ኢትዮጵያ ቲያትር ቤት አይደለችም። ይድረስ ለማከብርሽ እህቴ ለአርቲስት አስቴር በዳኔ።

 

ኢትዮጵያ ቲያትር ቤት አይደለችም።
ይድረስ ለማከብርሽ እህቴ ለአርቲስት አስቴር በዳኔ።
አዲስ አበባ።
ዘለግ ያለ ሙግት ነው።
"ክርስትያን ታደለ ጅል ነው" | አስቴር በዳኔ ምን እያለች ነው? "| ዶ/ር አብይ እና ስልጣን | Haleta Tv
"በንጉሱ ቤት ዬነበረው ጃንደረባኢትዮጵውያዊው አቤመሌክ
ኤርምያስን በጉድጓዱ ውስጥ እንደ አኖሩት ሰማ።"
(ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፯)
 
አስትሽ እንዴት አለሽልኝ? እንዴት ነው የዬካቲቱ ትንቢትሽ ሠመረ? ጓዘ ቀላል ጥያቄ ነው። በሕይወቴ እማልፈልገው ነገር ሴቶችን መሞገት ነው። ሁለት ፍሬ መድረክ ላይ ወጥታችሁ እናንተን መንካት ሃጢያትም ወንጀልም መስሎ ስለሚታዬኝ እጅግ ተቆጥቤ በራሴ ላይም ዲስክርምኔሽን ፈጽሜ እኖራለሁኝ። ፈቅጄው ማለት ነው።
ይህን ቃለ ምልልስሽን ሳዳምጠው ግን ያ እናትነት፤ ለብሄራዊ ሰንደቅሽ ተቆርቋሪነት፤ ለአገር የአሳቢነትሽ በትረ አምድ ተተረተረብኝ። አልደብቅሽም አስደንግጠሽኛል። ለመፃፍ ከራሴ ጋር ስሟገት ውዬ አደረኩኝ። አሁን ግን ወሰንኩኝ። እና ዕይታዬን ረድፍ በረድፍ ደርዝ በደርዝ ላቀርብልሽ ወደድኩኝ።
በሰጠሽው አስተያዬት ላይ ያልተገቡ ትልልፎችን አይቼ አዝኛለሁኝ። የትውልድ ያልሆነ ጠባሳ አይቻለሁኝ። ለምን ብዬ እራሴን ስጠይቅ የአገላለጽሽ ባህሬ ስላቅ እና የመመፃደቅ ዓይነት ስለሆነ ነው። አሾፍሽ - አፌዝሽም። አስቱዬ የማከብርሽ እህትዬ ያ እንደ አለፈው ይህም ያልፋል። ተስፋችን እንደ አንቺ የፋንታዚ ልዑል፤ የዲስኩር አጤ ሳይሆን ሰማይ እና ምድርን በቃሉ ፈጥሮ ያፀና አባት መዳህኒዓለም ክርስቶስ አለን። እነሱ ከበደሉን በላይ ያንቺ መዶሻ ይበልጥ ውስጤን ጎዳው።
ኢትዮጵያ ቲያትር ቤት አይደለችም። ኢትዮጵያ የኮሚኮች ሙዚቃ በባንድ የሚጨፍሩባት ኦኬስተር አይደለችም። ኢትዮጵያ ሳይንስ፤ ኢትዮጵያ ፍልስፍና፤ ኢትዮጵያ ቫወል፤ ኢትዮጵያ ዩንቨርስ፤ ኢትዮጵያ ሐዋርያም ናት። እናትን አሻቅበሽ ያዬሽበት መንገድ ያቆስላል። አብዝተሽ ሳቅሽ። አብዝተሽ ተሳለቅሽ። አብዝተሽ ተመፃደቅሽ። አብዝተሽ ማንም እና ምንም ለዕንባ ዋናተኞች እንደለለ እንደ ዳንቴል ልብሽን ቧ አድርገሽ ተርትረሽ አሳዬሽን። እግዚኦታ። እናትነትሽ? የጥበብ ትጋትሽ? ወደዬት መጪ አሉ ወይንስ ወደምን አረጉ? እናትነት ሚስጢር ነው።
1) ስልጣኑ እንዴት እንደተገኜ?
