እነ ቢቢኤን "ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል።"
„የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል!“
ከሥርጉተ ሥላሴ 04.07.2018
(ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ)
„በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጁ ሰፊ ነው፤
መንገዱም ትልቅ ነውና፤ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
ወደ ህይወት የሚወስደው ደጁ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና፤
የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።“
መንገዱም ትልቅ ነውና፤ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤
ወደ ህይወት የሚወስደው ደጁ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና፤
የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው።“
(የማቴወስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፫ ቁጥር ፲፬)
- እንደ በር።
ከቶ እንዴት አላችሁልኝ ክብረቶቼ። አሁንም ትዝብቴን ላጋራችሁ ነው። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በባዕለ ሹመታቸው ባደረጉት ንግግር ላይ ሰፊ ቅሬታ ካሰሙት ውስጥ እንደ ሚዲያ ቢቢኤን እንደ የራዲዮዎ ጋዜጠኛ ደግሞ አቶ ሳዲቅ አህመድ ነበር። ያው "የድምጻችን ይሰማ" ቤተሰብ ስለነበርኩኝ ዜናው አዲስ ስለሚሆን ተግቼ እከታተለው ነበር። በመደበኛ።
የቢቤኤን ጋዜጠኛውን አቶ ሳዲቅ አህመድ ደግሞ ከማከብራቸው ነፃነትን ከሚሹ ቅኖች እንደ አንዱ አዬው ስለነበር ሳነበው ደነገጥኩኝ።
እርግጥ ነው ራዲዮ ጣቢያው ገና ከውጥኑ ጀምሮ ነበር ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ለእጩ ጠ/ ሚርነት ሲወዳደሩ ነበር ወጮፎውን ያወረደው። እስከ ደነግጥ ድረስ። አንድ ለውጥ ሲመጣ የለውጡ ቤተኞች ደስ ሊለን ሲገባ የሃይማኖት ሰበዝ መሰበዝ ተጀመረ። እኔም ላጣው ስላልፈለግሁኝ ሥሙን ጠቅሼ ጻፍኩኝ።
የሚገርመው ለቢቢኤን ጋዜጠኛ አቶ ሳዲቅ አህመድ የሹመት ንግግር ማለት ፖሊሲ መስሎታል።
ወይንም የሥራ ዘመን መከወኛ ሪፖርትም መስሎታል፤ ወይንም መጸሐፍ እንዲሆን ፈልጓል። አንድ የሹመት ንግግር የፖሊሲ ሃሳብ ሊይዝ ይችላል፤ አቅጣጫ አመላካችም ሊሆን ይችላል። ግን ለእነዛ በቀጣይ በህግም በዝርዝር የአፈጻጻም መመሪያ ጊዜ ጠብቆ የሚደገፍ እንጂ በሹመት ንግግር የሚጠቃለል አለነበረም። ለነገሩ „የድምፃችን ይሰማ“ ተጋድሎ ስለሆነ ወደ ትግሉ የጨመረው ብዙም የሚያስፈርድ ባይሆንም፤ በተፈጥሮው ባለው ንቃት እና ትጋት ግን ይህን መመዘን ይጋባው ነበር እንደ ምርጥ እና ተቃዊ የፖለቲካ ተንታኝነቱ።
- የመርዶው ሚዲያ።
