ለአቶ አዲሱ አረጋ ማስተባበያ ጉልበታም ምላሽ።

እንኳን ደህና መጡልኝ።
ለአማርኛው ደግሞ አስተርጓሚ
 አንሻም።
ትንሽ እስኪ ደብቁኝ በሉ!
ለቅጥፈት ድፍረት አያዋጣም
 እና!
„አቤቱ በአንተ ታምኛለሁ እና ጠብቀኝ።“
መዝሙር ፲፭ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
 04.03.2019
 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።

ምነው ዛሬ ነፍስ ምርጥ ኦሮሞነት ሆነሳ? እያለቀስኩኝ!

ይድረስ ለአቶ አዲሱ አረጋ እንደ ተለመደው ዛሬም ተመልሼ መጣሁኝ፤ ቅጥፈት መሸፈኛ ኮባ ስሌለው። የትርጉም ግድፈት የለበትም። ናዚያዊ ጉዞው ወንጀል መሆኑም እወቁ … ለውጡ መቀልበሱንም ሀምሌ ላይ የጻፍኳቸውን ማንበብ ነው። ከቀልቦሾቹ አንዱ እርሰዎ መሆነዎትን ዛሬ ሳይሆን ትናንት ተናግሬያለሁኝ። 

 የስሜን አሜሪካ ጉዞ ሞት ነበር ድግሱ እና ስምምነቱ፤ ያ አለመሆኑ ሲታወቅ እገታ ነበር ይህን በአንክሮ በተደሞ በሚገባ ጽፌዋለሁኝ። ዶር አብይ አህመድ እሰረኛ ስለመሆናቸው እኔ አሳምሬ አውቃለሁኝ። የሚደንቀው ምንም እንዳልተፈጠረ ወጥተው የሞገቱት ደግሞ ዕውቁ ተዋዳጅ ሊሂቅ "አክ ወሬ" በሚል ፕ/ አለማርያም ነበሩ። ትልቅ የታሪክ ግድፈት ነበር። ቢያንስ ሊሆን ይችላል ብሎ መጠርጠር ከአንድ የፖለቲካ ሊቀ ሊቃውንት የሚጠበቅ ነበር። 

ወደ ቀደመው ምለስት ሳደርግ እሳቸውን ሸኝቶ በለማው የ አብይ ልሁቅ መንፈስ መንፈስ ልታስቀምጡ ያሰባችሁት ሌላ መንፈስ ነበር፤ በፈጣሪ እርዳታ ያ ሳይሳካ መቅረቱን ስታውቁ፤ እገታውን አዬን፤ እሰረኛ ነበሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ከዚያ አና ብላችሁ ዓላማችሁን ተያያዛችሁት፤ በቀልና ጩቤ … በግርዶሽ … አቶ አዲዱ እርሰዎ ሲጀመርም ብጣቂ ኢትዮጵያዊ ስሜት የለወትም። 

በሽንገላ ኮሶ ነው የእርሰው ቃለ ምህዳን ማደማጥ ስልችት ብሎናል። የትርጉም ስህተት የለበትም። ማስተባባያውም ስላቅ ነው! መካች ማስረጃ ደግሞ ስላለ እሱኑ ያዳምጡት። ወልቃችሁዋልየኢትዮጵያ ህዝብ ነገን ሳይቀጥር ከቁርጠኛ ውሳኔ መድረስ ይኖርበታል።

ጠ/ሚር አብይ አህመድም ለሳቸው ተብሎ ናዚያዊ ሥርዓት በይፋ ሲታወጅ ሥልጣን እቆያለሁ ቢሉ ክብራቸውን ነው የሚያጡት፤ ምርቃታቸው ነው የሚነሳው። እውነቱን መናገር ያለባቸው ይመስለኛል እቀጥላለሁ ካሉ ያለባቸውን ጫና … ክንብንቡን መግለጥ ይገባል።

