እኛ የሚያስፍለግን የአብይ ጤነንት ከነቤተሰቡ ነው።

„አያ ጅቦ ሳታማህኝ ብላኝ።“
„በአምላክህ በእግዚአብሄር ፊት የተጠላ ነውና ነውር ወይንም ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይም በግ ለአምላክህ ለእግዚአብሄር አትሰዋ።“ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 13.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ቀልቤን የሳበው ጹሑፍ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የጻፈውን ከሳታናው ብራና ላይ አገኘሁ እና ሁለት ነገሮችን ነቅሼ ማውጣት ፈለግሁኝ። ጹሑፉ የትናንት ነው የሻሸመኔው አሰቃቂ ግድያ ከተፈጸመ በፊት እና በኋዋላ ስለመሆኑ እማውቀው ነገር ስሌለ ልዝለለው። እርእሱ እንደምታዩት ነው።

አሁን ያለው መፈንቅለ መንፈስ ኩዴታ የማን ስለመሆኑ በማን ስለመማራቱ ፍንጭ ማውጣት አልፈለገም። ሁሉንም ችግር ጠቅልሎ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ላይ ነው የደፈደፈው። የችግሩ አንኳር ያለው ግን ኦህዴድ ላይ ነው። በተቀጥላ ብአዴን ላይም እዬታዬ ነው። አሁን በቅደመ ተከተል ሁለቱን እንሂድባቸው።
„ህወሃት ከቤተመንግስት ተባሮ መቀሌ ከመሸገ ወዲህ ሁለት ግንባሮችን ከፍቶ በሰፊው እየሰራበት ነው (መሳይ መኮንነ)“
August 12, 2018
  • ·      ቀዳሚው።

„ከአንድ ሰሞን ዘመቻ ተላቀን በራዕይና ተልዕኮ በተቀረጸ የተግባር እርምጃ ላይ እናተኩር ዘንድ የሁላችን ቅን ልቦናና ዝግጁነት የሚጠይቅበት ወቅት ላይ ነን።“ እህ ቅንነት? ? ? ?

መቼ ነው የእኛ የነፃነት ትግል ከንፋስ ወጀብ ወጥቶ የሰከነ ሥራ ሠርቶ የሚያውቀው። ይህን እራሱ ድርጅቱን ይጠይቀው። ጥያቄ ሚዲያውን ሳይሆን የራሱን የፖለቲካ ድርጅትን ግነቦት 7 ማለቴ ነው።

ባለፈው ዓመት ይህን ግዜ ትንሳኤና ህይወት እኛ ነን የሚል  በአውሮፓው ህብረት አንድ ክንፍ የሚመራ የሸግግር ሰነድ አዘጋጅቶ ነበር አገር አቀፍ ንቅናቄው፤ አሁን ደግሞ በተናጠል እዬገቡ ነው ማህበርተኞቹ፤ ልንገባ ነውም እዬተባለ ነው፤ በማከብራቸው አቶ ኮንቴ ሙሳ የሚመራው የአፋር ድርጅት ተነጥሎ ለጠ/ ሚኒስትሬ የሰላም ኖቤል ሽልማት ሎቢ እያደረኩኝ ነው ብሏል። ቅንነቱንም ንጽህናውንም አይተናል የድርጅቱን። 

የኦቦ ሌንጮ ለታ ቡድን አገር ቤት ቀድሞ ገብቷል። ለመሆኑ ያን ያህል የተዘፈነለት አገራዊ ንቅናቄው የት ገባ?

ሌላም ግንቦት 7 የትጥቅ ትግሉን አቁሞ በአዲስ መንፈስ ሰላማዊ ትግሉን ለመቀጠል አገር ውስጥ ለመግባት በቂ መሳናዶ እዬተደረገ እንዳለም እያደማጥ ነው። አቀባበሉም አሸነፊ ድርጅት ስለሆነ ማለቴ ወያኔ ሃርነት ትግራይን አርበድብዶ አፈር ድሜ አስግጦ ስለሆነ ሆ! እዬተባለለት እልል ኩልል እዬተባለለት ሊጋባ መሆኑን ሰምተናል። ለ እሱስ ስለምን ይቀርባታል። እሱም አንድ አካላችን ነውና። በሚዛን ሲለካ ማለቴ ነው። ስለምን ከዚህ ቀደም ለሚገቡት አልተደረገም ለሚለው ያው በተደጋጋሚ እንደተናገርኩት የራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ መሪ ስለመሆኑ ገልጫለሁኝ።

 ያው እኔ እንደማስበው ለ እነ ጃዋር መሃመድ የተደረገው፤ የተፈጠረው መድረክ ሁሉ ለግንቦታውያን ይሆናል፤ ከልጅልጅ ቢለዩ አመትም አይቆዩም እንደሚባለው።

ሌላው ግንቦት 7 የትጥቅ ትግል ማቆሙ አዲስ ሊሆን አይችልም። ያስታጠቀችው ኤርትራ ትጥቁን ፍቱ እና ብትፈልጉ እዚህ ባትፈልጉ አገራችሁ ገብታችሁ ታገሉ ማለቷን ዘሃበሻ አስደምጦናል። ይህን ማድረግ ደግሞ ኤርትራ ግድ ይላታል። ያን የመሰለ የፍቅር ዕዳ እና አደራ የተሸከመ የፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥት ይህን ቢያደርግ የሚደንቅ አይደለም። 

