ልጥፎች

ከማርች 5, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ለአቶ አዲሱ አረጋ ማስተባበያ ጉልበታም ምላሽ።

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ለአማርኛው ደግሞ አስተርጓሚ  አንሻም። ትንሽ እስኪ ደብቁኝ በሉ! ለቅጥፈት ድፍረት አያዋጣም   እና! „አቤቱ በአንተ ታምኛለሁ እና ጠብቀኝ።“ መዝሙር ፲፭ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  04.03.2019  ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ምነው ዛሬ ነፍስ ምርጥ ኦሮሞነት ሆነሳ? እያለቀስኩኝ! ይድረስ ለአቶ አዲሱ አረጋ እንደ ተለመደው ዛሬም ተመልሼ መጣሁኝ፤ ቅጥፈት መሸፈኛ ኮባ ስሌለው። የትርጉም ግድፈት የለበትም። ናዚያዊ ጉዞው ወንጀል መሆኑም እወቁ … ለውጡ መቀልበሱንም ሀምሌ ላይ የጻፍኳቸውን ማንበብ ነው። ከቀልቦሾቹ አንዱ እርሰዎ መሆነዎትን ዛሬ ሳይሆን ትናንት ተናግሬያለሁኝ።   የስሜን አሜሪካ ጉዞ ሞት ነበር ድግሱ እና ስምምነቱ፤ ያ አለመሆኑ ሲታወቅ እገታ ነበር ። ይህን በአንክሮ በተደሞ በሚገባ ጽፌዋለሁኝ። ዶር አብይ አህመድ እሰረኛ ስለመሆናቸው እኔ አሳምሬ አውቃለሁኝ። የሚደንቀው ምንም እንዳልተፈጠረ ወጥተው የሞገቱት ደግሞ ዕውቁ ተዋዳጅ ሊሂቅ "አክ ወሬ" በሚል ፕ/ አለማርያም ነበሩ። ትልቅ የታሪክ ግድፈት ነበር። ቢያንስ ሊሆን ይችላል ብሎ መጠርጠር ከአንድ የፖለቲካ ሊቀ ሊቃውንት የሚጠበቅ ነበር።  ወደ ቀደመው ምለስት ሳደርግ እሳቸውን ሸኝቶ በለማው የ አብይ ልሁቅ መንፈስ መንፈስ ልታስቀምጡ ያሰባችሁት ሌላ መንፈስ ነበር፤ በፈጣሪ እርዳታ ያ ሳይሳካ መቅረቱን ስታውቁ፤ እገታውን አዬን፤ እሰረኛ ነበሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ከዚያ አና ብላችሁ ዓላማችሁን ተያያዛችሁት፤ በቀልና ጩቤ … በግርዶሽ … አቶ አዲዱ እርሰዎ ሲጀመርም ብጣቂ ኢትዮጵያዊ ስሜት የለወትም።  ...