ለሉላዊ ዓለም ግልጥ የሆነ መረጃ ሊሰጡት ይገባል። የወቅቱ ጠ/ሚር እኔ ነኝ የሚለውም ተረብ ተግ ብሎ እውነተኛው የመንፈስ ጠላፊ ሊገለጥ ይገባዋል፤ የግል ጉዳይ አይደለም ይሄ፤ ይህ የ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የ አፍሪካ ቀንድም የምስራቅ አፍሪካም ጉዳይም ነው።

·         መነሻ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት በተደረገ የጨፌ ኦሮሚያ የእርቅ ህዝባዊ ሸንጎ፣ አቶ ለማ መገርሳ ከጉባኤው ተሳታፊዎች አዲስ አበባንና ኦሮሚያን አስመልክቶ ለተነሱ ጥያቄዎች የሰጣቸውን መልስ ተከትሎ ብዙ ኢትዮጵያዉያን ከፍተኛ ተቃዉሞ እያሰሙ ነው

·         መከቻ።

Ethiopia: የአቶ ለማ መገርሳ ንግግር ያስነሳው አቧራ ሲፈተሽ | 108 አመቱ ወጣት ጋር የተደረገ ቆይታ

ርዕዮት ሚዲያ ከዶር አብርሃም አለሙ ጋር ባደረገው ቆይታ ምንም የትርጉም ግድፈት ያለነበረበት ስለመሆኑ በድጋሚ ተርጓሚው ያረጋገጡበት ቃለ ምልልስ።

