጠርነት ነው ይሄ።
ስለምን
ነው የአማራን ሰላማዊ እና ማህበራዊ ህይወት ማበከን የምትፍልጉት? ጥርስ ውስጥስ ለማስገባት ስለምን ነው መከራውን የምታበሉት?
አታውቁት አያውቃችሁ።
በዬጊዜው
ማህበራዊ ሰላሙን አጥቶ እንዲበዝን ዘመናዮችን ተቀባይ እና ሸኚ የሚሆንበት ምክንያት ስለምን ነው አማራ? ስለምን እናንተ ቦታችሁን አትለቁም?
ኑራችሁም አላማረባችሁም እና?
የት
እምታውቁትን የአማራ ተጋድሎ ነውና? ኦህዴድ ቁጭ ብላችሁ ስታንቀላፉ እዬጣላችሁ ማለፉን አታዩትንም? ከዱከም እስከ ቢሸፍቱ የኢንደስትሪ
ከተማ ለማድርግ የተጀመረውን ፕሮጀክት አላደማጣቸሁንም? አይበቃም ወይ ቀልዱ?
አማራ
በቀዬው ባበድማው እንዲህ ሆኖ ነው የኖረው።
„እኔም ተመለስሁ፣ ከፀሐይ በታችም የሚደረገውን ግፍ ሁሉ አዬሁ፤ እንሆም የተገፉት ሰዎች እንባ ነበር፤ የሚያጽናናቸውም
አልነበረም፤ በሚገፏአቸው እጅ ሃይል ነበር፤ እንርሱን ግን የሚያጽናናቸው አልነበረም።“
ከአለ አንድ ባሊህ ባይ፤ ካለ አንድ አጽናኝ፤ ካለ
አንድ አይዞህ ባይ 27 ዓመት ሙሉ። አሁን ደግሞ ለአዲስ እርድ ለኦነግውያን እዘጋጁት … ምን አለ ምድሪቷ የአማራ ደም ካለዬች
አይሆንላትም እና ለአዲስ ለሰላ ሁለት አፍ ለለው ማጭድ እንዲህ አዘጋጁት። ምን ሲገድ የአማራ እናት ትውለድ ለዬዘመኑ ማገዶነት ለሰው ሊኳንዳ ቤት።
ለጃዋርውያን
ተልዕኮ እና የግልበጣ መንፈስ ነው ያ ሁሉ 20 ሺህ ወጣት የታሰረው? ጥፍሩ የወለቀው? አካሉ የተኮንላሸው? የሞተው? የተሰደደው?
ባድማው የተቃጠለው ለአቶ ዳውድ ኢብሳ መንፈስ ነበርን? ማፈሪያ!እናም ለግንቦት 7? ይሄው ነው መሰናዷችሁ። እንደ እናንተ ለ አማራ በጸርነት የተሰለፈ ፍጥርት የለም። ጥቃትም የማያወጣ።
የጀመራችሁት
የቆያችሁበት ሴራ ግብግቡ ከቅንነት ጋር ስለነበር ልዑል እግዚአብሄር በኪነ ጥበቡ ይፈታዋል። የአማራ ጀግኖች በወለቃ ሲገቡ አቋጣሪ
የላቸውም፤ በቦሌ የገባው የፌስ ቡክ ጀግና ግን ምን እና እንዴት እንደተሆነለት እኮ ታይቷል።
ለዛውም
ለግራጫማ ሰብዕና። ለዛውም ስሜት እና ፍልስፍና ድብልቅል ላለበት፤ በተመክሮም በሁለመናም ከእርሰዎ ሊያሚያንስ ሰብዕና ያን ያህል
ከፍ እና ዝቅ? ያሸማቅቃል!ኦህዴድ አቻ ድርጅታችሁ ነው ግን ቀጥ አድርጎ አንቀጥቅጦ እዬነዳችሁ ነው። ደግ አደረገ።፡
ትድናላችሁ
መስሎኝ ነበር እኔ በይቅርታ መንፈስ ቢታገዙ እያልኩ የደከምኩት። ለነገሩ የእርሰውን መንፈስ አፍነጋጭነት አስቀድሜ ስለተረዳሁት
