የነፃነት አርበኛው የህግ ባለሙያው አቶ ታየ ደንደኣ ዕሳቤ እና እውነታው።
ባለፈንጣጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ።
„ወደ እግዚአብሄር ቤት በገባህ ጊዜ እግርህን ጠብቅ፤
ለመስማት መቅረብ ከሰነፎች መሥዕዋት ይበልጣልና፤
እንርሱም ክፉ እንዲያደርጉ አያውቁምና።„
መጽሐፈ መክብብ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ ©ሥላሴ
13.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
ውዶቼ ሊንኩ ከሳተናው ብራና ያገኙሁት ነው።
„ኦህዴድ እና ብአዴን፤ አቅማቸዉን ያባከኑ ታላላቅ ሃይሎች! (ታዬ ደንደኣ)“ ነሃሴ 9, 2018
እንዲህ ይሉናል የነፃነት አርበኛው የህግ ባሙያው አቶ ታየ ደንደኣ …
„የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ቢያንስ 70% ይሆናል። በኢትዮጵያ ፓርላማ ኦህዴድ 190 አባላት አሉት። ብአዴን ደግሞ 150 የሚጠጋ አባላት አሉት። በድምሩ የአማራ እና የኦሮሚያ ተወካዮች 340 አከባቢ ናቸዉ። ይህ በፓርላማዉ እጅግ በጣም ወሳኝ ድምፅ ነወ። ብአዴን እና ኦህዴድ ቢተባበሩ ፓርላማዉ የሚያወጣዉን ህግ መቆጣጠር ይችላሉ። ሁለቱ ድርጅቶች ያልደገፉት ረቂቅ አዋጅ ሊፀድቅ አይችልም። ሁለቱ የፈለጉትን ረቂቅ አዋጅ ደግሞ በአብላጫ ድምፅ ማፅደቅ ይችላሉ። ስለዚህ ለኢትዮጵያ የዴሞኪራሲ መቀጨጭ ተጠያቂ መሆን ያለበት ሌላ አካል ሳይሆን ኦህዴድ እና ብአዴን ናቸዉ። ሁለቱ ሀይሎች ተባብረዉ ለኢትዮጵያ ዴሞኪራሲ እና ልማት ከመሥራት ይልቅ እርስ-በእርስ በመፈራራት አምባገንነት እና ድህነት በኢትዮጵያ ምድር እንድሰነብት አድርጓል“
በጣና ኬኛ ዘመን በአማራ ቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ ከተደረገላቸው የኦሮሙ ሊሂቃን ውስጥ አንዱ ናቸው አቶ ታዬ ደንደኣ። እንግዲህ በዚህ በወያኔ ሃርነት ትግራይ መራሹ ውስጥ ፍዳቸውን ሲከፍሉ ከኖሩት መከረኞች ውስጥ አንዱ ናቸው። በዚህ ጹሁፋቸው ቤታቸው ውስጥ ያለውን ነገር አልዳሰሱትም፤ አልገባቸውም። እሳቸው ሁሉም እንደ እሳቸው መስሏቸዋል። ይመስለኛል፤
ዕጣ ፍንታቸው እንደ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ ዓይነት ነው። ከውስጤ አከብራቸዋለሁኝ። እማከብራቸው ግልጽ ስለሆኑም ጭምር ነው። ስለ ኦነግ ያላቸውን አዎንታዊ አመለካከት ሲገልጹ እንኳን በድፍረት ነው። በሌላ በኩል ስለ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የነበራቸው ጽኑ ዕምነትም ውስጣቸው ዕውነትን እንጂ ሰው ፍለጋ አለመሆኑን አሳይቶኛል።
ለዚህ ነው እኔ ዴሚክራሲ ግንባታ ይበሉት ቀረጻ ይበሉት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/ እግዚአብሄር በሚ/ር ማዕርግ የሚመሩት አካል የነፍሳችን ጉሮሮ ስለሆነ በጠቅላል መዋቅሩ ይቀዬር ብዬ አቤቱታ ሳቀርብ ይመጥናሉ ብዬ ካቀርብኳቸው ወገኔ አንዱ ናቸው።