·         የማለዳ ጉዳዬ

መታመን እንደዚህ ዘመን ድንኳን ጥሎ ሀዘን የተቀመጠበት ዘመን ከቶ የለም። መታመን በግፍ የተቀጠቀጠበት ዘመንም እንዲህ ዘመን አይቼ አላውቅም። ቅንነትም እንጥፍጣፊ ሳያስቀር በግፍ የተደፋበት፤ የተደበደበት ዘመን እንደዚህ ዘመን አይቼ አላውቅም። ትህትናም እንዲዚህ ዘመን ፊት የተነሳበት ወቅት አይቼ አላውቅም። ልዩ አክብሮትም እንደዚህ ዘመን  በእርግጫ በጢንባራው የተደፋበት ዘመን እንደዚህ ዘመን አልሰማሁም አላዬሁም። እርግጥ ነው የአማራ ተጋድሎ ሲነሳ በዚህ መሰል ሁኔታ ሰፊ ክብር ፍቅር ትህትና ስስት በገፍ የተሰጣቸው ሊሂቃን ይህን መሰል ግድፈት ሲፈጽሙ አስተውያለሁኝ በ2008። ለዛም ነው ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል ብዬ ክሀሊናዬ የነበረውን ተሰፋ የፋቅኩት፤ እና የተሻለ በምለው ላይ የተጋሁት። 
የእነሱ ግን ውጭ ባለነው በተወሰነው አገር ወዳድ ወገኖች የተሰጠውን ልዩ ፍቅር ነበር፤ ስለዚህ ከዚህ ዘመን ጋር ላመጣጥነው አልችልም። መጠኑ አይገናኝም። ይህ እኮ ሰማይ እና መሬት በጥምረት በሐሴት የሰከሩበት ወቅት ነበር የለማ አብይ የለውጥ ሐዋርያነት። ከሊቅ እስከ ደቂቅ፤ ከከተማ እስከገጠር፤ ከጽንፍ እስከ ጽንፍ መላ አለም በአሃቲ ልቦና ሁለመናውን የገበረበት ልዩ ዘመን፤ ልዩ ታሪካዊ ኤራ ነበር። እንደገና የመወለድ ያህል ነበር።
በዬዘመኑ ለውጥ በመጣ ቁጥር ኢትዮጵያን አጥበቀው በሚጠሏት የኦሮሞ ሊሂቃን ለውጥን በመቀልበስ እንዲህ የሚናፍቃቸውን የታመሰች አገር የማዬት ህልማቸውን ሾከክ እያሉ ያሳካሉ። የትናንቱ እንደሆነው ሁሉ ነው ዛሬም ይሄው በስል ተገብቶ ተደገመ።
በሚሆነው በሆነው ነገር ህልም እስኪመሰል ድረስ ብርሃን ወደ ጭጋግ ተለወጦ ተስፋ እንጦርጦስ ተላከ፤ እንደ ወትሮው ሁሉ ዛሬም ታሪክ እራሱን ደገመ በኦሮሞ ሊሂቃን። ምዕራባውያን እውነታቸው ነበር ፍልስፍናቸው „ኦሮሞ አገር መመራት አይችልም“ የሚሉት። እንዴት እንዳጠናቸው ፍንተው ብሎ የታዬበት ዘመን ይህ ዘመን ነው።
የሆነ ሆኖ እጅግ በበዛ ታማኝነት ኢትዮጵያን ወደ ላቀ ደረጃ ያሸጋግሯታል ብለን ያሰብናቸው፤ ስለጤንነታቸው አብዝተን የምንጨነቀላቻው ዶር ለማ መገርሳ በእኛ ውስጥ እንዳልነበሩ የተረጋገጠበት ማስረጃ በርዮት ሚዲያ በዶር አብርሃም አለሙ ተተርጉሞ መቅረቡ ምክንያት በማድረግ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ ላይ የሰፋ ጥላቻ ያላቸው አቶ አዲሱ አረጋ አንድ ማስተባባያ ይዘው ከች ብለዋል። የዛሬ ጉዳዬ ይኸው ነው።ይህ ማስተባበያ ምን ያህል ምን ስለመሆናቸው ሌላ ሰፊ የሆነ ግብረ ምላሽ ይሰጠናል።
አገር በጠና ታመመች! እኛም!
ባለፉት ሦስት ቀናት እራሴን በጠና አሞኝ ነበር። ወደ ሲዊዝ ከምጣቴ በፊት ከልጅነቴ ጀምሮ ራስ ህምምተኛ ነበርኩኝ። ከዚህ ከመጣሁ ግን ያ ቋሚ የራስ ህመሜ ተገላገልኩኝ። እንዲህ ዓይነት ራስ ህመም አሞኝ ከማያዋቅ ወደ 12 ዓመት ይሆነኛል። አሁን በ ዶር ለማ ንግግር ግን ራስ መርዘኔ ተነስቶብኝ ነው የጠፋሁት አርብ፤ ቅዳሜ እና እሁድ።
ያን ያዳመጥኩት እለት ከራስ ጸጉሬ እስከ እግር ጥፍሬ ነው የተሰነጠቅኩት። ዕንባዬም ፈቃዴን ሳይጠይቅ ነበር የተንዠቀዠቀው። እርግጥ ነው ዶር ለማ መገርሳ ለኦሮሞ የተለዬ የሚስጢር ልብ እንዳላቸው እረዳ ነበር። ይህንንም የስሜን አሜሪካ ጉብኝት ወቅት በሜኖሶታ ያደረጉት የንግግር ቶን ከባዕድ ህዝብ ጋር የቆዩ የሚያስመስል ነበር። በጣም ነበር ያራቁን። የ እውነትም አዝኜ ስለነበር ጹሑፍ ጽፌያለሁኝ በወቅቱ። በተያዬ ጊዜ ያን መሰረት አድርጌ መከፋቴን በስፋት ጽፌበታለሁኝ።