ዶር አብይ አህመድ ጠ/ ሚር ከሆኑባት ቅጽበት ጀምሮ ብጥብጥን ሲለቃቅም፤ ምሾ ሲያወርድ፤ መርዶን አጭቶ ሲያጋባ፤ ዋይታን ሲደለቅ ከራረመ የተከበረው ቢቢኤን። ከተወሰነ ጊዜ በኋዋላ ጤናዬ ያስፈልገኝ ስለነበር አቆምኩት። ያቆምኩት ሁለቱንም ነው። ህብር ራዲዮን ጨምሬ። ምን በወጣኝ ልጢስ፤ ምን ባደረኩኝ ልንደድ፤ ምን ስለሆነ ልክሰል። ያው ሁሉ ማዕት የሚወርደው ዬፓርለማውም የምክርቤቱም አፈ ጉባኤዎች የእስልምና ተከታይ ሴቶች ናቸው። ሁለቱም።
አሁን ዛሬ ከሳተናው ድህረ ገጽ ስገባ አዲስ ዜና ይዞ ጉብ ብሏል አጅሬው አቤቶ ቢቢኤን።
እርጋታ የነሳው፤ አቅል የነሳው፤ አደብ የነሳው ልግመኛው የኢትዮጵያ ፖለቲካ በሃቅ ምህዋር እዬተረታ ነው። ተመስገን። መተቸት ቀላል ነው። መበተንም ቀላል ነው፤ ማሳሳትም ቀላል ነው። መቀደድም ቀላል ነው። ማፍረስም ቀላል ነው። የትውልድን ሰብዕና በጠራ ሞራል መግንባት፤ ማነጽ፤ ማቋቋም፤ ማብቀል፤ ማጽደቅ፤ ማብቃት ደግሞ ፈታኝ ነው። ለዛውም ቂም እና በቀል፤ ሴራ እና ሸር ቦብንዳ በሚቸበቸብበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ።
የኢትዮጵያ ሚዲያ የሚመርጠው መንገድ ደግሞ ቀላሉን መንገድ ነው። መጥኔ ለእነሱ … አሁን በአንድ ራስ ሁለት ምላስ እንዲሉ እንዲህ ይሉናል …
- ዜና ብሥራት።
„የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጋር ተገናኝቶ ተወያየ! July 4, 2018“
ይልቅ ኡስታዝ አህመዲን ጀብል አላሳፈረኝም „የድምጻችን ይሰማ“ ቤተኝነቴን፤ ከኢትዮ ዩቱብ ጋር በነበረው ቆይታ በእስልምና ተኮር ብቻ ሳይሆን ስለ ሰው ልጅ ትጋት ማድረግ እንደሚፈልግ ገልፆል፤ መንፈሴ በሳጥን ውስጥ እንዲቆለፍበት አልሻም ብሏል።
በእስር ቤት ውስጥ ቆይታዬ አገሬን እንዳውቃት አድርጎኛል ይላል። እኔም ተባረክልኝ ወንድም ዓለም ብያዋለሁኝ። እኔ ባገኘው ቃለ ምልልስ ባደርግለት ደስ ይለኛል። ምርጤ ነው። እነ አጅሬማ ዛሬ „የህዝበ ሙስሊሙ የደስታ ቀን ነው“ ነበር የቢቢኤን ዘገባው። የደምጻችን ይሰማ አርበኞች መፈታት የኢትዮጵውያን ደስታ አልነበረም። እኛን ደስ አይለንም ወይ? እኛንስ ይከፋናል ወይ መፈታታቸው?
እነሱ በመንፈስ ይህን ያህል አግለውን አርቀውን እኛ ግን አሁንም እናከብራቸዋለን። ቢረሳ ቢረሳ የጎንደር ህዝብ እንዴት ይረሳ። ለነገሩ ሥርጉትሻ ብቻ እኮ ናት "እኔም ድምጻችን ይሰማ" ብላ የወጣችው፤ እሷም ጎንደሬ ናት።
Ungerecht (injustice) neue
ይሄ ፊልም በጣም ብዙ ቦታ ተልኳል። እዚህ ሲዊዘርላንድ ውስጥ አንድ የአጭር ፊልም ውድድር ላይ ተሳትፏል። እናት ከሚለው አጭር ፊልሜ ይልቅ ይሄኛው ፊልም የተሳታፊው ምርጫ ነበር፤ አሸናፊውም ያው ከፍቅር ጋር የተያያዘ የአንሜሽን ፊልም ነበር። በውስጤ ሳትኖሩ እኔ ሥርጉተ እንዲህ እምሰራው ይመስላችሁዋለን? አትሰቡት።
ሰማይ ዝቅ ምድር ከፍ ቢል ሥርጉተ ስታምንበት ብቻ ነው መንፈሷን የምትለግሰው። ያለመንኩበትን አላዬውም፤ አላዳምጠውም፤ አላነበውም። ድርሽ አልልበትም። አሁን በታሪኬ ሦስት ጊዜ የአብይ መንፈስ ያለበትን የሹመቱን፤ የከቢኔ ሽግሽጉ እና የሰሞኑን የፓርላማ ውሎ ሙሉውን አዳምጫለሁኝ። የእኔ ስለው፤ አጀንዳዬ ስለው።