1.1 በበሰበሰው ኢህአዲግ ውስጥ ከዛ ለሚወጣ ኃይል ማን ዕውቅና ሊያሰጠው ቻለ ብለሽ ጠይቂ፤ ባለሙያ ነሽ አይደል ዬፖለቲካ? ለነገሩ ዬሳይንቲስቱም ፕ/ መራራ ጉዲና ሙያው እና ዲስፕሊኑ ዳጥ እና ምጥ ላይ ነው። ስለሆነም በአንቺ አያስፈርድም እንደማለት።
1.2) ህወሃት ሥልጣን ላይ እያለ ማህበራዊ መሠረቱ በአውሮፓም፤ በምዕራባውያኑም እንዴት ተናጋ? እንደምንስ ተነቀለ? በቅንድብ ፀጉሩ በኦነግ ፖለቲካ ጥረት ስኬት ሆነ ብለሽ ውሽክ እንዳታሰኝኝ። ያለውን ዬህወሃት አቅም ከሥልጣን ወርዶ ተመድን 15 ጊዜ ብድግ ቁጭ እንዳደረገ፤ አሁንም ቅንጣት ግዴታውን ሳይወጣ ከጠበቀው በላይ የመብት ጉርሻ በወረፋ ተሰልፎ ለጥ ሰጥ ብሎ ሰግዶለት፤ አደግድጎለትም በግርማ ሞገስ ላይ እንደ አለ አንቺም ስንቅ አገልግል ለመሪሽ ዘመቻ ወገብሽን ታጥቀሽ ዬተሰለፍሽበት የኤሊኮፕተር ዘመቻ ጣሪያውም፤ ግድግዳውም በምን ተቋጭቶ እያደገደጋችሁ ነው ለወያኔ፤ "አፍንጫቸውን ተይዘው" እንዳሏችሁ እኛም በትዝብት እንከታተል ዬነበርነውንም ያለውንም እያዬን ነው። የቀን #ኮቸሮ፤ የዘመን #ሙጃ ዬለውም እና። ዬአስተሳሰብ ግን ግሽፈትም፥ ምግለትም ቁስለትም፦ መኩረፍረፍም አለ። እንደ ኩርፍርፋ "መደመራችሁ" ቃሉን የሌብነት ያህል እጠዬፈዋለሁኝ።
1.3) ጠቅላይ ሚር አብይን ዓለም በምን ሙድ ተቀበላቸው? ጀርመን ላይ ዬነበራቸው አቀባበል ምን ይመስል ነበር? ለማያውቁት ሰብዕና ጀርመኖች ያን ያህል ክብር እና ማዕረግ እንደምን ሊሰጡ ቻሉ? የኦስትራሹ ጠቅላይ ሚር እንደምን ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ቻሉ? ጀርመንም ላይ ተገኝተው አብረው መምከራቸው በምን እንዴት ሊሆን ቻለ?።በምን የጭብጥ በዬትኛው ዬኢህአዴግ የክስ የመነሳት አፕሮባል??? ማለቴ በህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የማያዳግም ክርክም ያለ መረቅ እና ጠፈፍ ያለ ተግባር ተከውኖ ስለነበር። ዬማታውቂውን ስኩን፤ ጭብጥ ሂደት ቢያንስ በዝምታ ብትተባበሪን እንደማለት። ብዙ ተለፍቶበታል። ቲም ገዱ በአፍ ጢሙ ቢከነብለውም። ባዶውን አጨብጭቦ ቢሰናበትም።
1.4 ) ጠቅላይ ሚኒስተርሽ ስለምን 50% ዬሴት ካቢኔ እንዲኖራቸው እንደ ፈለጉም በስሌት መርምሪው። ዱብ ዕዳው ለሌላው ነው። እኔ ግን ሥራዬን አውቀዋለሁኝ። ማንን ለማማለል ዬቅብ አርግዶሽ እንደ ተከወነ።
ስለዚህ ቀደም ብዬ በትህትና እንደ አሳሳብኩሽ፤ በማታውቂው፤ ባልነበርሽበት ዓውደ ምህረት በዝምታ ብትተባበሪን መልካም ይሆናል። በሌላ በኩል የቀድሞው ጠቅላይ ሚር ዬተከበሩ ልበላቸው ዛሬ አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ ልባላቸው ለዶችቬሌ የሰጡትን ቃለ ምልልስ እንግሊዘኛውን ሄደሽ አዳምጭው። ዶር ደብረጽዮንም ተናግረውታል። የአማራ ልጆች አገር ውስጥና ውጭ ባደረጉት ተጋድሎ ብለው።
ሌላ በጥድፊያ ስልጣን ላይ ከወጡም በሰበር እስራኤል የገቡበት ሚስጢር፤ አውሮፓ ህብረትን ጋብዘው ሹፌር የሆኑበትን አመክንዮ፤ በተጨማሪም ለተመድ ጉባኤ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴን ልከው እንደምን በሰብዕናቸው ላይ ጥገና እንደሠሩ በግርፋ እና በግርድፋ ሳይሆን በጥሞና እና በማስተዋል መርምሪው። አንበሳው ኢትዮጵያኒዝም የሚመራው የአማራ መንፈስ ሃሳብ አለው፤ ፋክት አለው፤ መርህ አለው ኮንቢንስ የማድረግ። ብዙ የናረ፤ ዬተለጠጠ፤ ጣሪያ ዬነካ፤ የስላቅ ማሽካካት ገጽሽም፤ አንደበትሽም ላይ አስተውያለሁኝ። ዓለምን የሚመራት የብዕር ጉልበት ነው። የፋንታዚ #ቅርሻ አይደለም።