በሌላ በኩል ግን ኢትዮጵያ ኤርትራ መዳፍ ውስጥ ቀስ እያለች ሰተት ብላ እዬገባች ነው። የአቶ ጃዋር መሃመድ ሆነ ነገ የምናዬው የግንቦት 7 አቀባበል እና የውይይት ፕሮግራም ከዬትም የመጣ ጫና ነው አንድንል ግድ ይለናል? በጀቱስ ሸፋኙ ማን ነው?  እርዳታ የማያስፈልግ ከሆነ ማለቴ ነው።

እንግዲህ ቅደመ ድርድር አለበት ማለት ነው ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር። ኤርትራ ስትረዳቸው የነበሩት የፖለቲካ ድርጅት የፖለቲካ አቅም ካለገኙ ምቾት አይሰጣትም።

ይህን ባትቀበል ኢትዮጵያ የ አሰብ ወደብ የመጠቀም ዕድሏ ይጠባል። በሌላ በኩል ከ20 ሺህ የማያንስ የጦር ሠራዊት የአቶ ሞላ አስገዶም ደምሂት በመዳፏ ነው። አሁን በሯ ክፍት ነው። ፍቅር አስከፍቷል።

 ሌላም ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ባደረጉት የቀጥታ ውይይት ጁቡቲ የጀመረችው የተደፈርኩ ዘመቻ አለ። አሁን ጅቡቲን አታሎ ለማምጣት ሌላ ፈተና አለበት የ ኢትዮጵያ መንግሥት፤ ኤርትራን ላቆላምጥ ከተባለ የአብይ አስተዳደር አቶ ጃዋር መሃመድ እና ግንቦት 7 እንዲሁም  የአቶ ዳውድ ኢብሳን፤ የግረ ከይሲውን የ አቶ ተስፋዬ ገብርአብን ሌጋሲ አካታች መሆን አለበት።

ወደብን በሚመለከት ኢትዮጵያ ቢከፋይ ብመለስ እንዳትል ሆና ተሸምደምዳለች። ይሄን በስክነት ማዬት ይጠይቃል። ደግሞ አሰብ ለ አንድ ትውልድ ዕድሜ ያህል የሌላ አገር ኩንተራተኛ ስለመሆኗም ተደምጧል። ይሄ ከታወቀ የ አሰብን ወድብ መነካካት አይገባም ነበር። ከጁቡቲ ጋር ያለውን አጠናክሮ መቀጠል አሰብን እንደ ግንኙነቱ ጥንካሬ እና መሰረት መያዝ ቀስ ተብሎ በርጋታ ሊያዝ የሚገባው ነበር። ለነገሩ በመንትያ ልብ የነበረ አማካሪ ከነበረ ይሄ እንዲሆን ግፊቱ መኖሩ ደግሞ ሌላው አመክንዮ ነው። ሰው ግን ስንት ልብ ይሆን ያለው? ሳዬው ቀስ እዬተደረገ የ አብይ መንፈስ ስንጥቅ ውስጥ እንዲገባ ሲደረግ እንደቆዬ ማስተዋል ይቻላል።  

የዚህ አገናኙ ደግሞ አቶ ሃብታሙ አያሌው ናቸው። አንድ ጊዜ ገበርዲኑን ለብሶ ዲሲ ላይ የሚንጎባለለው ብዬ የጻፍኩት እሱ ነው። ተከፋይ ነው። ለአማራም መከራው አብሶ ጎጀም እና ጎንደርን ለመነጠለ የተፈጠረ የሰላ ማጭድ ነው። ያ የነጠረ አማራዊ መንፈስ በፍጹም አልተመቸውም አቶ ሃብታሙ አያሌውን። በብአዴን በኩል አንባሳደር አቶ ንጉሡ ጥላሁን ሁለገብ ናቸው። 

በኦህዴድ በኩል  የነጠለው መንፈስ እንዳለ ሂደቶችን በጽሞና መመርምር ይቻላል።ይህን እያወቀ ነው እንግዲህ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ልቦናችን ወያኔ ሃርነት ትግራይ ተኮር ብቻ ይሁን የሚለን። ይህ ሁሉ አብሳ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ ነው እያለ ነው የሚያጃጅለን። ወያኔ ሃርነት ትግራይን 27 ዓመት እሱ ያውቃዋል እኔ ደግሞ ከሱ በተሻለ ከዚህም ረዘም ላለ አመት  አውቀዋለሁኝ። በዛ ላይ ጎረቤታሞች ስለሆንም በሥነ ልቦና እንተዋወቃለን። ስለዚህ አቅሙን በምን መልክ እንደሚሰነዝር እና ውጤቱና ሂደቱ አዲስ አይደለም። 

አሁን አፍንጋጩ የመንፈስ ጠላፊውን አንጃ ነው መመርመር የሚያስፍልገው። በዚህ ግርግር የሚመጡ የህዝብ ሰላማዊ ሰልፎችን ሁሉ መዝጋት ያስፍልጋል። ውጪ ያሉ ቅኖች ብቻ ለሚያገኙት አካላት መረጃዎችን መስጠት ይጠበቀወባቸዋል። እንጂ በገፍ ወጥቶ መጨፍጨፍ የማይታሰብ ነገር መሆን አለበት። 