በቅርቡም የኦሮሞ ሊሂቃን በዬዘመኑ „በታላላቅ የመንግሥት ቦታዎች ቢቀመጡም ለኦሮሞ አልጠቀሙም“ ማለታቸውን ሳዳምጥ እኛ ትርፍ መሆናችን፤ የክት እና የዘወትር ሰው እንዳላቸው ተርድቻለሁኝ። በዚህ ጥልቀት ልክ ግን ይሆናል ብዬ ፈጽሞ አላስብም ነበር።
እርግጥ ነው ሁሉም ያለበት ወደ ወገኑ ማድላት ያለ፤ የነበረ፤ ወደፊትም ሊኖር የሚችል ስለሆነ፤ የሳቸው ላቅ ቢልም ያቻችሉታል የሚል ግንዛቤ ስለነበረኝ ይህን መሰል ናዚያዊ መስመር ይከተላሉ የሚል ቅንጣት ጥርጣሬ አልነበረኝም። ፈጽሞ። ተገደው፤ ተጠልፈው የሚለው በሳቸው ዘንድ አይሰራልኝም። ስለምን ለሚለው በጣም የተመሰጠ የኦሮሞነት ጥልቅ ስሜት ስላላቸው። ይህን ግን ከኢትዮጵያዊነት ጋር አቻችለው አመዛዝነው ቢያንስ ቅኖች የለገስናቸውን ያን ተዝቆ የማያልቅ ፍቅር፤ ያን ብጡል ትህትና፤ ያን ሊቅ አክብሮት፤ ያን ሥጋዊ እና ነፍሳዊ መሳሳት፤ ያን አይቶ አለመጥገብ ሲዩ አንጀታቸው ይራራል የሚል ጥልቅ ዕምነት ነበረኝ። አልሆነም
ዛሬ ፕ/ መስፍን አንድ የሀዘን መግለጫ አውጥተዋል። ለእኔ የሐዘን መግለጫ ነው እምለው። እሳቸው እንኳን ሁሉን በመተቸት የሚታወቁት እንሱን „ከሰማይ የተላኩ“ ሲሉ እነ ገዱን ገፋ አድርገው ነበር። የሆነ ሆኖ በዛሬው የሀዘን መግላጫቸው መቋጠሪያ እንዲህ ብለዋል … ዛሬ „የእነ ለማና አብይ አብዮት እተቀለበሰ ነው ለማለት ይቻላል [ይመስለኛል]:: ደግሞ ሌላ ስው ቀልብሶባችው አይደለም:: እራሳቸው [ለማ+ አብይ] እየቀለብሱት ነው:: ”
እኔ ይህ ለውጥ መቀልበሱን ከሐምሌ 19 ቀን 2010 ጀምሮ ጽፌያለሁኝ። በህልሜም ወንበሩ ባዶ ሆኖ ስላዬሁት። ስውሩ መንግሥት ስል ባጅቼ አሁን ግን ግልጽ አድርጌ የአቶ አባ ዱላ ገመዳ ቡድን አቶ ንጉሱ ጥላሁንን አክሎ ስለመሆኑ ግልጥ አድርጌ ጽፌአለሁኝ።
እንደ እኔ የተሸወዱት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ይመስሉኛል። እሳቸውን በኢንሳም ሆነ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር በነበሩበት ጊዜ በነበራቸው ኢትዮጵያን ከፍ የማድረግ ዓላማ መረማመጃ አድርገው እሳቸውንም አስገድደው ወደዚህኛው ጽንፈኛ አመለካከት ለውጠዋለቸዋል ብዬ ነው እማስበው። በውስጣቸው እኔ ኢትዮጵያ እንዳለች አስባለሁኝ። ይህን ሁለት ጽንፍ ለማገናኘት እንደ ድልድይ በጫና ብዛትም ቢሆን ዕድሉን ልጠቀምበት ብለው ያሰቡም ይመስለኛል። ብዙም ተስፋ አልቆርጥም በሳቸው።  በአማራ ላይ  ያላቸው የማይሻሻል የማግለል አቋም አንደተጠበቀ ሆኖ። አንደበታቸው አማራ ላይ ያመዋል። ሌሎችን ማቅረብን ይመርጣሉ። 
የሆነ ሆኖ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድን እኔ የማይበት፤ አቶ አዲሱ አረጋ እና አቶ ካሳሁን ጎፌ እማይበት፤ አቶ ታዬ ዳንአ እና ዶር ነገሬ ሌንጮ የማይበት ዕይታ ለዬቅል ነው። ለእኔ ዶር አብይ አህመድ፤ ዶር ነገሬ ለንጮ፤ አቶ ካሳሁን ጎፌ በኢትዮጵያዊነት ውስጥ እንዳሉ ነው እማስበው፤ ስለምን? 
ከኦዴፓ ማዕካላዊ አመራር አካላት አቶ ካሳሁን ጎፌ ደፍረው ስለ ጠ/ሚር አብይ አህመድ የሚመሰከሩ ቅን ሰው ስለሆኑ። ለዚህም ነው እሳቸው ተገፍተው ጃዋርዊው አቶ ንጉሡ ጥላሁን የፕሬስ ሴክረታሪ ጽ/ ቤት ሃላፊ የሆኑት። አማራ ክልልንም በማመስ እና በማተራመስ ሌላ ትልዕኮ ያላቸው ናቸው እሳቸው። እንቅልፉ ብአዴን አግር ብረቱ - ካቴናው - ሰንሰለቱ የተጠለቀለት በሳቸው አማካኝነት ነው። እንደ ደቡብ ሁሉ አማራን እዬተረተሩት የሚገኙ እሳቸው ናቸው አቶ ንጉሡ ጥላሁን። የጭቃ እሾኽ።