ወደ ቀደመው እንደ አቨው ምልሰት ሳደርግ ዛሬ የውጭ አገር መንግሥታት ለህወሃት ወደ ሥልጣን መመለስ አጀንዳቸው እንደሆነ ያን ጊዜም የህወሃት ከሥልጣን መወገድ የለትተለት ተግባራቸው ነበር። ያን ነው አለቃሽ፤ ስስት ጭንቅ ጥብብ የምትይላቸው የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ሌ/ኮ አብይ አህመድ አሊ በአፍጢሙ ደፍተው የአማራ ምንጠራ፤ ለተዋህዶ ወጀብ፤ ለስሜን ኢትዮጵያ አሳር፤ ለኢትዮጵያዊነት ነቀላ ላይ የሚጣደፋት። ለመሆኑ ቢቀር ቢቀር እንዴት ለሰንደቅሽ መሆንስ ተሳነሽ? አንድ ጊዜ ይህን አጀንዳ ትይዥው ዘንድ አሳስቤሽ ነበር። ቀናዕይ ናት ብዬ ስለማምን።
2) "ዶር አብይን አታውቁትም።"
እህታለም ዕውነት ነው አናውቃቸውም። በስሱ እኔ ከ2016 ጀምሮ ለፍቅራዊነት ፕሮጀክት ሳስስ ከዶር ምህረት ጋር አገኘኋቸው። ያን ጊዜ ቁጥር አንድ ዶር አብይ ነበሩ። ያ ሰብዕና ነበር እንድደግፋቸው፤ እንድሞግትላቸውም ያነሳሳኝ። ጉግል ላይ ሥማቸውን ስፈልግ ጥቂት ቁጥር ነበር 500 እንኳን አይሞላም ነበር። ዬሆነ ሆኖ በአወቅኋቸው ዘመን ጀምሮ አሁን ቁጥር ስምንት አብይን አይቻለሁኝ። የፌስቡክ ምዕራፌም ስምንተኛ ነው። በተመፃደቅሽበት ጉባኤ ላይ ያው ስምንተኛውን አይተናል። ምን ትጠብቂያለሽ ብትይኝ። ቁጥር #ዘጠኝን ዶር አብይ አህመድን። አሳቻ ካልኳቸው ሦስት ዓመት ሆነኝ። አውዲዮም አለ። ፈቃድሽ ከሆነ እራስሽን ብቻ ከምታደምጪ ሌሎች ምን ይላሉ ብለሽ ዩቱብ ቻናሌ ላይ ገብተሽ አድምጭ። እርግጥ አክብሬ ነው እምሞግታቸው።
በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ #ቬርሙዳ ትርያንግል ስለመሆናቸውም ካወጅኩ ቆዬሁኝ። ይህን እዬመረመሩ ያሉ ነፍሶች እንደ አሉ ሙሉ ተስፈኛ ነኝ። ያው የሚያርዷቸው አለቆቻቸው። አጋድሜ ነው እምነግርሽ። ሌላም ልከልልሽ እህታለምዬ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ እንደ አዶልፍ ሂትለር፤ እንደ ፈርዖን፤ እንደ ጲላጦስ በህይወት እያሉ ለማወቅ ሊቸግር እንደሚችል፤ የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና በሥጋ ሲያልፋ አጥንታቸው ተመርምሮ ከተደረሰበት ብዬ ጽፌያለሁኝ። ለአፍሪካ ቀንድ፤ ለመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ፤ ለአህጉራችን እና ለዓለም፤ በተለይም #ለሴሜቲክ ማህበረሰብ አለርም ናቸው። ግን በህይወታቸው የዘለቀ ታማኝ ጓደኛ አላቸውን? ለዛ ገራገር ለዶር አንባቸው መኮንንም አልሆኑም እና። ፈንግል ናቸው። ሰብዕናቸው ንግሪኝ ካልሽ #ግራጫማ #ሲቃ ነው።
ይህን ዓለም ያጠናዋል። ዝም ብሎ ፈሶ ይቀራል ብለሽ አትሰቢ። ፈጽሞ። ለአለምም የአደጋ ምልክት ናቸው እና። አሁን ካልተገሩ ጋዳ ናቸው። ያልተገራ ወይፈን በረቱን እንደሚያውከው ዓለማችን በእሳቸው ትታወካለች የሚል ስጋት አለኝ። በቀለኛ፤ ቂመኛ፤ ምህረት የለሽ፤ አይዟችሁን የተላለፋ፦ ፍፁም ጨካኝ ግን ለስላሳ ቆዳ ያላቸው ናቸው እና። ዬሆነ ሰብዕና ሲያገኙ ይሰልቡታል። ውጭ ሲሄዱም መካኒዝማቸው ነው። ግን ይህ ጤዛ ይሁናል። እመኝኝ ብዬ አላስገድድሽም። ኮቴያቸው እራሱ ሊመረመር ይገባዋልና።
አዬሽው የልዩ ኃይል መፍረስ አጀንዳን መቼ እንዳመጡት? አስታራቂው ቲም መቀሌ ሳይገባ እሳቸው ቀድመው ቲማቸውን እንደምን እንደላኩ? ተዋህዶን አብጠልጥለው እንደገና ስንጥቁን ለመጠገን ምን እንደ ሠሩ??? አዬሽው አይደል ተዋህዶን እያወኩ ህወሃትን የጫካ መስተንግዶ ላይ ሲኳትኑ? በውሽልሽል ትርኪምርኪ ግድ ዬለም፤ ይሁን ሊባል ዬሚገባ ሰብዕና ዬላቸውም። ህወሃቶችም ቢሆኑ ሲነሪቲያቸውን አስመንጥረው አዲስ ከተቆረጠ ግንድ ላይ የሚያጨበጭብ ሁነት ይገጥማቸዋል። የቆዬ፤ ዬለማ፤ ዬቀደመ ነገር አይሹም። ቀስ ብለው ገብተው ያተራምሱላቸዋል። በእደሳ ስም። ጠብቂው። የወረደብን የዘመን በለቅ ይህ ነው። ይህን ዓለም ያጠናው፤ ይመረምረው ዘንድ ግድ ይላል። ዘመኑ ግሎባል ነውና።