አያድርገው እና የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በህይወት  ባይኖሩ የተዶለተው ይሄው ነበር። እራሱ የአዲስ አባባው የድጋፍ ሰልፍ ጤነኛ አልነበርም። እኔ ተቃውሜ ጽፈያለሁኝ። ወደፊትም ቢታሰብ ከጤና አይሆነም። መፍትሄው አለመውጣት ነው። 

በጠ/ ሚር አብይ የህዝብ ፍቅረኛ መሆን ያልተቃጠለ  ሰው ታዋቂ ሰው ማግኘት ከባድ ነው። እጅግ ጥቂት ቅን ሊሂቃን ናቸው ይህን መንገድ በቅንነት የደገፉት። ከፖለቲካ ድርጅት መኢሶን እና የዶር ኮንቴ ሙሳ ድርጅት እንዲሁም የዶር ኦባንግ ሜቶ የሲቢክ ድርጅት። ሌሎቹ ከፖለቲካ ድርጅት ምንም ንክኪ የሌላቸው አገር ወዳድ ዜጎች ናቸው። ዶር አብይን የደገፈውም በብዛት የማንፌስቶ ማህበርተኛ ያልሆነው፤ ባለቤትም ያልነበረው የእኔ ቢጤ ቅኑ ሳይለንት ማጆሪቲ የሚባለው የማህበረሰብ ክፍል ነው።

ሌላው በለውጥ ሃይሉ ውስጥ የተፈጠረውን አንጃ በራሱ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ሊያነሳው አልደፈረም። ለምን? ለነገሩ "የልጅም እንደሆን ይጋፋል የቂጣም እንደሆን ይጣፋል" እንዲሉ ነው።፡
  • ·      ተከታዩ ጭብጥ።

„ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው እንዲሉ በተባራሪ፤ አፍና ጭራ በሌላቸው ሀሰተኛ ወሬዎች ህዝባችን ምን ያህል እንደሚደናገጥ የሰሞኑንየአብይ የመግደል ሙከራወሬ አይነተኛ ማሳያ ይሆናል።“  ይህ የጋዜጠኛ መሳይ መኮነን እማተኩርበት ነጥብ ነው።

ምን በአደባባይ እኮ ሰኔ 16.2018 ግድያ ተከናውኗል ማን ከወነው? አብሮስ ማን ነበር? ስለምንስ እንዲዳፈን ሆነ? ስለምንስ ቀጠሮ ይራዘማል? ማን እና የትኛው ድርጅት እንዳይገላጥ ተፈለገ? ነገስ?

የሆነ ሆኖ በዚህ በጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ትንተና ደግሞ ዶር አብይ አህመድ ምንም ችግር አልደረሰባቸውም እያለን ነው ከሰሞናቱ። ለዚህም ወሬውን የሚያናፍሱት የወያኔ ሃርነት ትግራይ ሠራዊቶች ናቸው እያለን ነው። እምደግመው ለመሆኑ የሰኔ 16ቱ ጥቃት ተጣርቶ ለፍርድ ይቀርባል እዬተባለ በቀን ማራዘም ያለውን ድርማ እንዴት ያዬዋል ጋዜጠኛው? ያን የግድያ ወንጀል ማን አቀደው? መጀመሪያስ ሰላማዊ ሰልፍ ማን ሃሳቡን አቀረበው? እንዴትስ ቶለ ተፈቀደ? ስለምንስ ሰለ ነገረ አባይ ጥያቄ ቀረበ? ስለምንስ መልሱ ፖስት ተደረገ? ስለምንስ ቆመስ ኢንጂነር ስመኛው በቀለ በግፍ ተገደለ? ማነው ይህን ሁሉ ፈጻሚው? ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብቻ?  

የሀምሌ 19 የቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው አሟሟት ጉዳይ? የባለቤታቸው መሰውርስ? ስለምን የውሽማ ሞት ሆኖ እንዲዳፈን ተደረገ? አልቃሾች እኮ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ቀብርም ተከልክለዋል ስለምን? እውቁ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ያለው የለም። ድፍን ነው። 

በጣም የሚመርመረው ደግሞ የዶር አብይ አህመድን ሌጋሲ አፈር ድሜ ለማስጋጥ በመንግሥት ደረጃ ተፈቅዶለት አቶ ጃዋር መሃመድ እና ሌሎችም እዬሠሩ ያለውን ተግባር ሊነካካው አልፈቀድም። በጀርባው ያለው አሰተባባሪ ቀልባሽ መንፈስን መድፈር በፍጹም አልፈለገም ለምን?