ይህን ጉዳይ በመጀመሪያው ዘመነ ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው ላይ አቶ ኤርምያስ ለገሰ ተግቶ ሲሳራበት ነበር፤ እርግጥ እሱ ሲል የነበረው ሁለቱም ትተው ይውጡ ነበር። እኔም መልካም ሃሳብ ነው የሚል ዕይታ ነበረኝ።
አሁን ግን ይህን ዕይታ አልደግፈውም። በሁለት ምክንያት፤ አንደኛ ዘግይቷል፤ ሁሉተኛው ያ እርምጃ ቢወሰደም በአንድነት የሁለቱ ድርጅቶች የመንፈስ ጥምረት ይቀጥላል ብዬ አላስብም አሁን ማለቴ ነው። ምክንያቱም ብአዴን 45 ድምጹን ሰጥቶ፤ አቶ ደመቀ መኮነን የጠ/ ሚኒስተርነትን እጩ ተወዳዳሪነታቸውን ሰርዘውም ታዬ እኮ … ሴራ እና ቅናት በዬት ተገፍተው? እንዴትስ እነዚህ እሾኻዊ ስብዕናዎች ተቀብረው? የኢትዮጵያ ፖለቲካ አንከሊስ ነው። ክትባትም የማይገኝለት።
- ያዬነው።
ኦህዴድ ንጉሰ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ሆኖ እኮ ወጥቷል። አራጊ ፈጣሪው ኦህዴድ ነው ዛሬ። ኦህዴድ የሚሊዮኖች ድምጽ ፍቅር ስካር አሰከረው እና የእሱን መንፈስ መንበር ላይ ያሰቀመጠውንም፤ ጉልላቱን፤ አንጎሉን በግማሽ ልብ ይሁን፤ በእርቦ ህሊና ይሁን በመን ያሀል ፐርሰንት ሲደግፍ መቆዬቱ አሁን አሁን የሚታዩ ግልጽ ተውኔቶች ያሳጡበታል።
ሌላ ተቀናቃኝ መንፈስ ፈቅዶ እኮ ዝብርቅ ውስጥ ነው ያለው ኦህዴድ። የአብይ ሌጋሲ የገነባውን እዬነሳደው እኮ ነው ያለው በይፋ በ አደባባይ። አዲስ ረግረገማ መከራ ለኢትዮጵያ አጭቶ ላይ እና ታች እያለ ነው እራሱ ኦህዴድ።
ወላድ በድባብ ትሂድ እንጂ በምንም መልኩ ደግሞ ጥቃትን የማይቀበሉ ኢትዮጵውያን ደግሞ ስለተሸፈነ፤ በሚስጢር ስለተያዘ ነው እንጂ ግልጽ ባለ ቋንቋ ቢወጣ ጥቃቱን የሚመክት አቅም ኢትዮጵያ አታጣም ነበር።
እኛ ቅንነታችን ፍቅራችን ጊዜያችን ሁለመናችን ለመልካምነት መስጠታችን የሚጸጽተን አይደለም። ኦህዴድ አሸናፊ ሆኖ እንዲወጣ መትጋታችን ከጸጸት ይታደገናል እንጂ ጸጸት የሚተክልብን ፈጽሞ አይሆንም። ከኦህዴድ ውስጥም እናት አገሬ እትዮጵያ የሚሉ እንደሉ አስባለሁኝ። ግን ተድጠዋል ወይንም ተጨፍልቀዋል። ስለሆነም ፍቅራችን በገፍ ብንለግስ ከመልካምነት ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለውም እና። እርግጥ ነው እግዚአብሄር ደግ አምላክ ነው ሳይገነግን ችግሩ ገና በጥዋቱ ምልክቶችን እያሳዬን ነው።
ዛሬ ሚሊዮኖች ልባቸውን ህሊናቸውን የሰጡት ኦህዴድ ይህን ዕድል በምን ሁኔታ እዬተጠቀመበት ነው ቢባል ይሄ የአደባባይ ሚስጢር እኮ ነው። ኦነጋውያን አሸንፎናል ወይንም አብረን አሸንፈናል እያለን እኮ ነው ኦህዴድ።
ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ተወዳጅነት ዛሩን ያስነሳዋል። አበሾው እኮው ፍቅር በፍቅር ረበብበልን ነው። አማራብህ ሲባል ኦህዴድ የበለጠ አምሮ እና ተውቦ መቅርብ ሲገባ አሁን ያለውን ነገር በስውሩም በግልጽም የሚገርሙ ነገሮች ናቸው። „አውቀች አወቀች ቢሏት የቄስ ሚስት መጽሐፍ አጠበች ነው የሆነው።“ አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ገዢው ሃሳብ የኦነጋውያን ሆኗል። ቀደም ባለው ጊዜ ኦህዴድን ተቀበሉ ነበር፤ አሁን ደግሞ እኛ ወደ ኦነግውያን ተቀይረናል እና ተሸከሙን ነው። ትክሻችን ዝሏል ... አንችልም ...