በጥንካሬዎት ላይ ብቻ ነበር አትኩሮቴ።
እርግጥ
ነው እኔ የገዱ እና የአንባቸው መንፈስ የተሻለ ራዕይ አላቸው ቢታገዙ የሚል ሃሳብ ነበረኝ። ግን ራሳችሁን ለመሆን አቅም የላችሁም።
አማራ ጥገኛ ለዛውም የመንፈስ ሲሆን እጅግ ይጎመዝዛል።
እንግዲህ
ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ከዬትኛው እንደሆኑ ደግሞ እሱ ይሁናቸው። መቼስ ፍትነት በዬደቂቃው ማንዘርዘሪያ ስለሰራልን ማን ምን እንደሆነ
ገማናው ብትከድንቱም ውልብሊቢቱ ግን ምን እና ምን እዬሆነ እንደሆን እዬደረሰብነት ነው።
ለመሆኑ ለእናንተ ቆሞስ ስመኘው በቀልስ፤ ቆመስ አቶ ተስፋዬ ጌታቸውስ ቁስሉ እንዴት ይዟችሁ ነው አሁን እንዲህ ሠርግ እና መልስ የተሆነው። ፍቅሩ ከግራጫመነት ስብዕና ጋር ብነግረዎት የሳሙና አረፋት
ነው ከግራጫማ ሰብዕና ጋር መተንፈስ ትርፉ ድካም ነው ወይንም ድንጋይ ላይ ውሃ ማፍሰስ።
- · ክሽፈት ይሆን ይህን ሆደ ቡቡነት ያመጣው?
የሆነ
ሆኖ ይህን የምጽዕት ጥሪ ሳዳምጥ የመንትዮሹ መፍንቅለ መንፈስ ከሸፈ ወይ አሰኝቶኛል። ሚሊዮኖች የሰገዱት ለቅንነት እንጂ ለሸር
እና ለተንኮል አልነበረም። ለዛውም ለኦነጋውያን … ህም!
በእናንት
ምክንያት እንጂ እኔ አጀንዳዬም ሆነው አያውቁም። ምኔ ሆነው ነገስ ምኑ ስለሚሆኑ ልድከም እና?
የፈለጋችሁት
የአማራ ወጣቶችን አቅጣጫ ለማስቀዬር ነው ሥራ እየሠራችሁ ያለችሁት። ለነገሩ የአማራ ተጋድሎ መሪ አለው። መሪውን ይከተላል፤ ደግሞ
በምግብ ብክለት እንደ አቶ ተስፋዬ ጌታቸው ሌላ ጣጣ ካላመጣቸሁ።
ሰምቻለሁኝ የአማራ ወጣቶች ማህበር እንደ ተመሠረተ። የተረሳ ዜጋ፤ ዜጋ አይደለህም የተባለ
ነፍስ ቢያንስ ስለመኖሩ ራሱ ለራሱ ይንገረው እንጂ እንዲህ። የማለደብቀውት ነገር ግን በመንፈሳችን ውስጥ ያለው የአማራነት ቋያ የሚፋጅ ስለመሆኑ ነው።
- · ማነው ባለሳምንት ይጥመድ በ18 ..
ተረኛ እንግዳ ደግሞ አላባችሁ መሰል፤ በቅድሚያ የመጡትን
አንጣፊዎችን ሰምተናል የጎንደር ማህበርን ሰምተናል አመላቸው ነው ስጋጃ አንጣፊነት። ግን ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን እርስዎ በመንፈሰዎት የብአዴን ወይንስ የዬትኛው ድርጅት አባል ነዎት? ይህ
ደግሞ በቀጣይ ቀናት ይፋ ይሆናል?