ለመሆኑ የአብይን ሌጋሲ ለማስቀጠል ግንቦታውያን እንሱ ይፈቅዱታልን? ወደለውለታል የአብይን መስመር? ወደውለታል የአብይን ተወዳጅነት? ወደውለታል የአብይን ብቃት? ስለምን የለበጣ ጉዞ እንደሚያስፈልግ ግራ ይገባኛል። 

ቀድሞ ነገር ዶር አብይ አህመድ ለእኛ ሊፈጠር የማይገባው ድንቅ ሰው ነበር። ግን ነገር ግን  ከእኛ ተፈጠረ እና እሱን አስወግዶ የራስን ሃይል ለማስቀመጥ ነው ሸር ጉዱ አሁን። መሪ ደግሞ አለው። መሪው በጀት መድቦ እዬሠራ ነው። ኢትዮጵያ በቅታ ማዬት እኮ ህልማችን አይደለም? በፍጹም።
  
ዶር አብይ አህመድን ኦህዴድ አሁን ምረጠው ቢባል ደግሞ ይመረጠዋል ወይ? ወይንስ ቀጣዩ ከኦህዴድ ሊቀመንበርነት አስወግደነዋል ውሳኔ እንጠብቅ ወይ? ወይንስ በአስቸኳይ ጊዜ የፓርላማ ጥሪ እረፍት ላይ መሆናቸውን አውቃለሁኝ ግልባጭ አንጃዎቹ ሌላ ጥያቄ አንስተው መምራት አልቻለም የአብይ ካቢኔ ብለው ሌላ ግርግር ይፈጥሩ ይሆን? 

ክንያቱን ዶር አብይ አህመድን ገድለን የፈለገነው እንዳርጋለን ብለው አሰቡት ሁለት ጊዜ ለጊዜው ከሽፏል። እገታም የለም እሱን አትሰቡት ነው የሚለን ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን። ቀልዱ ይቁም እሺ!

እገታውም ግድያውም ነበር። ይህን ያደረገው ደግሞ ከለውጥ ሃይሉ ውስጥ የተፈጠረው አንጃ ነው። ያን አንጃ የሚመራው ለጊዜው አይታወቅም። ባውቀውም አልናገረውም። 

ኢትዮጵያ ስንት መንግሥት እንዳላት እዬታዬ ነው። የትናንቱ ብአዴን ዛሬ ከአብይ ጎን ነው ወይ? የትናንቱ ኦህዴድ ዛሬ ከአብይ ጎን ነው ወይ? የትናንቱ 8 ቢሆኑ የደቡብ ህዝቦች ከአብይ መንፈስ ጋር ናቸው ወይ? ንጹሃንማ ቀድመው ተገደሉ እንደ አቶ ተስፋዬ ጌታቸው እንዲሞቱ የተደረጉት በዚህ ሚስጢር ነው። ዶር አንባቸው መኮነንም ቀኑን የሚጠበቅ ይሆናል። ኦህዴድ ላይ ተከድኖ ይብሰል ነው እነማን የአብይን መንፈስ እንደሚደግፉ።

ለዚህ ነው እኔ የመንፈስ ኩዴታ አለ የምለው። ሁለም አብዷል የሚሊዮኖች ድምጽ አብይ አብይ ሲል። ይህን ኩዴታ ደግሞ የሚመራው የወያኔ ሃርነት ትግራይ አይደለም። አዲሱ ለውጡ እኮ ከወያኔ ሃርነት አቅም በላይ ሆኖ ነበር። በመሃል ይህን እንዳይሳካ መሰንጣጠቅ የጀመረው ኦህዴድ ነው። ስለዚህ ተጠያቂው ኦህዴድ ነው። ኦህዴድ ቸኮለ አብይን ለማስወገድ። 

ኦህዴድ ቸኮላ የኦሮምያ መንግሥት የበላይነት ዓዋጁን ለማወጅ።  ብአዴን አካፋ ነው። ሲያረጅ ማንም እንደ ሻው የሚጠቀጥቀው። ትናንት ለሳጅን በረከት ስምዖን ዛሬ ደግሞ ለአቶ ንጉሡ ጥላሁን መንፈስ እያደገደገ ነው።
ከጥቂት ጊዜ በኋዋላ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በዚህ ትርምስ አቅም አግኝቶ እራሱን ችሎ ይወጣል። ስለዚህ አዲሱ የለውጥ ሃይል ውስጥ የተፈጠረው ለእነ ጀዋር መሃመድ ሆነ ነገ ለምናዬው ድራማማ ሽፋን እዬሰጠ ያለው የራስ ተሰማ ናደው ሌጋሲ ጋር ግብግቡ ይቀጥላል። እንዴት ጅማ ውስጥ አንድ ጠ/ ሚር ይፈጠራል ነው ዕድምታው እና ተደሞው።

ዋናው ፍሬ ነገር ዶር አብይ አህመድ በህይወት አሉ። ዓለም ትፈልጋቸዋለች። መቼም ጅማ ሊሂቅ ሲወጣ አመል ነው። ያን ጊዜ ሳይንቲስ አንጂነር ቅጣው እጅጉን አጣች፤ ዛሬ ደግሞ ካለዘመኑ የተፈጠረው ልጇን ልታጣ አፋፍ ላይ ናት። አሁን እኔ ያዬሁት ህልም ወንበሩ ባዶ ነው። መልሶ ከወንበሩ ሰው ሲቀመጥ አላዬሁም። ህልሜን እየጠበቅኩኝ ነው። ግማሽ ሙሉ የሰው ገጽ ግን አይቻለሁኝ። ያ መንፈስ ደግሞ ለጊዜው ውጭ አገር ነው። ያዬሁት ግማሽ ፊትም አገር አልገባም።
  • ·      እንኳንም ህይወታቸው ተረፈልን።  