3) ዬሥልጣን ልቀቅ ጥያቄ "ጅል፤ ጅላጅል ጅል አንፎ ነው" ብለሻል። እንዲያውም ብልህ ጥያቄ ነው፦ ተፈቅዶለትም ይሁን አይሁን አቶ ክርስትያን አነሳውም አላነሳውም ወቅት ይጠይቃል። ጥያቄው የተነሳበት ምክንያትም አዬሩን በጅራፍ ሾጥ ለማድረግ ሆን ተብሎ ነው። እኔም እኮ ክብርት ባለቤታቸውን ቀዳማይ እመቤትን ዝናሽ ታያቸውን አሳምነው መላ ይፈልጉ ዘንድ ተማጽኛለሁኝ። ምክንያቱም አቶ ኃይለማርያም ሥልጣናቸውን ሲለቁ የነበረው አዬር ደግሞ አይገኝም። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ በፈቃዳቸው ካልሆነ ብዙ ነገር ሊደረምሱ ይችላሉ። ጥንቃቄ ይሻል። እርግጥ ነው እኔም በኃይልም፤ በግርግር ምንም ነገር አልወድም። እራሱ መፈንቅለ መንግሥትን አልሻም። ደካሞች ይጎዳሉ። አናርኪዝም በባህሪው ልቅነት ስለሆነ ብዙ ጉዳት ያሸክማል። እሳቸው ወደው ግን ከሥልጣን እንዲለቁ ምኞቴ ነው። ማን ይተካ ዬሚለው። ቅብዓ እዮር ነው ዬሚወስነው።
4) ምርጫው ለአንቺ ነው በምርጫ መመረጣቸው ቅቡል የሚሆነው። እኔ እንደ አንድ የህዝብ አደራጅ እና መሪ ግን ምርጫ ልግጫ፤ ምርጫ እርግጫ፤ ምርጫ የስጋት ወፍጮ ቤት ሆኖ እንደአለፈ ይሰማኛል። ተጀምሮ እስኪፈፀም በአናርኪ ጉዞ ነበር። እንደሚገባኝ የፖለቲካ ፓርቲ ኦፊሻል ሠራተኛ ሆነሽ አታውቂም። ለዚህ ነው መርኽ አፈፃፀም ላይ ዳጥ እና ምጥ ዬሆነብሽ። ሁለት ነገሮችን አነሳለሁኝ በአጭሩ።
4.1) የጨነገፈ ምርጫ ነበር የተካሄደው። " ገዳዊ ብልጽግና " ብሄራዊ ጉባኤ፤ ማዕከላዊ ኮሜቴ፤ ፖሊት ቢሮ፤ ኤድትርያል እና ቁጥጥር ኮሚሽን፤ መሠረታዊ ሰነድ ደንብ እና ፕሮግራም፤ ከሁለቱ ዬሚመነጭ መሪ ዕቅድ ሳይኖር፤ አንድም አባል ሳይኖረው፦ መሥራቹ እንኳን አባል ሳይሆኑበት፤ በውራጅ አባል፤ በጉራጅ አካል፤ በዬኢቬንቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ተለቅሞ ዕውቅና የተሰጠው ነው። ሥሙን እራሱ እጠዬፈዋለሁኝ። አናርኪዝም ልቅነት ህግ አልቦሽ ስለሆነ። ለነገሩ ዬኦነግ ፖለቲካ ከህግ፤ ከሥርዓት፤ ከድንጋጌ፤ ከኖርም፤ ከሞራል ጋር የተፋታ ነው። ዶሮ በአጓት። በተለይ ለአንድ የፖለቲካ ድርጅት አናርኪዝም የመቃብር ሥፍራው ነው። የቮልሸቢክ እና የሜንሸቢክ ታሪክን በምልሰት አንብቢ።
4.2 ) በስጋት ዲል ባለ ጭነት ዬተከወነ ምርጫ ነው። ዓለም እንዲያውቀው በጀርመንኛ ጽፌዋለሁኝ። ትልልቅ ፖለቲከኞች ሳይቀሩ በዕለቱ እንደፈራነው አልነበረም ሲሉ ሰምቻለሁኝ። ያ እንዲሆን ቀድሞ ዬተሰሩ እስትራቴጂያዊ ኦፕሬሽኖች ነበሩ። የልበወለዱ የማፍያ ሞገድ ጋዜጣ እውን የሆነውም በኢትዮጵያ ነው። እንደ ጥንቸል ዬመሞከሪያ ጣቢያ።
ህዝብ ህወሃትን አክ እንዲለው ዬሰኔ 16/2010 የምስጋና ቀን፤ የኢንጂነር ስመኜው ህልፈት አባይን ከእነ ምንጩ ኦነግ ለመቆጣጠር፤ አንድ ከካናዳ፤ ሁለት ከአዲስ አበባ ወገኖች ነፃ እርምጃ የተወሰደባቸው፤ ባሊህ ባይ ያጡት 1300 አዲስ አበባወች ጦላይ ተወርውረው እስታሁን የቀሩት ያልተፈቱት፤ የአዲስ አበባ አምስት ሰማዕት ጭፍጨፋ፤ የቡራዩ ጭፍጨፋ፤ ዬለገዳዲለገጣፎ መፈናቀል፤ የአቶ ጃዋር የተከበብኩ እና ዬንፁኃን 87 ጭፍጨፋ፤ የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግደያ እና እሱን ተከትሎ የነበረው ጭፍጨፋ፤ የባህርዳር የአማራ ሊቃናት ጭፍጨፋ፤ የኦነግ ክንፍ በጫካ አጥቂ ሆኖ እንዲወጣ ዬተደረገለት ሙሉ የሎጅስቲክስ ድጋፍ፤ የአማራ ተማሪወች እገታ፤ የአጣዬ ከዘጠኝ ጊዜ በላይ፤ ዬሽዋ ሮቢት፤ የዝዋይ፤ የሻሸመኔ፤ የአርሲ ነገሌ መንደድ፤ የመስከረሙ የአዋሳ ትራጀዲ፤ የወላይታ፤ የገዲኦ፤ የአማሮ ሞት እና መፈናቀል፤ የመተከል ማዕትና የጭካኔ ዶፍ፤ ዬገዳማት እና የፓርክ ቃጠሎ ቀደምቱን እያነደዱ ነው አረብ ቀመስ ፓርክ እዬገነቡ ዬሚገኙት።