ዛሬ ላይ ብአዴን እና ኦህዴድ የተሰማሙበት የምርጫ ውጤት ወደዬት እያመራ እንደሆነ አሰተርጓሚ አይስፍልገንም። ስለሆነም ከ ኢህአዴግ አባል ድርጅነት ቢወጡም ይኸው መከሰቱ አይቀሬ ነበር።
የቀረው ባህርዳር ላይ የኦንግን የፖለቲካ ድርጅቱን ዓርማ ማውለብለብ ነው። መፍትሄ እኮ የአማራ ተጋድሎ እራሱ ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ሳይሆን ከጃውርያን ተብሎ ከፍ እና ዝቅ ሲባልለት ተሰነብብቷል። አሁን ደግሞ የሲዳማ ጉዳይን ፈቹ ጃዋርውያን መንፈስ ሆኗል።
የቀረው ባህርዳር ላይ የኦንግን የፖለቲካ ድርጅቱን ዓርማ ማውለብለብ ነው። መፍትሄ እኮ የአማራ ተጋድሎ እራሱ ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ መንግሥት ሳይሆን ከጃውርያን ተብሎ ከፍ እና ዝቅ ሲባልለት ተሰነብብቷል። አሁን ደግሞ የሲዳማ ጉዳይን ፈቹ ጃዋርውያን መንፈስ ሆኗል።
ስለዚህ በዚኸም ይሁን በዚያኛው ወርቁን አቅልጦ ያፈሰሰው ኦህዴድ ነው። ከዚህ በላይ ምን ይሰጣው፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ በእኛ ዕድሜ ማለት ነው ይህን ያህል የዓለም አቀፍ የሚዲያ ሽፋን አግኝታ አታውቅም፤ በሰባዕዊ መብት አያያዝም በተባባሩት መንግስታት የሰብዕዊ መብት አስከባሪው ጽ/ ቤት ሳይቀር ለናሙና ቀርባላች ከ43 ዓምት በኋዋላ።
የሃያላን ምንግሥታት ክፍለ አካል የሆነችው ፈረንሳይ ቀጥተኛ ግብዣ አቅርባለች፤ የተባባሩት መንግስስታት ስብሰባ ላይ ኦህዴድ ንግግር እንዲያደርግ ጥያቄ ቀርቦለታል። ኦህዲድ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ድርጅት የሰላም የኖቤል ተሸላሚ እንዲሆን ፕሮፖዛል ቀርቧል።
መንትዮሹ ጠ/ ሚኒስትራት ከቁመታቸው ልክ ከአስረሁለቱ አካላቸው በላይ የጸጋ ስግደት እዬተሰገደላቸው ነው። አርቲስት አቶ ታማኝ በዬነ እኮ የጸጋ ስግደት ሰገደ። መቼም ለእሱ ኢትዮጵያዊነት ሰሃ ስለማይወጣለት እሱ ከነዙፋኑ ሰገደ ሲባል ኢትዮጵያ አፈር ቅማ ፍግም ብላ ሰገደች መለት ነው። እሱ ለዬትኛው ድርጀት ለዬትኛው ሊሂቅ እንዲህ ሲያደርግ ታይቶ ይተዋቃል። ለ እሱ ነው ሲሰገደለት እኔ ያዬሁት እኔው ባለደርገውም። እኔም አንዷ ሞገደኛ እቴጌ ነኝ እና ...