አስደሳቹ ነገር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ውስጣችም መንፈሳቸውም ጤናቸው ደህና መሆናቸው ነው። ሥልጣኑን ግቡና ተቀራመቱት። እኛ የሚያስፈልገን የእኒያ ታይተውም፤ ተደምጠውም የማይጠገቡት ቅን ሙሴ የዶር አብይ አህመድ ህይወት እና የቤተሰባቸው ደህንነት ብቻ ነው። ደቡብ ላይ ስለምን ትርምስ እንደተጀመረ፤ ማን እንዳስጀመረው እኮ እናውቃለን።

ያ የጠቅላይ ሚኒስተሩ አቀባበል በ አዋሳ ያሳበደው መንፈስ ያቀደው እና የከወነው ነው። በወያኔ ሃርነት ትግራይ አቅም ብቻ አይደለም አሁን አገር እዬታመሰ ያለው። በውስጥም በውጪም ያሉ የአብይ መንፈስ ተቀናቃኞች ያሰናዱት የተቀባይንት መንፈስን የመራድ ትርኢት ነው።

የፖለቲካ መስመራችን እፉኝነት ነው። ሲረገዙ አባትን ሲወለዱ እናትን መግደል።

ዛሬ የተጀመረውን ለውጥ ያወለዱንት ዶር አብይ አህመድን አጥፍቶ በዛ ላይ ሌላ ንጉሥ ለማንገሥ ነው ዕቅዱ እና ትልሙ … ለሁላችሁም ሳይሆን አራቱ እግር አንዱ እጅ ላይ ወድቆ የተመኛችሁት የሲሪያ ዕጣ በእልቂት እና በእንባ ይወራረዳል። ኦህዴድ ያን የመሰለ ፖለቲካዊ አቅሙን የት ይድርሳል ሲባል ለስሜታዊነት ዳረው እና እንዲህ ሆነ ... ፈጽሞ እኮ የነበረው ቁመናው የታምር ያህል ነው የነበረው። 

ለአገርም ለወገንም ያን ንጥር መዋለ ሃብቱን ማዋል ተስኖት እንዲህ ሲሆን ለደከሙት፤ ለለፉት ለማሰኑት የራሱ ወገኖች መርዶ ነው። ሚሊዮኖች ለማውያን ነን ማለታቸው ከውስጡ ሊየስገባው፤ ከመንፈሱ ሊ ያስጠጋው አለመቻሉ ዛሬ ላይ ሆኖ ቢያስበውም ቢመዘንውም ደግሞ የማያገኘው ዕድሉ አምልጦታል ብዬ አስባለሁኝ። 

እነ አቦይን ተሸክሞ ይህን ያህል ሙሽርነት የሚስፈልግ አልነበረም፤ አሁን ያው በተለመደው ንፋስ መመራት ነው፤ አቅምስ አቅልስ ካልተሰጠ ከዬት ይመጣል? የዶር አብይ አህመድ ንጽህና ከዛሬ በላይ ነገ ይታያል። እዬነጠረ የሚታዬው ዛሬ አይደለም። ኪንግ ማርቲን ሉተር አቅማቸው የታወቀው ከታጡ በኋዋለ ነበር … ይህን ደግሞ ማጠቃለያውን አብይ ኬኛን ማንበብ ነው … ቀድሜ ተናግሬዋለሁኝ። 

ዛሬማ አላወቅንበትም የውጭ መንግሥታት በጉዳያችን ጣልቃ እንዲገቡ የኢትዮጵውያን መንፈስ ቅኝ እንዲገዛ የባንዳነት ተግባር እዬተከወነ ነው … ያለው። እሲኪ ባለስድስት ክንፎች የአገር መሪ ሆነው ደግሞ ይታያሉ …  
  • ·      ሌላው ያላለቀው ጦርነት …  

ኦህዴድ በውስጡ የተፈጠረው አንጃ፤ የዳውድ ኢብሳ አንጃ፤ የአቶ ጃዋር መሃመድ አንጃ፤ አድፍጦ የተቀመጠው የአቦ ሌንጮ ለታ አንጃ፤ እና የዶር መራራ ጉዲና አንጃ ነው። እነሱ እራሳቸው አጥንፊና ጠፊ ሆኖው ዓይናችን ምን ሊይ እንደሚችል መጠበቅ ነው።

የትናንቱ ያ ስቃይ ያ መከራ ሻሸመኔ ላይ የተፈጠረው ጭካኔ የትም ቦታ እና በዬትም ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ይገመታል።

ኦሮምያ እያንዳንዱ ቀጠና የራሱ ንጉሥ አለው። የራሱ መሪ አለው። የራሱ ሙሴ አለው። ስለዚህም ያላለቀው ጦርነት የሚጀመረው እዛው ኦሮምያ ላይ ነው …. ተፋጠዋል … የ ኦሮሞ ንጉሳውያን ቤሰቦች። ሌሎችም እኛስ ብለዋል ደግሞ …
  
ኢትዮጵውያን ማመን ካለባቸው የአብይን ንጹህ መንፈስ ነው። መታመን ካለባቸውም ለአብይ ሌጋሲ ነው እንደ እኔ። ምክንያቱም አብይን አገለብጠን አይተነዋል። ፈትሸነዋል። አጀንዳው ሰው ነውአጀንዳው ኢትዮጵያዊነትን ማስቀጠል ነው። እንዲቀጥል የሚፈለገው ዛሬ ደግሞ ኦነጋውያንን ነው። በተቀጥላም ሌላም መንፈስ አለ። ያም ቢሆን ጊዚያዊ ቅልቅል ነው።

