ልጥፎች

ከኤፕሪል 4, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዴሞክራሲን ስትታገልለት እና ስትታገለው አስተውለው። ቃሉ ብቻውን ግብ አይሸልምም እና።

ምስል
  ዴሞክራሲን ስትታገልለት እና ስትታገለው አስተውለው። ቃሉ ብቻውን ግብ አይሸልምም እና።     ይድረስ ለአጤ ቅንነት ቡናችን ፋት እያልን እኛ እኛኑ ይፈታትሸው። ዬውስጥ ቤተመቅደሶቼ እንዴት አላችሁልኝ?? ዬርህርህናችሁ መጠን ቁሞ አስተማረኝ። ውስጣችሁን አሳዬኝ። ቤተ ሰለሞን የጨመተ ለእንባ፤ ለእውነት፤ ለፍቅር፤ ለሞራል፤ ለእሴት የሚሞግት በጨዋነት ዬአብርኃሙ ቤት ነው። የጥበብ ሰወች፤ ሞጋቾች፤ የሲዊዝ ፖለቲከኞ በቀለም የማይገናኙን የሁሉም እምነት፤፦ዬሁሉም ፖለቲካ አቋም አራማጆች ጠንካራ ሚዲያወች ሁሉም ከሊቅ እስከ ደቂቅ በቤታችን ይገኛሉ። እርግጥ ነው ሰብሰብ ብለን በተን ዬሚያደርጉን ተለዋዋጭ የፖለቲካ ቁመናወች እና የኃይል አሰላለፎች ቢኖሩም ዙረን የምንገናኝበት እሸቱ፤ ጎልማሳው አዛውንቱ፤ ሩህሩሁ ኢትዮጵያዊነት ነው። ሰብላቢያችን እሱ ነው። መሪያችን ቅንነት። ከሰሞኑ የአንዲት እናት ፎቶ ሼር አድርጌ ሼር የተደረገው ወደ ሁለት ሺህ ሊጠጋ ነው። በእኔ ልፋት ሪከርድ ሰባሪ ነው። በፁሁፌ ውስጥ ቃለ ህይወትን እጠቀማለሁ ፕሮፋይሌ የፃድቁ አባቴ ብፁዑ ሐዋርያ የቅዱስ መርቀርዮስ ነው። የሁሉም ዕምነት ተከታዮች፤ የማያምኑትም ሳይቀሩ ደስ ብሏቸው የህሊናዬ ምርት ታዳሚወች ናቸው ከዚህ በላይ ዘመንን ቁሞ ያሰተማረ አብሮነት ዬለም። አብረን እንደ ተፈጠር አብረን መሆናችን አሻራው ይህ ነው። ክፍት ሲለኝ በዝምታ የቤታችን ወገኖቼ ጋር አክብሬ መራራ ስንብት ሳደርግ እንኳን ሥም ቀይረው መጥተው ወደ ቤታቸው ይመለሳሉ። ቤታችን የፈቀዱ፤ ዬወደዱ አዲሶች ውዶቻችን ደግሞ ስለሚሞላባቸው ዬቤታችን አባላት ፈቅደው እስኪለቁ መጠበቅ ግድ ስለሚሆንባቸው በጓዳ መጥተው ይጠይቁኛል። ታግሰው ቤተኛ ይሆናል። ጥሪዬ ዬትውልድ ነው። ትውልድ መገንባት ያለበት ፈርሶ በሚ...

