እነ ቢቢኤን "ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል።"
„የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል!“ ከሥርጉተ ሥላሴ 04.07.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ) „በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጁ ሰፊ ነው፤ መንገዱም ትልቅ ነውና፤ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ ወደ ህይወት የሚወስደው ደጁ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና፤ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።“ (የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፲፬) እንደ በር። ከቶ እንዴት አላችሁልኝ ክብረቶቼ። አሁንም ትዝብቴን ላጋራችሁ ነው። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በባዕለ ሹመታቸው ባደረጉት ንግግር ላይ ሰፊ ቅሬታ ካሰሙት ውስጥ እንደ ሚዲያ ቢቢኤን እንደ የራዲዮዎ ጋዜጠኛ ደግሞ አቶ ሳዲቅ አህመድ ነበር። ያው "የድምጻችን ይሰማ" ቤተሰብ ስለነበርኩኝ ዜናው አዲስ ስለሚሆን ተግቼ እከታተለው ነበር። በመደበኛ። የቢቤኤን ጋዜጠኛውን አቶ ሳዲቅ አህመድ ደግሞ ከማከብራቸው ነፃነትን ከሚሹ ቅኖች እንደ አንዱ አዬው ስለነበር ሳነበው ደነገጥኩኝ። እርግጥ ነው ራዲዮ ጣቢያው ገና ከውጥኑ ጀምሮ ነበር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለእጩ ጠ/ ሚርነት ሲወዳደሩ ነበር ወጮፎውን ያወረደው። እስከ ደነግጥ ድረስ። አንድ ለውጥ ሲመጣ የለውጡ ቤተኞች ደስ ሊለን ሲገባ የሃይማኖት ሰበዝ መሰበዝ ተጀመረ። እኔም ላጣው ስላልፈለግሁኝ ሥሙን ጠቅሼ ጻፍኩኝ። የሚገርመው ለቢቢኤን ጋዜጠኛ አቶ ሳዲቅ አህመድ የሹመት ንግግር ማለት ፖሊሲ መስሎታል። ወይንም የሥራ ዘመን መከወኛ ሪፖርትም መስሎታል፤ ወይንም መጸሐፍ እንዲሆን ፈልጓል። አንድ የሹመት ንግ...