አሁን አብይ ነፃ ነው በሙሉ አቅሙ እንዲሠራ ተፈቅዶለታ ማለት ግን አልችልም። አሁን እኔ ያዬሁት ህልም ወንበሩ ባዶ እንደሆነ ነው። ስለዚህ ተወቃሽም ተነቃሽም ሊሆን በፍጹም አይችልም።

ይህን ጥሶ ወጥቶ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የአብይን ሌጋሲ እንዲቀጠል አደርጋለሁ ካለ ልጆቹን ማዳን ይችላል። ተለጣፊ የሆኑትን የእሱ አሽከሮችንም ማሰለፍ ይቻልል። ቤንሻጉልን እና አፋር ክልሎችን።  ምክንያቱም አሁን እዬተደረገ ያለው ዘመቻ የበዛው በማን ላይ እንደሆነ እራሱም ያወቀዋል። እራሱ በዬቦታው የጫራቸው እሳቶች ተንቀልቅለው ቤተ መንግሥስት ደርሰዋል። አሁን ኢትዮጵያን እዬመራት ያለው የኦነጋውያን መንፈስ  አራጦ ነው። ፍሬ ነገሩ ይሄው ነው። አብይ ያልተወደደውም ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ስለሚል ነው። ኢትዮጵያ እና ዕሴቷቿ ለእሱ የነፍሱ ጥሪ ናቸው። ይህ ደግሞ ለኦነግውያን ኮሶ ነው እንቆቆ ...

ስለዚህ የስውሩ መንግሥት ቀጣና በዚህች ሰከንድ ኢትዮጵያን ወደዬት ሊወስዳት እንደሚችል መገመት ይቻላል። የሁሉም አትኩሮት ከ4 እግር እንጨቷ ላይ ነው። ለእሷ ነው ይሄ ሁሉ መሟሟት እዬተደረገ ያለው። ሌላው ግን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ጉዳይ ነው። እግዚአብሄር ቢፈቅድ እና ቢወድ ዶር አብይ አህመድ እሰከ ቤተሰቦቻቸው ቤተ መንግሥታቸውን ጥለው ቢወጡ እንዴት መልካም በሆነ ነበር።

ሲደመደም. ---  አሁን እዬሆነ ያለው ነገር በወያኔ ሃርነት አቅም አይደለም፤ ይህ ግልጽ ሆኖ ሊታወቅ ይገባል። የውጭ የኢትዮጵያ ባልታሰብ መንገድ መንጠቅ ብላ መውጣት ያሰጋቸው ጣምራዎች በሚመሯቸው በጀት በለውጥ ሃይሉ በተፈጠሩ አዲስ አንጃዎች ነው።

ወያኔ ሃርነት ትግራይ አቅም እንዲኖረው የተደረገው በህልመኞች ሴራ ነው። ሴራው ውስጥ ደግሞ ሁሉም እራሱን ይመርመር። ማዘናጋቱን ለሌሎች ይሁን እኛን አይቻልም። አሁን አቶ ጃዋር መሃመድ አንድ የመሻገሪያ አጀንዳ አግኝቷል „ሰላማዊ የሆነ የመንግሥት ሽግግር“ ይህቺ ማዘናጊያ የለበጣ ነገር ናት። ቀጥሎም በ እናቴ ክርስቲያን ነኝም አለበት። እራሱን ለጠ/ ሚር ቦታ ማጨቱ የዛሬ አይደለም የቆዬ ነው።

የሆነ ሆኖ የሽግግር መንግሥቱ ያ መፍትሄ አይደለም። እንኳንስ ለሽግግር አንድ ላይ ሁላችሁን ሰብስቦ አስቀምጦ አንድ አጀንዳ አጸድቆ በዛ ለመወያዬት የማትችሉ ስለመሆናችሁ አሳምረን እናውቃለን። 

ጠ/ ሚሩ ሲመጡ እንኳን አንድ ርባና ያለው ወጥ ጥያቄ ማቅረብ አልተቻልም። ጉልበታም የሚባለው፤ አቅም አለው የሚባለው ሁሉ ምን ላይ እንደ ነበረ ታዝበናል። ስለምን ነፃ ሃሳብ በመፈራበት ዲያስፖራ ታስሮ የኖረ ያልደረጀ ሁኔታው ያልነበረው በአንድ ሰሞን አምጦ ምን ሊያመጣ ሲችል ነውና። 

እርግጥ ነው ፈጣሪ በጥበቡ በቃችሁ ብሎ ፍጹም ቅን፤ ሰው አማኝ ለሁሉም ምቹ የሆነ ሙሴ ሰጥቶን ነበር እሱንም እድሜ ለአፍንጋጮች አሳልፈው ሊሰጡት ጥቂት ደቂቃዎች ነው የሚቀሩት።

ሲጠቃለል ግንቦት 7 አሁን ካለው ሰውር በለውጥ ሃይሉ ውስጥ ከተፈጠረው አፍንጋጭ አንጃ ጋር ግንኙነት ካለው እና አቶ ጃዋር መሃመድን በበጀት እዬደገፈ ከሚመራው የውጭ መንግሥት ጋር ግንኙነት ከኖረው አገር ገብቶ የአብይን ሌጋሲ የሚፈታትን ተመሳሳይ ተግባሩን  በይፋ ይቀጥላል። ሁለቱ ሲፎካካሩ ደግሞ እኛ አዲስ ቲያትር እናያለን። 