የብሄራዊ ኃይማኖታዊው እና አገራዊ ባዕላት ወከባ፤ ዬአብን፤ የባልደራስ፤ የአማራ እስር እና ጭፍጨፋ ይህ ሁሉ ህዝብ በፍርሃት፤ በጭንቀት፤ በስጋት ሆኖ ያን ሥርዓተ አልበኝነት ሂደት አማራጬ ብሎ እንዲቀበል ተገደደ። ዕውነቱ ይህ ነው። ሦስት ሰኔ፤ ሦስት ጥቅምት፤ አንድ መስከረም የስጋት ክብረ ባዕላት በኢትዮጵያ በአብይዝም የመቃብር ሥፍራ።
ለቀጣዩም ከአሁኑ እንደሚጀምሩ ተመረጥኩ ያሉ ዕለት ጽፌዋለሁኝ። ገና ዬአማራ ልጅ ይለቀማል፤ ይታፈናል፤ ይታገታል። ገና ብዙ ኦፕሬሽን ይጠበቅ። ብዙ ተፅዕኖ ፈጣሪም ይሸኛል። ጠብቂው። ብዙ ምስቅልቅል ይመጣል። ዛሬ የምናያቸው ነፍሶች ነገ ማዬት አንችልም። እኔ እንዲያውም ጭካኔው አልተጀመረም ብዬ ነው እማስበው። የከፋ እና የገዘፈ መከራ ፊት ለፊት ገና አለ እና። አብንን ባልደራስን እንደምን አሽመድምደው እንደወቋቸው ፊትሽ ላይ ያለ ሃቅ ነው።
4.3) አማካሪዬ ስለ እሳቸው ሳጫውታት ኦስካር ቢሸልማቸው ጥሩ ነው ትለኛለች። በራሱ ዬሚተማመን ጀግና በዬወሩ #ለፖፖ አይራወጥም። ለመሆኑ ሰምተሽ ታውቂያለሽ አንድ ወር ላይ መፈንቅል ሊደረግብን ተሞክሮ አከሸፍነው ያልተባለበት? ሙሉ ዓምስት ዓመት ሙሉ። ልታፍሩ ይገባችኋል። ፍርኃት ስለመፈጠሩ ሚስጢሩ ከጠቅላይ ሚኒስትርሽ ይገኛል።
4.5) አንድ ፓርቲ ጉባኤ ሲያካሂድ ስብሰባውን የሚመራው በፕሪዚዲዬም ነው። ቅድመ ጉባኤም አያካሂድም። ምርጫም በአስመራጭ ኮሜቴ ነው የሚመራው። ዕብኑ፦ የጨነገፈው የገዳ ምርጫ ቦርድ ይህ ዝክንትልትል እና ዝልግልግ ሂደት ሞገሱ ነው። የበታች አካላት ስብሰባ ካልሆነ ቅድመ ጉባኤ አይካሄደም። ልባቸው ደጭ ደጭ የሚሉት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ አስቀድመው ቅድመ ጉባኤ አካሄዱ። ከዛ እራሳቸው ዬአስመራጭ ኮሜቴ ሰብሳቢ ሆነው እንደ እንግዳ ዶሮ እዬባተቱ እራሳቸውን አስመረጡ። አንቺ ደረትሽን ነፍተሽ የምትናገሪለት ምርጫ በእኛ ዘንድ #እንኩቶ #እብቅም ነው። ዬመርህ ጥሰት የተጫነው። ለእኔ አልተመረጡም።
4.5) "ዬምርጫ ጊዜ ጠብቁ" ከትከት ብዬ ነው የሳቅኩት። ምንም የተያያዘ የተቀናጀ ፓርቲያዊ ዲስፕሊን ላለው ትምክህቱ ያስኬዳል። ለዚህ እኮ ነው በአመክኖዮ በሚራመድ ማህበረሰብ ዘንድ ስለወላለቀ ሰርክ ባህርዳር ላይ ጋራጅ ቤት ዬተከፈተው። "እሚሉሽን ባትሰሚ ገብያ ባለወጣሽ? "ብልጽግና ፓርቲ" ሆኖ???? እኔ እንደ አንድ የሠፈር እድር አላዬውም። ሥሙን ስጽፈው እጠዬፈዋለሁኝ። ለምን? የፖለቲካ ድርጅት የራሱ ማንነትን ያለው የትውልድ የህሊና ልቅና መቋጫ ስለሆነ።
4.5) አምስት የአብን አባላት የገባችሁት ወደ ፓርላማ ተፈቅዶላችሁ ነው? really? አስቱ? ዶር ደሳለኝ ጫኔን ወደው ፈቅደው? በበላዩ ላይ መፈንቅል የተደረገው ወጥ አማራ፤ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጅ ስለሆነ ነው። እሱን ከሚዩ ቀን ማንነቱን ቀይሮ ጨለማ ቢሆንባቸው ይመርጣሉ። እሱ ብቻ አይደለም በዚህ ልክ ውስጥ ያሉ አማራወችን ፈጣሪን ቢያገኙት ይበቀሉታል።
በዋዜማው ጉባኤ ተካሄዶ በማግስቱ አቶ ክርስትያን ታደለ ተፈታ። ለምን???? ዛሬ ዶር በለጠ ሞላ የያዘው የሚር ቦታ ዶር ደስአለኝ ጫኔ ቢሆን አይሰጡትም ነበር። አንድም ቀን በአቻ አይተው አጠገባቸው እንዲቀመጥ ፈቅደው አያውቁም። ሲመረጥ የአብይዝም ካንፕ ራድ በራድ ነው የሆነው። በምልሰት ሄደሽ በስውር የሚደግፏቸውን ሰብዕናወች እይ እዛ ሚዲያ ላይ አሁንም ስለሚንጎባለሉ። ለባልደራስ ከዲስ ሰው ስለምን ተላከለት??? ዬሆነ ሆኖ ዶር ደሳለኝ ጫኔ በከፍተኛ ድምጽ ሲመረጥ እንዴት እንደ ደነገጡ በሚገባ ከውስጤ ተከታትዬዋለሁኝ። በውሽልሽል ፖለቲካ ላልተፈጠርን ሁሉ ነገር ጉዳያችን ነው።
ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ 1% ዬአማራ ልጅ የሚጠብቀው ብናኝ ፈቃድ እና ውለታ ዬለም። የኦሮሞ ልጆች እንደ እኛ ለሳቸው አልተጉም። አውሮፓም አሜሪካም ሰብስበው አስገብተው በዶላር የሚያዘማንቸው፤ በአህጉር፦ በአለም አቀፍ ተቋማት ኑሯቸውን ያደራጁላቸው እነማን እንደሆኑ እናውቃለን። ይህ ሚኒሊካዊውን ዶር ጋዜጠኛ ታምራት ነገራን አይጨምርም።
የአማራን ሊቃናት ህዝብ ግን ያላቸው እንኳን እንዲደህዩ አምስት ዓመት ሙሉ በማቃጠል፤ በማንደድ፤ በማሰር፤ በመረሸን ሁለመናውን በከሉት። ዬአማራ ህዝብ በውጭጭ ነው የሚኖረው። እንኳንስ ለፓርላማ ሊታጭ??? አትቀልጂ እሺ። ለሞጋሳ ተጠማቂዎች ብትይ ያምርብሻል። ያው በጎደለ ሞላ ስለመሆኑ እዛው ፓርላማቸው ላይ ነግረዋቸዋል። ቅኔው ጎጃም ግን ወለም ዘለም ሳይል እሳት የላሱ ልጆቹን መርጦ ያን የተኛ፦ ለሽ ያለ፤ የታከተው፤ በዲስኩር አጥሚት መሽቶ ዬሚነጋለትን ግዑዝ አዳራሽ ነፍስ ሆነው፤ ነፍስ ዘርተውበታል።
በአንድ ነገር እስማማለሁኝ። ጥያቄውን ያውቀዋል ላልሽው። እሱ ብቻ አይደለም ጥያቄው እራሱ ጭብጡ ተፈልጎ ነው ወይንስ ከራስ መንጭቶ የሚለውም እንዲሁ ፈታትሸዋለሁኝ። ዝምታዬም ለዛ ነበር። አንቺ አላስቀምጥ ብለሽ አስነሳሽኝ እንጂ። ሌላው እኔ ስለፖለቲከኞች መመስከር፤ መሞገት ከንቱ መሆኑን ስለተረዳሁኝም በዝምታ ነው እምተባበረው። ምክንያቱም አናውቃቸውም። እነሱም አያውቁንም። ስለሆነም ዬተነሳው ጥያቄ አትራፊነቱ አፈፃፀሙ በማን? ለምን አላውቀውም። ግን ከአቶ ክርስትያን ታደለ በፊት በጥዋቱ ሻለቃ ዳዊት ሲያቀርቡት አውቃለሁኝ። ከዚህ ጋር አለካልከሽ ያቀረብሽው ስለ አማራ የሥልጣን ፍለጋ ያቅለሸልሻል። የአማራው ውክል ሙሉ 45 ድምፁን ሰጥቶ ነው ለዚህ ያበቃችሁ? ዕዳ አለባችሁ።
5) "ሃሳብ የላችሁም" እንዲህ ቃለ አቀባይ ሊቀ መኳስ መሆንሽን አላውቅም ነበር። ጉልበታም፤ ዬደረጀ፤ ግርማ ሞገስ ያለው ልዑቅ ሃሳብ አለን። #ኢትዮጵያኒዝም። ከዚህ በላይ የላቀ ልዑል ንጉሥ ሃሳብ ዬለም። ኢትዮጵያኒዝም ዩንቨርስቲ ገብተው ሊማሩት የሚገባ ፍልስፍናም ሳይንስም ነው። ሰብሳቢያችን፤ ሙሴያችን የአብርኃሙ ቤት #ኢትዮጵንያኒዝም ነው። ማስትሽ ያሰኝሽ ይሆን? ቃለአባይነት በኢትዮጵያዊነት፤ ክህደትም ቅጣቱ የላይኛው ነው። የተከበርሽበት ሚሊዮኖች አስቱ የሚሉሽ ምራቅ ላይ ባለው #"መደመር" አይደለም።
5.1) ከዚህ ሌላ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊን ዬሚያግዝ አካል እንዲደራጅ የቀደመ፤ ዬተደራጀ፤ ነፍስ ያወቀ፤ ለዕይታ ክፍት የሆነ ሃሳብ መዋቅሩን ሁሉ ሠርተው አቶ ልደቱ አያሌው አቅርበው ነበር። ለቅንድብ ፀጉሩ ለኦነግ የጭካኔ ፕላን ስላልተመቸ ከርሸሌ ተወርውረዋል። ሞትም ተፈርዶባቸው ነበር። በኪነ - ጥበቡ ነፍሳቸው ተርፋለች። ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ሙሉውን የአቶ ልደቱ መንፈስ ዘራፊም ናቸው። ከቀለም ምርጫ ጀምሮ። አሉ የሚባሉት 10 የኦነግ ድርጅቶች ህወሃት የፈጠረው ኦህዴድን ጨምሮ ተጨፍልቀው የአንድ የአቶ ልደቱን ሃሳብን ቀድሞ የማደራጀን አቅም ዬላቸውም።
እራሱ ተጨባጩን አጥንተው፦ ዬሌላውን ሰው ሃሳብ ሰብስበው ማኔጅ የሚያደርጉበት፤ የሚደርሱበት አስስመንት፤ ከዛም ከዚህም የሚራወጡ የሃሳብ አዙሪቶች መልክ እና ቁሙና ከተሟላ አመክንዮ ጋር በቸር ፐርሰን ኳሊቲም የሃሳብ ማዕከል የመፍጠር፤ የማቅረብ አቅማቸው አንቱ ነው። በራሳቸው የዕይታ እና አድማስ የፖለቲካ አቋም።
ያ ዬሽግግር ሃሳብ ግን እንዲደናቀፍ ባልደራስም በዲሲ አማካሪው በአቶ ኤርምያስ ለገሰ፤ ኦፌኮም በሚኒሶታ አማካሪው እና በአቶ ጃዋር መሐመድ ተዳባይ ሰነድ ተጣድፈው አቀረቡ። እናም ዬአቶ ልደቱ በጣም ጠቃሚ፤ አዳኝ፤ የቀደመ ሃሳብ ተዳፈነ። ከፋክክር ያን እንደ መነሻ ሃሳብ ወስዶ በፓናል ዲስከሽን ማዳበር፤ መቀነስ፤ መጨመቅ፤ እና አንጥሮ ማውጣት ይቻል ነበር። ከዛ በኋላ ነው አይደል ጦርነቱ ዬተካሄደው???