የሚገርመው እንደ እናንተ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ፓርላማው ወስጥ ስላለ፤ ስሌለ የሚለው በውስጤ የለም። ያን ብትክትክ እንጉልቻም ካቤኔ በሥርዓት የሚመራ ሙሴ፤ አፌ ጉባኤ አለ ብዬ ስለማምን እከታተለዋለሁኝ በአደብ። ለሚቀርቡ ጥያቄዎችም አመርቂ መልስ የሚሰጥ ነፍሴ አለ እዛ። እንደራሴ ጉዳይም አድርጌ እንጂ አርቄም አይደለም እምከታተለው ይህም የእኔ ስላልኩት ብቻ ነው።
የማይመች ሃሳብ ሳይፈጠረ የሚመች ሃሳብ ስለመኖሩ አናውቅም ነበር። ዴሞክራሲ የማይመችህን እንደሚመችህ አድርገህ መቀበል እና ሞግተህ የሚመችህ ሃሳብ አሸናፊ እንዲሆን ማስቻል ነው። ያ ደግሞ አዬር ላይ በሚመራ የፖለቲካ አቅም አይደለም። በበሰለ እና በበቃ ንቃተ ህሊና መሬት ላይ በሚሠራ ተግባር ነው። የነቃውን የህሊና ክፍልን ማሰራት ግድ ይላል። መርሁን ጠንቅቆ በብቃት የሚያውቅ ወስጤ እዛ ስላለ ደስ ብሎኝ እከታተለዋለሁኝ። ወደፊትም። የሚተች ሲኖር ደግሞ አልምረውም።
- · ቢቢኤን እና ፖለቲካ የለውጥ መንፈሱ እንዴት እንደተባጀ ይታወቃል።
እንደዛ ስናብጠለጥል፤ መንፈስን በሰላ ፋስ ስንከፍል፤ ስሜትን እንዳሻን ስንሰነጣጥቅ ስንበትን ባጀን። አሁን ለዛ ማን ካሳ ይክፈል? መንግሥታዊ አማራር ወንዝ ወረድ ተብሎ እንደሚቀዳ ውሃ ተምስሏል። ለዛውም በኢትዮጵያ ዝብርቅ፤ ቅይጥይጥ ፖለቲካ ስሌት ደግሞ እጅግ ጎምዛዛ መራራ ጉዳዮች አሉበት።
አስተዳደር ሽልንግ ተይዞ ገብያ ተሄዶ የሚሸመት ሸቀጥ አይደለም። ሃሳብ ያስፈልጋል፤ ከዛ ንድፍ ያስፈልጋል፤ ከንድፍ ቀጥሎ ዕቅድ ያስፈልጋል፤ ከዕቅድ አስቀጥሎ ጊዜ ያስፈልጋል፤ ከዚህ ጋር መዋለ ንዋይ ያስፈልጋል። ፈጻሚ አካል ማደራጀት ይጠይቃል። ለዚህ ሁሉ ደግሞ መፈጸሚያ ወለል ያስፈልገዋል። አፈጻጸም ከባድ ነው። የወንዝ ውሃ አይደለም ወይንም የመስኖ ...
አመራር ህሊናን ማደራጀትን ይጠይቃል። በዚያ ላይ ኢትዮጵያ አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ውስጥ ሆና ነው የባዕለ ሹመቱ የተከናወነው። ይህ በሌላ አገር ታሪክ እራሱ እኔ ሰምቼ አላውቅም። ምን ያህል በታፈነ መከራ ውስጥ ሥርዓቱ እንደ ተከወነ መመዘን ይገባል ሰው ከተሆነ፤ ህሊና የሚባለው ልጥፍ ሳይሆን ተፈጥሯዊ ከሆነ። ከእኛ ጉዳይ ጋር ያቺ ቀን መያያዟ ሳይሆን ስለ አገራችን ቀጣይነት ነበር ለሁላችንም አጀንዳ ሊሆን የሚገባው። በውጪም በውስጥም ሊፈነዳ የተቀረበ እውክ አዬር ነው የነበረው፤
በወያኔ ሥር የነበሩት መዋቅራዊ ሰንሰለቶች ቀጠዮች ናቸው። 27 ዓመት ተስርቶበታል። በቀላሉ መናድ እና ማፍረስ የሚችል ክንፍ ያለው የመላዕክታን ካቢኔ አይደለም የአብይ ካቤኔ። ከላይ እስከታች በስሚንቶ ተገንብቷል። ማረሚያው ደግሞ የአንድ ሰው ሃላፊነት አይደለም የትውልድ ነው። ሥርዓት መፍጠር ነው ትኩረት ሊደረግበት የሚገባው። ሰው ሊኖርባት የሚችል አገር መፍጠር መቻል ነው አጀንዳ ሊሆን የሚገባው የነበረ።