- · የምደግፍው ጥሪ የእኔም በዚህ ውስጥ ነው።
ማቃጠል አትራፊ አይደለም። ያለችን ድሃ አገር ናት፤
በዛ ላይ አማራ በለቤት የሌለው ማህበርሰብ ነው። ስለዚህም ያቺ ያለችውን ጥሪቱን ማቀጣል፤ ማንደድ አይገባውም። በፍጹም። ከአመድ
ምን ትርፍ ይገኛል። ከበቀልስ ምን ትሩፋት።
ማቀጠል እኮ ሃላፊነት የጎደለው ሰብዕና ውጤት ነው።
ትናንት አቃጥሉ አንድዱ ሲል የነበረው አቶ ጃዋር መሃመድ ስለምን መንፈሳችን ሳይቀበለውም ሳያገለውም ኖረና። በዚኸው የናደው ተግባሩ ነው።
ምንም ነገር ይሆን መቃጠል የለበትም። ምንም ነገር
ይሁን ቂምን በቂም የመመለስ ሙከራ መምከን አለበት። ምንም ነገር ይሁን አሁን በቀሉ ቢቀጥል ነገም ቢቀጥል ሥልጡን ህዝብ ወገኑን ገድሎ አይጨፍርም። በወገኑ ሃዘን አይዳንስም አማራ።
በወገኑ ሬሳ ላይ ከበሮ አይደለቅም አማራ። ዘመን
እና ጊዜ በመንፈስ ቢያለያዬንም ዘመንም ደግሞ መልሶ ማገናኘቱ ስለማይቀር ከክፉ ነገር መቆጠብ በእጅጉ ይገባል። መግደል ወንጀል
ነው። በሰማይም ቅጣት አለበት።
አብሶ አማራ ክልል የለውም፤ አማራ ክልልህ ነው ብሎ
በተሰጠውም ቦታ ቢሆን በተለመደው የአባት አደሩ ወግ ባህል ልማድ እና ትውፊት መሰረትነት በማንም ላይ አይደለም ጥቃት የጠቆረ ፊት
እንኳን ማሳዬት አይኖርበትም። ይህን ማድርግ አማራነትን ጥያቄ ውስጥ ያስገባዋል። የአማራ ገበሬ በሬውን አያ አይዋ ሆይ! እያለ
እኮ ነው እያቆላመጠ እንዲያገለግለው የሚያደርገው፤
ዘመን እንዳጠቆረን እንዳይቀር መልካምነት መርሃችን
መሆኑን በመሆን ማስመስከር ይገባል። ፍቅር ሰጥቶ፤ ይቅርታ ብሎ የተጎዳ ነፍስ የለም። ቢያንስ ስናልፍ በሰማይ ብርሃን አለ።
በዚህ የማፍረስ ተልዕኮ፤ ቂም ዘር ተልዕኮ፤ የጥላቻ
ተልዕኮ፤ አባቶቻችን አልኖሩበትም። ስለምን? ብዙ አገራዊ ድርሻ ነበረባቸው። ሃይማኖታዊ፤
ትውፊታዊ፤ ቅርሳዊ፤ እውቀታዊ፤ ፍልስፍናዊ እጅግ ዘርፈ ብዙ ሃላፊነት ነበረባቸው። አባቶቻችን እና እናቶቻችን ስልጡን ነበሩ።
ስለዚህ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ያበከኑት ጊዜ
የለም። ዛሬን አበጅተውልናል። አለን የምንለው ሰጥተውናል። ለመንፈሳችን ለሥነ ልቦናችን
የሚሆን በቂ ጥሪት ሰርተውልን አልፈዋል። ስለምን? አባቶቻችን እና እናቶቻቸን ሥራ ፈት አልነበሩሙ። የቂም እና የበቀል ችግኝ ሲኮተኩቱና
ሲያስተምሩ አልኖሩም።
አንኳንስ ለእኛ ለአውሮፓ የበቃ የበቀሉ ሊቀ ሊቃውንታት
ነበሩ። ስለዚህ ማቀጠል ሥራ ፈትነት መሆኑን በመገንዘብ በጊዘያችሁ በመጠቀም በማንበብ፤ በመጻፍ፤ በመመራመር፤ መንፈስን በማላቅ
ተግባር ላይ መታተር ያስፈልጋል።
አብሮ የሚኖረውም ወገናችሁ ኢትዮጵውያን ነው። ሰው
እና ተፈጥሮ ፍጥረትነታቸው የፈጣሪያቸው ነው። ህግ መተላለፍ አይገባም። ከህግ በላይ መሆን የተገባ አይደለም። ለዚህ ነው ልብ አምላክ ዳዊት "ህግ ተላአለፊዎችን ጠላሁ ያለው"
„አማራነት ይከበር!“
ልክ እንደ ኢትዮጵያዊነቴ አማራነቴንም አውደዋለሁን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