ለነገሩ ስውር እጆች አብን እና ባልደራስን አይሆኑ አድርገው ዕውቅና ለኦነጋዊ ምርጫ መንፈስ እንዲያገኙ ተደርጓል። አዲስ አበባ ላይ የአብን አርማ እንዳይታይ የተደረገበት ቅንቅን ሴራ የዘመን ግማድ ነው። በወቅቱ ከዲሲ እስከ ቤተመንግስት የተሠራ ሰንሰለት ብዬ በተከታታይ ሞግቸዋለሁኝ። 50+ አማራ በሆነባት የዳዊት ከተማ በሸፍጥ እንደዛ ታሪክ ተቀበረ።
5.2) ያን ሞገደኛ የዲያስፖራ የፖለቲካ አቅም እና አቋምም እንደምን እንደሰለቡት ታውቄያለሽ። መሪው በቀን አምስት ሚዲያ ላይ ይቀርብ ነበር። ነፍሱን አያውቀውም ነበር። ሌላው ግንቦት 7 ሚሊዮኖች ተስፋ ያደርጉት ነበር። እናቶች ሁሉ ይወዱት ነበር። እኔ በጥዋቱ ገምግሜ ያደምጡኝ ዘንድ በትህትና አሳስቤም፤ ባለመሳካቱ ተስፋ ለማድረግ ባይዳዳኝም። ሞጋቹም ነበርኩ። ብዙም አግቶኛል።
ቁምነገሩ ግን ሁሉን ያቀፈ መንፈስ መፍጠር አለመቻሉ፤ ተስፋችን ማስጠጋት ባለመቻሉ የነቁት ይወርሳል ሆኖ ዕድሉ ??? ይህው ኢትዮጵያ ለግራጫማ መንፈስ ተሰጠች። ሃይማኖቱ፤ የፖለቲካ አቋሙ፤ አምሳያው የማይታወቅ #ቬርሙዳ ትርያንግል። ግንቦት ብልህ ቢሆን አቅም ቢንከባከብ፤ ላም እረኛ ምን አለ ቢያደምጥ ኖሮ ባለሜዳላይ ይሆን ነበር። ተቦርን የሚለው ነገር ነበር "ሙሽራ ሁን ስንለው ሚዜነት አሰኜው።" በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ሃይማኖት አላቸው ብዬ አላምንም። ቅይጥይጥ፦ ዝንቅንቅ፦ ዝብርቅርቅ ስለሆኑ።
#ብቻ …… አወን ብቻ ……
በጣም ተዳፈርሽ። ኢትዮጵያ ሊቃናት የመከኑባት፤ ኢትዮጵያ ሊሂቃን #መሲና የሆኑባት አገር አደረግሻት። ለዛውም የፍርሻ፤ የንደት ፋንታዚን የሙጥኝ ብለሽ። ግን ግን ዬእኔ አስቴር ስለ ሳይለንት ማጆሪቲ ምን ታስቢያለሽ? አገላለጽሽ ለሙጠሽ ስላቀረብሽው። የታመቀ ዕንቁ እዛም እንደአለ ላስታውስሽ ብዬ ነው።
6) ትምክህት ረግረግ ነው። እህታለም ይቅርብሽ። "ሰው የላችሁም፤ ሃሳብ የላችሁም።" ጭካኔ ነው። እንኳን እኛ አውሮፓውያን እና ምዕራባውያን ሙሴ ፍለጋ ላይ ናቸው። ይህ መርዶ ሊሆንብሽ ይችላል። እመኝኝ ብዬም ዳገት ቁልቁለት አልማስንም። ግን #ዜሮ ላይ እንዳሉ ጠቅላይሽ በትህትና ላስታውስሽ እሻለሁኝ። ለህወሃት ከፍ እና ዝቁ ብጣቂ ርህርህና ቢቸረኝ ብለው ነው። አይሳካላቸውም። #ቬርሙዳ ትርያንግልን አምኖ ቅንነትን፤ መታመንን የሚቀልብ የአለም የፖለቲካ ሊቃናት ይኖራሉ ብዬ አላስብም። ግን ዶር ወርቅነህ ገበዬሁ ዬት ናቸው? ዘና ወዛ የምታደርግ ጥያቄ ለክብርቴ።
7) "ባነንኩኝ" #ዳ! ብለሽ ነበርን??። እሰይ እናቱ! #ፐፐ! የሚሊዮን ዲያስፖራ ግብዣ ዘመን የዬካቲቱ ትንቢትሽ ለማን ተሸጠ። አዲስ አበባን ፈጠራት አዘመናት ስትይ እኮ በውስጡ እንደአለሽ አመሳጣሪ ነው። ቦግ ድርግም በሚለው ተቃውሞሽም ዕንባ ስደት ስለመሆኑም እኮ እንደ ትልቅ ሙዚዬም አሳይተሽናል። "ከልብ ካዘኑ ዕንባ አይገድም ይላሉ" ጎንደሮች ባለቅኔ ናቸው እና። #ቃ#!