ኢትዮጵያ ቲያትር ቤት አይደለችም። ይድረስ ለማከብርሽ እህቴ ለአርቲስት አስቴር በዳኔ።

  ኢትዮጵያ ቲያትር ቤት አይደለችም። ይድረስ ለማከብርሽ እህቴ ለአርቲስት አስቴር በዳኔ። አዲስ አበባ። ዘለግ ያለ ሙግት ነው። https://www.youtube.com/watch?v=EVkviBf3j_s "ክርስትያን ታደለ ጅል ነው" | አስቴር በዳኔ ምን እያለች ነው? "| ዶ/ር አብይ እና ስልጣን | Haleta Tv "በንጉሱ ቤት ዬነበረው ጃንደረባኢትዮጵውያዊው አቤመሌክ ኤርምያስን በጉድጓዱ ውስጥ እንደ አኖሩት ሰማ።" (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፯)   #ጠብታ ። አስትሽ እንዴት አለሽልኝ? እንዴት ነው የዬካቲቱ ትንቢትሽ ሠመረ? ጓዘ ቀላል ጥያቄ ነው። በሕይወቴ እማልፈልገው ነገር ሴቶችን መሞገት ነው። ሁለት ፍሬ መድረክ ላይ ወጥታችሁ እናንተን መንካት ሃጢያትም ወንጀልም መስሎ ስለሚታዬኝ እጅግ ተቆጥቤ በራሴ ላይም ዲስክርምኔሽን ፈጽሜ እኖራለሁኝ። ፈቅጄው ማለት ነው። ይህን ቃለ ምልልስሽን ሳዳምጠው ግን ያ እናትነት፤ ለብሄራዊ ሰንደቅሽ ተቆርቋሪነት፤ ለአገር የአሳቢነትሽ በትረ አምድ ተተረተረብኝ። አልደብቅሽም አስደንግጠሽኛል። ለመፃፍ ከራሴ ጋር ስሟገት ውዬ አደረኩኝ። አሁን ግን ወሰንኩኝ። እና ዕይታዬን ረድፍ በረድፍ ደርዝ በደርዝ ላቀርብልሽ ወደድኩኝ። በሰጠሽው አስተያዬት ላይ ያልተገቡ ትልልፎችን አይቼ አዝኛለሁኝ። የትውልድ ያልሆነ ጠባሳ አይቻለሁኝ። ለምን ብዬ እራሴን ስጠይቅ የአገላለጽሽ ባህሬ ስላቅ እና የመመፃደቅ ዓይነት ስለሆነ ነው። አሾፍሽ - አፌዝሽም። አስቱዬ የማከብርሽ እህትዬ ያ እንደ አለፈው ይህም ያልፋል። ተስፋችን እንደ አንቺ የፋንታዚ ልዑል፤ የዲስኩር አጤ ሳይሆን ሰማይ እና ምድርን በቃሉ ፈጥሮ ያፀና አባት መዳህኒዓለም ክርስቶስ አለን። እነሱ ከበደሉን በላይ ያንቺ መዶሻ ይበልጥ ውስጤን ጎዳው። ...

ለመላከ ሞት ሚስጢርን በገፍ መመገብ ዕቀባ ሊደረግበት ይገባል። ሚስጢር ላልተገባው እርኩሰት መግለጥ የመላእከ ሞት መንገድ። በሁዳዴ በስጋ መረቅ ላበደ መንፈስ ቤተመቅደስንቧ አድርጎ መክፈትስምየለሹ የገመና ረግረግ።

ምስል
  ለመላከ ሞት ሚስጢርን በገፍ መመገብ ዕቀባ ሊደረግበት ይገባል። ሚስጢር ላልተገባው እርኩሰት መግለጥ የመላእከ ሞት መንገድ። በሁዳዴ በስጋ መረቅ ላበደ መንፈስ ቤተመቅደስንቧ አድርጎ መክፈትስምየለሹ የገመና ረግረግ። "አንተስ ብትሰማኝ ሌላ አምላክ አይሆንልህም፤ ለሌላ አምላክም አትስገድ" (መዝሙር ፹ ቁጥር ፱)   እዛው ላይ ደርቀው ይቀራሉ ብዬ አስቤ ነበር። ድፍረታቸውን ከውስጤ መረመርኩት እና መሃከነ አልኩኝ። መጀመሪያ ሳዬው ግን ደነገጥኩኝ። በሌላ በኩል ድቁና ለአሳትያን ሲሰጥ እና እንዲህ ሲወራኝበት በቤተ መቅደስ ዝምታ ምራኝ ሲባል ምንኛ አላዛሯ ኢትዮጵያ ቀራንዮ ዕለቷ፦ ጎለጎታ ማዕልቷ እንደሆነ አስተዋልኩት። በቅድሚያ ከ7 ጊዜ በላይ ጎንደር የተገኙት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ የሱማሌን መሪ፤ የኤርትራን መሪ ይዘው ጎንደር ሄደው ነበሩ። ያን ጊዜ አገር አቋርጠው ቱሪስቶች ዬሚዩት ዬዓለም ቅርስ እና ውርስ ሳይሆን ጉዳያቸው ሰው ሰራሽ ግድብ ነበር። ለዛውም በደርግ ጊዜ የተወጠነ ፕሮጀክትን አሳይተው ተመለሱ። እሳቸውም ከባለቤታቸው ጋር ሆነ በተናጠል በሚያደርጉት የወረራ ጉብኝት አንድም ቀን ትዝ ብሏቸው ስለማያውቅ አበክሬ እወቅሳቸው ነበር። የሚገርመው ዬጎንደር ከንቲባ መልካም ነገር አደረጉ ተብሎ ዜና ካዳመጡ ሳምንት ሳይሞላ ከሃላፊነታቸው ይነሳሉ። ጎንደር #ኩሽናቸው ። አንዱ ከንቲባ ለመጀመሪያ ሰው ተገኜ ሲባል ጎንደሬን ለማፍዘዝ ስሜን አሜሪካ ተልከው እዛው እያሉ ነበር ከሥልጣናቸው ተነስተው ከአዲስ አበባ ሰው ተልኮ ካለ ደሞዝ ከንቲባ እንዲሆኑ አንድ ነፍስ ዬተመደቡት። ሃይማኖቱን ተከድኖ ይንተክተክ። ሁለገብ ምንጠራ ሁለገብ ነቀላ በቱሪዝም፤ በባህል ዘርፍ በከተሞች ፖለቲካ። ልክ አዲስ አበባ ከተማ እንደሚጫወቱት ገበጣ ጎንደር ላይም ይከወ...