አሜሪካን አገር ታይቶም፤ ተሰምቶም፤ ተደምጦም በማይታወቅ ሁኔታ፤ ከዬትኛው ፕላኔት እንደሆን ግራ እስኪገባን ድርስ ያን ያህል ፍቅር እረበበ። አገር ወስጥም መሰሉ ተከወነ። ይህ እንግዲህ በሦስት ወር ውስጥ ነው። በዚህ ሁሉ ሂደት ግን ለዚህ ያበቃን የአማራ ተጋድሎ ነው አልተባለም። ቄሮ ነው የነገሠው። የቄሮ መሪ ደግሞ አጤው ጃዋር መሃመድ ናቸው።
ያ ሁሉ ፍቅር ከሊቅ አስከደቂቅ ከፖለቲካ ሙህር እስከ የኔቢጤው ያልተማረ የሰጠው ፍቅር አክብሮትን ደግሞ አቤቱ ኦህዴድ ይህን ጥሶ ደግሞ አዲስ ሰው ይዞ ቀርቧል ኦህዴድ አቶ ጃዋር መሃመድ እና ፕ/ ህዝቃኤልን። አንግሶ ዙፋኑን አስርክቧል።
ይህም ላይበቃው እኛ አማናውቃቸው ይመስል እነሱን ደግሞ አንግሱልኝ ብሎ በሠረጋላ ነጋሪ እያስጎሰመ ጫን ተደል የሆኑ ክብሮችን እዬደረደረ ሚዲያው ሁሉ እንዲያረግርግ እዬተደረገ ነው። የዛሬ ዜና አንባቢ ደልደል ያለ ነው ብዙ ጊዜ ፈገግ ብሎ ነው የሚጀመርው፤ ዛሬ ግን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እንዴት ስልችት እና ችክ እንዳለው በዚህ ማዬት ይቻላል።
ይህን አንባቢውን ተመልከቱት እንዴት እንደተሰላቼ በዚህ አቅጣጫውን በሳተው ዘገባ ይሁን የለበጣ ግብግብ፤ በእዬለቱ ገቡ ነው ተፎከካሪዎችም፤ ልባቸውን ይሆን ህሊናቸውን ይሆን ክፋታቸውን ይሆን ምን ይዘው እንደሚገቡ እና ምን አዬሠሩ እንደሆነም አይታወቅም። ገብተው እስኪያበቁ እዬተጠበቀ ይሆን? ቀጣዩስ ምን ሊሆን እንደሚችል አያታወቅም።
Ethiopia: ኦብነግ ትጥቁን ፈቶ አዲስ አበባ ገባ !!
የገለማ ነገር ነው ያለው። የሰለቼ ነገር ነው ያለው።
በአዲስ ጃኬት ኦህዴድ እና የብአዴኑ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በጣማራ ምን እዬሠሩ እንዳሉ ጠንቋይ ቤት መሄድ አያስፈልገንም። ስለሆነም ለአንድ ውሳኔ ጥምረቱ ቢኖርም በቀጣይነት ጸንቱ መዝለቅ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ አንከሊሱ ነው።
ኦህዴድዶች አላወቁበትም፤ ስለዚህ እያመለጣ ነው። ከእንግዲህ እንኳንስ ኦነጋውያን የምዕት ቅኔ ያልናቸው ዶር ለማ መግርሳ እንኳን ዳግም ቢነሱ ልብ ለልብ የሚታሰብ አይደለም። ምክንያቱም ብዙ ነገር ታዘብን። ብዙ ነገር አዬን። መንፈሳችንም ባልተወለደ አንጀታቸው ቀጠቀጡት።
የኢትዮጵያ ህዝብ የመሞከሪያ ጣቢያ ነውና አዲሶቹን ሹመኞች የፌስ ቡክ አርበኞች ደግሞ አዝሎ ሆነ አሸክኮ አድርጎ ይንገራገጭ። ቅንነት ለነጠፈበት መንፈስ ፍቅር ቀድሞ ነገር አለርጅኩ ነው።
መጀመሪያ ኦህዴድ ለራሱ መንፈስ፤ ለዛ ንጹህ፤ ሰርቶ የማይደክም፤ ፍጹም ቅን መንፈስ ለአብይ አህመድ ነፍስ ይጨነቀው? እንዲህ እንደባይተዋር ከሚያው።
ያ ሁሉ ማዕት ሲወርድበት እንኳን ወጥቶ የሞገተለት የለም ከአቶ ካሳሁን ጎፌ በስተቀር። የሆነ ሆኖ አሁን እሳቱ እዛው እራሱ ውስጥ ነዶ እራሱ ጭነቅላቱ ላይ ይነዳል። ከእንግዲህ ግን አማራ በዝርግ ይሁን በጠፍጣፋ፤ በሞላላ ይሁን በሰርታቴ ስሌት የሚያረገርግበት አንዳችም ነገር የለም። ወትሮውን ኢትዮጵያ ስለተባለ ነው።
ያው ቀሪው ጊዜ የኦነጋውያን መዝሙሩ ዓርማውም ቋንቋውም ብሄራዊ ሆኖ ማዬትን እንጠብቃለን። በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አመራሮችን ይጠበቃል። ዘመነ ኦነጋውያን ዕውጃውን ሆነ ነጋሪት ጉሳማውን ከሚኒያ እሰከ ሚሊዬነም አዳራሽ አይተናል። አስተውለናል።
ከዚህም በላይ ግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ፤ ሁለት እና ሦስትን ከውኖ አራተኛውን ፕሮጀክት በነዲድ እዬተቃጠለ እንደተቃጠለ ደመ ከልብ ሆኖ የቀረው የአቤል ድምጽ አሁንም ይጮሓል፤ በተራው ደግሞ ባለተራው ተራውን ይጠብቅ … ይሄው ነው። ምን አልባት ዶር አንባቸው መኮነን …
የኔዎቹ አንድ ነገር ግን ቅኖች በሁሉሙ ቦታ አሉ። ደጎች በሁሉም ቦታ አሉ። እግዚአብሄር ፈቅዶ አዲስ የቅንነት ጋላሪ በጥበቡ ተሠርቶልን ነበር፤ ግን „ነቅናቂ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣል“ ሆነና እና የሚታዬው ተከሰተ። ኮሰኮሳቸው ያ መንፈስ በሁለገብ አቅሙ ለግለግ ብሎ ሲወጣ ኢትዮጵያን አፍሪካን ሊታደግ ሲማስን በሸታቸው ሆነ።
ለመሆኑ ዶር ለማ መግርሳ የት ናቸው? በምንስ ሁኔታ ይገኛሉ? ከተቀለበሰው ወይንስ ሊቀለበስ ከታሰበው ወይንስ እያቆጠቆጣ ካለው መንፈስ ከዬትኛው ይሆኑ?