ከኦነጋውያን ከሚያስተባብረው ሃይል ጋር  ምንም ግንኙነት ከሌላው ግን ኢትዮጵያ ግንቦት 7 አገር ቤት አይገባም። ምክንያቱም እጅግ የከፋው ዕድል ለግንቦት 7 መሪዎች መንትዮሽ መሪዎች ስለሚሆን። አሁን ባለው ሁኔታ ምንም እርግጠኛ የሚያደርግ የለዬት አቅጣጫ የለም እና።

እውነት ለመናገር ለተፎካካሪ ፓርቲዎች ኦነጋውያን ይሁን ወያኔያውን ምቹዎች አይሁኑም። ምቹው ንጹሁ የአብይ ሌጋሲ ብቻ እና ብቻ ነው። እራሱ  ለኦንጋውያን፤ ለወያኔያውን፤ ለግንቦታውያን አስማምቶ አቻችሎ ሊመራው የሚችለው የአብይ ሌጋሲ ብቻ ነበር። በፓርላማ ሁሉ አንገነጣላለን የሚሉትም ወንበር እንደሚኖራቸው እና ሃሳባቸውን አቅርበው መሞገት እንዲችሉ ሥርዓት ሊኖር ይገባል ብለዋል። መገንጠሉ መፍትሄ ከሆነም።

የሆነ ሆኖ አሁን አብይ ሌጋሲው በድርጅት ደረጃ ብቻውን መለመላውን የቆመ ነው። ህዝቡ ደግሞ ነፍሱ ጥፍት እስኪል አብይን ይወዳል። የአብይ መንፈስ ድርጅቱ ዲካ የለሹ ወደ 85 ሚሊዮኑ የሚጠጋው የኢትዮጵያ ህዝብ ነው።

የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን መንፈስ ካጣ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ኦነጋውያን እና ፕሮ ኦነጋውያን አቶ ንጉሱ ጥላሁን ይጨምራል እንግዲህ አሳቸው ክርስቶስ ለስጋው አደላ ሆኖባቸው የትኛውን እንደሚመሩጡ አይታወቅም፤ አቶ ጃዋር መሃመድ አጤያቸው እንደሆነ ግን ተመልክተናል በ እርግጠኝነትም መናገር ይቻላል። ፍቅሩ የቆዬ ነው። የስልክ ግንኙነቱም እንዲሁም። ሃዲዱን የዘረጉት ኦቦ አዲሱ ረጋሳ ናቸው። እነሱም መሸጋገሪያ እንጂ ግራጫማ ሰብዕና ዘመድም ወዳጅም እርቅም ምህረትም ፍቅርም አያውቅም። ብልጭ ድርግም ነው የሚሰጠው ለሁሉም አትኩሮቱ ... 

የህዝብ ማዕበል ከመጣ እስከ አሁን ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጋ ህዝብ ነው የተፈናቀለው፤ የሞቱን ትተን ከዛም የባሳ እና የከፋ ሁኔታ ይፈጠራል አብሶ አዲስ አባባ ከተማ ላይ። አብሶ ሰልፍ በድጋሚ ከተወጣ። ወያኔ ሃርነት ትግራይ አሳታራቂ ልሁን ቢል፤ ለአብይ ለጋሲ ደጋፊ ነኝ ቢል አይፈረድበትም። ኦህዴድ እራሱን ለማጥፋት ታሪኩን ለማጠልሽ ክብሩን ለማዘረፍ እዬሠራ ስለሆነ። ይህን ታሪክ አይደለም ነገ ዛሬ አምልጦታል ኦህዴድ አሁን ያለው መንፈሱ ምቾት የማይሰጣቸው ሚሊዮኖች ናቸው። እምነት ተሰጥቶት ደግሞ ታይቷል ሲፈጠር ተሰጠው አማራ ሰጠው ክዶ 27 ዓመት ቆዬ፤ ድጋሚ ደግሞ ተሰጠው አሁንም መሰሉን ፈጸም። ስለ ስንት ዓላማ የታጨ በ አጭሩ ተጎረዶ ቀረ። አልጸጸትም። ስለምን ቅንነትን የገፋው እራሱ በጸጸት ቋያ ይንገብገብ። 

„ሰው ሆኖ የማይሞት የለም ባለተገባ ጊዜ መግደል ደግሞ ውድቀት ነው። በመግደል ማሸነፍ እንደሌላ አሁንም የሱማሌው ጉዳይ ያመላክታል  አስር ሰው 20 ሰው ብትገልድ እና ብትቀጥል ጸጸት ይዘህ ትቀጥላለህ አንጂ አታሸነፍም።“ ይህ መታመን ሲቃጣል ከቆሰለ ልብ የፈለቀ ቅኔ ነው። ማን ማንን ካደ። 

ኦህዴድ ሙሉ ነው አይደለም ማለት አልችልም ግን አብይን ክዷል። አቶ ንጉሡ ጥላሁንም ሲጀመር ጀምሮ ከመንፈሱ አልነበሩም አኩራፊ ነበሩ፤ ይህ ቢሆን እኔ አይገርመኝን የሚገርመኝ ዶር አንባቸው መኮነን አብይ አህመድን ቢክዱ ነው። ደግሞም አያደርጉትም።
  
