ትውልዳዊ ድርሻውን #በልቀት ላጠናቀቀ ሰብዕና "#በቃ" ለማለት ዘግይቷል መባል ይችላልን?
ትውልዳዊ ድርሻውን #በልቀት ላጠናቀቀ ሰብዕና " #በቃ " ለማለት ዘግይቷል መባል ይችላልን? "የቤትህ ቅናት በላኝ።" እንዴት ናችሁ ውዶቹ ውቦቹ? ባለፈው ሳምንት አንከር ሚዲያ ከልጅ መስፍን አማን ጋር ውይይት አድርጓል። በእግረ መንገድ ይሁን ታቅዶ የቀድሞ ጠሚር አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ "በቃ" ለማለት ዘግይተዋል የሚል ጭብጥ ከጋዜጠኛ መሳይ መኮነን አዳመጥኩኝ። ከሳቸው በላይ የቀደመ በራስ ላይ የወሰነ እስኪ አንድ ሰው በዘመናችን ይነገረን ልጅ መሳይ መኮነን። ለመሆኑ አብይዝም ሥልጣኑ ህጋዊ ይሆን ዘንድ የምርጫውን መንፈስ ያገዘ ማን ይሆን? ቁልፋ ጉዳይ እኮ ይህ ነው። እኔ ከርዮት ቴዲ ሚዲያ ውጪ በሙሉ የኢትዮጵያ ሚዲያወች ቀን ከሌት ነበር የደከሙት ምርጫው እንዲሳካ። ያ ትልቁ " #የመደመር " ስኬት ነበር። በዚህ አግባብ ማን ያልዘገዬ ኖሮ ነውና ትውልዳዊ ድርሻቸውን በልቅና የተወጡ ተምሳሌት ሰብዕና ያላቸው አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በመዝግዬት ሊጠዬቁ፤ ሊወቀሱ የሚችሉት? ጎንደሮች ባለ ቅኔ ናቸው እና ሥራ ያጣ መነኩሴ የሚሉት አይነት ነው የሆነብኝ። እሳቸው እኮ ድርሻቸውን በብቃት የተወጡ #ጀግና ናቸው። ሥልጣናቸውን ፈቅደው እና ወደው እንዳሻችሁ አድርጉት ብለው የፈቀዱ፤ ህዝብ እንዲፀልይላቸው የጠዬቁ #ትሁት መሪ ናቸው። ለፓልቶክ #አድሚነት ጠበንጃ በሚያማዝዝ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የአንድ አገር መሪነትን ተረከቡ ያሉ፤ #ጤናማ መንፈስ ያላቸው ልዩ ሰው ናቸው እኮ። ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ ለለማውም፤ ለጠፋውም ምስጋናም ይሁን ተጠያቂነት ሁሉ ሲጠዬቅ ይጠየቁበት። አንከር በሆነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግን ፍፁም ልዩ የሆነ #በራስ መተማመን ላይ የተገነባ፤ #ስስ...