ለኦሮሞ የፖለቲካ ድርጅት በእኔ ዕድሜ እንዲህ የተነጠፈለትን የተጎዘጎዘለትን እንዲህ ሸር ጉድ የተባለለትን ጊዜ አይቼ አላውቅም። ወርቅ ከቀለጠ ይፈሳል።
ግን ጅማዎች የት ናችሁ? ትንሽ አይነሽጣችሁምን? ወኔ የላችሁንም? ጥቃት አይሰማችሁንም? በዬዘመኑ እንዲህ የሰማይ ሽልማታችሁ የፈተና መሞከሪያ ጣቢያ ሲሆን እንዲያው ዝም? ከአብይ ሌጋሲ ጎን ለመቆም ስለምን አቃታችሁ? ለነገሩ ተመረጠ ብላችሁ እኮ ደስታችሁን ለመግለጽ አልተፈቀዳለችሁም ተወቅታችዋኋል።
ግን ዜጋ ናችሁ እና ድምጻችሁን አሰሙ። አቅምን አምጣችሁ ውለዱ? ኢትዮጵያም የእናንተ ናትና!የ እናንተን መንፈስ የሁላችንም ነው። እኛም በ እናንተ መንፈስ ነን። ጭንቃችን ጭንቃችሁ ቢሆን ምርጫዬ ነው። ቢያንስ ጸሎት።
- · ይከወን።
ሥጦታውን ያላወቀ ተቀባይ ምርቃቱ መነሳቱ አይቀሬ ነው። የ ኦህዴድ መርቃት ተነስቷል ብዬ አስባለሁኝ።
ምን ልለዎት ነበር? እጅግ የማከብረዎት የነፃነት አርበኛ አቶ ታዬ እያመለጠ ያለ ነገር አለ፤ የሚሊዮን ፍቅር ድምጽ … „ቢከፋኝ ብመለስ“ እንግዲህ የሚኖር አይመስለኝም። ታሪክ አንድ ግዜ ነው አይደገምም አይሰለሰም። በጣም ቸኮሉ ለማወጅ። ለቅኖች ግን መልካም ነው። እንኳንም ይህን ቁመው ለማዬት በቁ ባለቅኔው ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ።
ችኮላው ጥድፊያው ፉከራው ቀረርቶው ያለግዜው ነበር። ለዚህም ነው ባለቅኔው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ „ሰው ሆኖ የማይሞት የለም ባለተገባ ጊዜ መግደል ደግሞ ውድቀት ነው። በመግደል ማሸነፍ እንደሌላ አሁንም የሱማሌው ጉዳይ ያመላክታል አስር ሰው 20 ሰው ብትገልድ እና ብትቀጥል ጸጸት ይዘህ ትቀጥላለህ አንጂ አታሸነፍም።“
እስቲ ሞት የማይነካቸው ባለስድስት ክንፋሞች እዬተዘዋወሩ ህዝብ እያነጋገሩ አያደለም? የቀዱትን ከአብይ የተማሩትን ገልብጠው …. ሞትም ትውር ሳይልባቸው የቅዱስ ሄኖክን ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ተቀብለው ዕድሜ ልካቸውን ሲገዙ ይባጁ ህልማቸው ከተሳካላቸው ... ዙሮ ዙሮ ለዛች መከረኛ እናት ነው ...
„ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል!“
የኔዎቼ ክብረቶቼ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