በዚህ ማህል ሰፊው የአማራ ህዝብ፤ አክቲቢስት፤ ጋዜጠኛ፤ ተንታኝ በታኝ ድርጅት ይሁን አማራ ከአንግዲህ መናጆ መሆኑን አቆሞ እራሱን መንፈሱን በማጠናከር ላይ መትጋት ይኖርበታል። መሬት ላይ ጥሩ ሥራ እዬተሠራ ነው። አማራ ዘበኛው ተከላካዩ እሱ እራሱ ነው። 

ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን አንዲት ጫሪ ሃሳብ አንስቷል ስለቅማንት ጉዳይ ይህ ለአብይ ሌጋሲ ሰላም ታስቦ ነውን?

"ግጭት በዛስ" እንዲባዝ ይፈልግ አልነበርንም? ሟርት ብቻ አይደለም ሲደመጥ የባጀው? አገር ሰላም ሆኖ እንኳን። አሁንማ ቤተ መንግሥት እራሱ እዬተናጠ ነው። ገዢው መንፈስ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ አይደለም እንዲያውም ሰነበት ላይ ከቆሰሉት እጅግም ከከፋቸው ከጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጋር አብረው ሄዶው ቅዱስን አባታችን ብጹዑ አቡነ መርቀሪዎችስን አይተዋል። ጠይቀዋል። 

„አብሬ ልሂድ“ ማለት በራሱ ስንቶቹ ከድተው በተንሸራተቱ ሰዓት አይዞህም አለንህም ነው። ሌላው ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡን ማትያስ ደግሞ መስቀላቸውን ይዘው ጋርድ ሁነውላቸዋል።  እኔ አሁንም አለቅሳለሁኝ እሱን ሳስብ። አለንህ ከነመስቀላችን እያሉ ነው ብጹዕና አባቶቻችን። ምክንያቱም መከራው ክርስትናንም የሚያካትት ነውና። ቤተክርስትያነት በመቃጣል የታወጀው የግድያ እና የእገታ ዘመቻ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ያቀነባባረው አይደለም። ማንን ፈርቶ? ካደረገው አደባባዩ ላይ የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ እኮ አንድም ቦታ የአብይ ፎቶ አልነበረም። በቃ ግልጽ ባለ መልኩ ነበር ጥርት ያለ አቋሙን ያሳያው።

ለመሆኑ የ አዲስ አባባው የጥድፊያ ያ የድጋፍ ሰልፍ ቅንብር ማነው ያቀነበባረው? ስለምንስ? 

የሆነ ሆኖ የራስ አቅም ብቻ ነው ትምክህት ጉልበት የሚሆነው። በውጪም በአገር ውስጥም አማራ ለመናጆነት እንጂ በህሊናው ውስጥ ስለ አማራ መቆርቆር በሚመለከት ተንሳፋፊ ዕድምታ ነው። ስለሆነም እንደ አባት አደሩ „ሙያ በልብ ይሁን።“   

ለመሆኑ ዶር ለማ መግርሳ የት ናቸው? ከዬትኛስ ወገን ናቸው?  ከአፈንጋጩ የኦህዴድ አንጃ ኦነጋውያን ጋር ወይንስ ከምስኪኑ መንፈሳቸው ልዕልናዬ ክብሬ ጸጋዬ ከሚሏቸው አይተውም ከማያምኗቸው ከተማላው፤ ብቻውን ከቀረው፤ ከንጹሁ አብይ አህመድ ጋር? ግልብጥብጥ ብሏል። 

አንድ ጊዜ በጨርፍታ ጭንቁ ሁለቱ በመንፈስ ከተለያዩ እና ንፋስ ካሰገቡ ነው ብዬ ነበር … ድፍን ያለ ቢሆንም የሚኒያ ጉባኤ ሥነ - ንግግር ሙቀት እና ግፊት፤ የተዋህዶ የሁለት ጊዜው ከጠቅላይ ሚ/ር አብይ አህመድ ጋር የነበረው የዲሲ ጉባኤ እና ዕድምታው … የሚሊኒዬም አዳራሽ የዕርቅ ሁኔታ የቅድስት ተዋህዶ የመንፈስ አንድነት ጉባኤ ላይ የተገኙት እና ያልተገኙት የሁሉም የሃይማኖት ሊሂቃን መንፈስ ውልብሊት አቃምሶናል …

በተጨማሪም የሰሞናቱ የዝጉ የቤተ መንግሥት የእገታ ድርድርና ስንቦቾም … ወይ ጉድ ግን ምንታይቷቸው ይሆን „አገር ለመምራት አቅም የላችሁም ያሉት የውጭዎቹ“ እኛ አቅማችን አቅም አለው እያለን … ለካንስ እዮባዊነት የሁሉም ችግር ነበር።

ኢትዮጵያን የማዳን መፍትሄ ያለው ከአብይ መንፈስ ውስጥ ብቻ ነው!
ዕውን ቀጣይ ትወልድ የሚያስፈልገን ከሆነ ለአብይ ሌጋሲ ቀጣይነት እንትጋ።
የኔዎቹ ኑሩልኝ
መልካም ጊዜም።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።