 "ትታክታላችሁ እንጂ ዬእሱን ኢትዮጵያ እዬሠራት ነው።" ከዕቅዱ ዝንፍ ዬለም። ይህን ለማህበረ የፍሪንባ ቤተኛ፤ ዬሞገሳ ተጠማቂ ንገሪ። ታሪክ፤ ትውፊት፤ ቅርስ፤ ውርስ፤ ኃይማኖት፤ ማንነትን፤ ሰንደቅ ዓላማ፤ አማርኛ ቋንቋ፤ ግእዝን፤ ዬስሜን ፖለቲካ ሁሉም ጦርነት ታውጆባቸው እዬተደረመሱ ነው። ለመሆኑ የጠፋውን የቁቤ ትውልድ ለመመለስ ስንት ወርክሾፕ ኦሮምያ ላይ አደራጅተሽ መራሽ? እንኳን አንቺ አለቆችሽም አልደፈሩትም። የቅምጥ ፍላጎት ስበት ስበቃ ስላለ። ዬኦሮምያ የበላይነት ያለበት ዬአማራ አናሳነት በምንጣሩ አርቲፊሻል ኢትዮጵያ ምን አልባትም ……???
9) ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስተሩን የምርጫ ዘመን ሳያልቅ ከሥልጣናቸው የማንሳት ሙሉ መብት አለው። እንግሊዝ በአምስት ዓመት ውስጥ ወደ ስድስት የሚጠጉ ጠቅላይ ሚኒስተሮችን ሹሟል፤ ሽሯልም። መርህ ነው ይህ። አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ ፈቅደው ነው የወረዱት። እሳቸው ሲወርዱ ትካቸውን ዬሾመው ፓርላማው ነው። አቶ ለማ መገርሳ የፓርላማ አባል ስላልነበሩም ነው ዕድሉን ለዶር አብይ የሰጡት። ዶር አብይ የፓርላማ አባል ስለነበሩ በፕሮሲጀሩ ዶር አብይን በመሾም ኦህዴድ ለሥልጣን በቅቷል። በሰላማዊ መንገድ። እኛ ሠራነው በማለት በቀውስ ባጀት አነኮረው እንጂ። በመርህ መቃናጣት አይቻልም። ፈጽሞ። "በብልጽግናም" ጉባኤ እሳቸው ሌላ አሰራር ተከትለው በጉባኤ እራሳቸውን ጠቁመው ተመራጭ ሁነዋል። ስለዚህ ጉባኤው ሊያነሳቸው ይችላል።
እዬተንዘፈዘፋ እራሳቸውን ጠቁመው፦ እራሳቸው ድምጽ ያሰጡትም ለለዚህ ነው። በፓርቲ ህይወት ውስጥ ግን መሆን የነበረበት ጉባኤው ማዕከላዊ ኮሚቴ ይመርጣል። ማዕከላዊ ኮሚቴው ፖሊት ቢሮውን ይመርጣል። ፖሊት ቢሮው የፓርቲውን መሪ ይመርጣል። ያ እንኳን ባይሆን ማዕከላዊ ኮሜቴው መሪውን ይመርጣል። እርሳቸው ያላደፈረሱት ግሎባል መርህ የለም። እራሱ ኮሜቴ በጎደሎ ቁጥር ይመረጣል። ለምን? እኩል ድምጽ ከሆነ ዬሰብሳቢው ድምጽ ወሳኝ ስለሆነ። እሳቸው ይህን አይከተሉም የገዳን የሥራ ዘመን ወስደው ስምንት ያደርጉታል። ለአንድ ቀን የቆዩ ወዘተረፈ ኮሜቴ እና ኮሚሽኖች አዋቅረው ነበር።
በወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል የሚመራ የአዲስ አበባ የወሰን ኮሜቴ ሲያደራጁ ስምንት ነበር፤ አሁን የአዲስ አበባው ሥራአስፈፃሚው እንደዛ ይመስለኛል። የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያ ፓርላመንታዊ ሥርዓት ተከታይ ሆና እሳቸው ግን አካሄዳቸው በሁሉም የኢትዮጵያ መሬት ተወዳድረው እንደተመረጡ #ፕሬዚዳንታዊ አድርገው እዬመሩ ይገኛሉ። የሳቸው ውክልና በሻሻ ነው። በቃ። ይህን ያህል አያቀናጣም። ዬሚገርመው ፕሬዚዳንት ሥም ቀርቶባቸውም ነበር በፋንታዚው ድርጅታቸው ፕሬዚዳንት ተብለዋል።
10) "ከእኔ በላይ የሚያውቀው ዬለም።" ክብርት ቀዳማይ እመቤት ዝናሽ ታያቸው ይህን ይመልሱት።
#ይጠቅለል በባውንድ።
ለመሆኑ ሚሊዮን ወገኖችሽ ሲታረዙ፤ ሲፈናቀሉ፤ በዕንባ ሲዋኙ ቀረብ ብለሽ አይዟችሁን አጠጣሻቸውን?? እሩቅ ሳይሆን ከቅርብሽ ደብረብርኃን። አጣዬ ስንት ጊዜ ነደደች?? ጥቂት ዬቤት ሥራ።
ዬኦነግን ዬሞጋሳ ልጅነት የማንቀበል ጉዞውን #አክ! ብለነዋል። አንቺው ፏ ፍንትው ብለሽ ዘና በይበት።ፌዝሽ፤ ስላቅሽ፤ መስቃሽ፤ ማቃለልሽ፤ ማጣጣልሽን የኢትዮጵያን ሊቃናት እና ሊሂቃንን መታበዬሽን ግን ልክ አስይዢው። በልክ መራመድ። በልክ መኖር። ልክን አውቆ መኖር ጥበብ ነው። "ልክን ማወቅ ከልክ ያደርሳል" ይላሉ ጎንደሮች ቅኔውን ሲዘርፋት።
ወዳጆችሽ ነግረውሽ እንደምታነቢው ተስፋ አደርጋለሁኝ።
"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም
ይናገራል፤ ሰው ግን አያስተውለውም።"
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
31/03/2923
ከቅድስት ሲዊዘርላንድ፤፦ ከጭምቱ ቪንተርቱር ከተማ።
እህትዓለም መልካም ሰንበት።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸኔፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።