ለውጡን ቅኖቹ ባይደግፉት ሐዋርያቱ ባይገፉበት የዛሬው ቀን አይገኝም ነበር። ግን አቅል ከዬት ይሸመት? አልተፈጠረልንም። ለዚህ ነው እኔ እዮባዊነት በእጅጉ ያስፈልገናል ብዬ የጻፍኩተኝ። በሌላ በኩልም እጬጌው ሄደት ያልኩትም እንዲሁ። መቼም ከጣና ኬኛ በኋዋላ እኔ ብልህ ፖለቲከኛ ማግኘት አልቻልኩኝም። ተዉ! የሚል እንኳን አንድ ልብ ያለው አደብ የገዛ ሊሂቅ እንዴት ይጠፋል? አለመታደላችን ይሄው ነው። ሰላማዊ ትግል ሲሉ የነበሩት ሁሉ ሽብልል ብለው ማእት አውርድ ሆነው አረፉት።
ብቻ የሚያፍርበት ይፈር … ለወደፊቱ ግን የተከመረው የቅጥልልጥል የሥም ብዛት ብዙ ዓይነት ሥሞችን፤ መጠሪያዎችን ነው ያለን። ያ ድርቆሽ ሆኖ እንዳይቀር ሙያዊ ክህሎትን ለማሳደግ መጣር ያስፈልጋል።
ሳቢያዎች ራሳቸው ራሳቸውን ነው የሚፈልሱት። ምክንያታዊነት ግን ያዘልቃል። አንገትም አያስደፋም። ነፃነት ሲባል የአንድ ሃይማኖት ነፃነት ብቻ አገር እና ትውልድን አይገነባም። ሃይማኖት ሰው ከተፈጠረ በኋዋላ ነው የሚቀበለው፤ ሲፈልግም የሚቀይረው ነው። ሰው ግን አገርን የፈጠረ ዕጹብ ድንቅ የፈጣሪ ፍጡር ነው። በዛ ላይ መተታሩ ነው መልካሙ መንገድ። አገር ከሌለ፤ ህዝብ የለም። ህዝብ ከሌላ ሃይማኖት የለም። ማምለኪያ ቦታም አይኖርም፤
በጠ/ ሚር አብይ አህመድ የሹመት ንግግር ላይ የማከብረው ጋዜጠኛ ሳዲቅ ይህን ብሎን ነበር።
"ተስፋና ስጋት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሹመት – ከሳዲቅ አህመድ"
https://www.zehabesha.com/amharic/archives/89683
ለዚህ የተሰጠው መልስ ደግሞ ከአውስትራልያ ከሜልበርን ከጸሐፊ አቶ በድሉ በዛብህ ይሄ ነበር።
"ይድረስ ለሳዲቅ አህመድ እያየን እንራመድ !! እያስተዋልን እንተንፍስ !!"
ኦቦ ለማ መግርሳ ዕውቅና እያገኙ፤ ተቀባይነት እዬአገኙ ሲመጡ ቢቢኤን ይህን ሠራ።
"News Analysis: Hidden Truth About Lemma Megersa"
243 233 ህዝብ ተመልክቶታል፤ በኢትዮጵያዊው ሐዋርያዊው ለማ መንፈስ ላይ።
ኦህዴድ የሥልጣን ሽግግሽ አድርጎ ዶር አብይ አህመድን ወደ ፊት ሲያመጣ ደግሞ ቢቢኤን ይህን አመጣ። መቼም ኢሳት ይህን ቢያደርግ አይደንቅም ግንቦት 7 ህሊናው ስለሆነ። ኦቢኤንም ይህን ቢያደርግ አይደንቅም ኦርጅናሉን ኦንግን ስለሚያልም፤ ግን ቢቢኤን የትኛውን ፓርቲ ተጠግቶ ነው ሲያምሰን የከረም? ወይንስ እኛ የማናውቀው የተደራጀ ነገር ነበረ ወይ ያሰኛል?ይህን ሳስበው በጣም ያስፈራኛል።
„ሕወሓት ለማ መገርሳን ለጠቅላይ ሚኒስተርነት ለምን አልፈለገችውም?
– ጀዋር መሐመድ ያብራራል | ከሳዲቅ አህመድ ጋር ተወያይቷል“
ይሄን ደግሞ ዛሬ ጉግል ቢጋባ ምን ያህል ህዝብ አብይ እንደሚል ያገኙታል። የኬንኒያ ሚዲያ ሊሂቃኑ እንጸልዬለት ሁሉ ብለዋል።
ጽንስ በአንድ ቀን ተወለድህ፤ አድገህ፤ ዩንቨርስቲ ገብተህ፤ ተመረቅህ፤ ሥራ ስትመራ እንይህ ነበር ጉዱ። ለዛውም ማህበረ ደረጎንን ያህል ፍጹም ጨካኝ ፓርቲ ተሸክመን። ቀሪው ጊዜ ደግሞ እነሱ የአደባባይ ሰው የሚሆኑበት ጊዜ ይሆናል።
ማስታዋል እንደሰጠን አንጠቀምበት ዘንድ ይርዳን ፈጣሪያችን። አሜን።
የኔዎቹ ዛሬ በትዝብት ዙሪያ አቆዬሆችሁ። ርትህ ክፍል ስድስት ቀጣይ ነው … ሰበሮች ይቅደሙ ብዬ ነው።
በተረፈ፤ በተረፋማ ክብረቶቾ ሰላም ሁኑልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