የሆነ ሆኖ  ለውጡ የተቀለበሰው በራሱ በኦህዲድ መስራቾች በእነ አባ ዱላ ገማዳ ነው። ነገር ግን  በአብይ መንፈስ ትክሻ እና የምልዕት ድጋፍ የኦነግን ዓላማ ነው ሁላችንም ደግፈን እንዲሳካ ስንታትር የባጀነው፤ ግድፈቱ ለዚህ ላይ ነው። „አክ“ ወሬ ብለው ዕውቁ ሊሂቅ ፕ/ አለማርያም ሲጽፉ ይህንንም ሞግቼ በወቅቱ ጽፌያለሁኝ።
ለአንድ በሰባዕዊ መብት ለሚታትርም እንቅጩን ነገሬው ነበር። የሚገርመው አሱም በሳምንቱ መደመሩን አዳመጥኩኝ። አቅም አልነበረም ሂደቱን አጥንቶ መፍትሄ ለመሻት። ቢያንስ ለምዕራብውያን ሹክ እንዲል ነበር መረጃውን እኔ የሰጠሁት። ግን እሱም „ የአክ ወሬ“ ማስተባባያ ሰለባ ሆነ እና አገር ገባ።  
በዚህ ሂደት ከሁሉም በላይ ብአዴን ተሸውዷል። ትልቁ የጀርባ አጥንት እሱ ስለነበር። ለዚህ ነው አሁን መሬት እዬያዙ ሲመጡ ብአዴን በምርጫ ለማግለል ሳይችሉ በጉባኤው ሲቀሩ ካቤን ምደባ በይፋ እና በ አደባባይ ወና በመሆነ ዜሮን እንዲታቀፍ ያደረጉት ብአዴንን፤ ከዚህ በተጨማሪ ደቡብ ላይም ሌላ ትርኢት ጀምረዋል የደቡብ አቅምን መበተን። ይህም እዬተሳካላቸው ነው።
አሁን የክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜል መንፈስ አዬር ላይ ተንሳፋፊ ሆኗል። ተቀባይነታቸውም አን አህል ተበትኗል። ሌላ አዲስ ሃይል እዬፈጠሩባቸው ነው። ለዚህም ነው አቶ ሌንጮ ለታን ወደ አዋሳ ኦዴፓ የላኩት ከሲዳማ ጋር በልዩ ሁኔታ እንዲወያዩ፤ በሌላው ሂሳብ ደግሞ ፕ/ መራራ ጉዲናን ወደ አማራ ክልል። ሁለቱም ለኦሮሞ ኢንፓዬር በቀጣይነት አቅም ለማሰበሳብ ነው። በሌላ በኩል ጎንደር ቅስሙ እንዲሰበር 90ሺህ ሰው እንደፈናቅልም እራሱ የለውጥ ሃይል የሚባለው አዛዦቹ ከህወሃት ጋር የሰሩት ትርኢት ነው።
የሆነ ሆኖ ማለዳ ላይ ስለሆነ ሁሉም የሆነው ለኢትዮጵያ መራራ ግን እንደ መልካም ዕድል ይምሰለኛል። ግርጫማ ዕድል ልበለውን? ቢያንስ መደገፍ ከሆነም ዘመነ ኦሮሞ ኢንፓዬርን ለማንገሥ ስለመሆኑ እያወቅን ይሆናል ማለት ነው። አታለው - አባጭለው - አጭበርብረው ሊሆን አይችልም ከእንግዲህ።
የዚህ ሁሉ መከራ ግን ከሊቅ እሰከ ደቂቅ ለአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ የተሰጠው ዕውቅና ምንም መሆኑ ያመጣው ሚዛን የለሽ አቋም ይህን ረግረግ ሸልሞናል። ምን ይደረግ? ብቻ በዚህ ጉዳይ እኔ ዘለግ አድርጌ ስጽፈበት ባጅቻለሁኝ። ሰሚ አልተገኘም እንጂ። የአዲስ አባባ ጭፍጨፋ፤ የኢንጂነር ስመኘው በቀለ ህልፈት እኮ ብዙ የተጠቀለሉ ፖለቲካዊ ዕድምታዎች ነበረባቸው። ፈቺ አላገኙም።
·        ሸንገላና ሸፍጥ።
ወደ ቀደመው ምልስት ሳደርግ „ይሉኝታ ቢሱ ኦዴፓ አዲስ ተርብ ይዞ መምጣቷ „ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት ነው“ የሆነው። ግን አቶ አዲሱ አረጋ በውነት አይቀፋችሁም ወይ ይህን መሰል ሸፍጥ? አያሳፍራችሁንም እንዲህ ዓይነት ናዚያዊ ጉዞ? ወገናችሁ አይሁን ቢያንስ ሰው ናቸው ማለት እንዴት ተሳናችሁ? ቃል እኮ ከባድ ነገር ነው። „ቃል ይተክላል፤ ቃል ይነቅላል፤ ኢትዮጵያ የፈረሰችውም የበቀለችውም በቃል ውስጥ ነው“ ብለውን ነበር እኮ ጠ/ሚር አብይ አህመድ። ምነው በቃላችሁ ውስጥ ለመገኘት አቅም አጣችሁ?

እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ በምን ያህል ክብር እና ልዕልና እንደተቀበላችሁ እስኪ ዩቱብ ገብታችሁ አጥኑት? ግን ህሊና ማለት ይሉኝታ ያለው ሰው ለመሆኑ ምን ቸገር? የሰው ልጅ ከዛ በላይ ፍቅር እና አክብሮት በላይ ምን ይስጣችሁ? ምንድነው ከእኛ የምትፈልጉት? እናንተ በገዢነት እኛ በባርነት? አይሆንም! ! ፈጽሞ!

ያን ያህል ከሃይማኖታችን በላይ እኮ አመናችሁ። ልክ ደንበር ነበረውን ለምስጋናችን፤ ለእምነታችን፤ ለታማኝነታችን? ነበረው ወይ? እንክብካቤያችን እና ትህትናችን ከቶ በምን ያህል ጥልቀት ቀበራችሁት? ሌት እና ቀን የተገናው እኮ ቅን አማራዎች ነበርን ከዬትኛውም ማህበረሰብ በላይ። 

ከዬትኛውም ሚዲያ በላይ ሳተናው ድህረ ገጽ እና እኔ ብዙ በጣም ብዙ ሰርተናል። „ለማዋያን“ ነኝ እኮ አለኩኝ? መደመርን ባልደፍረውም።  ኦነጋውያን ስትሆኑ ደግሞ ጥቁር እለብሳለሁኝ አልኩኝ፤ አደረኩትም። ጥቁር ለብሼ ነው የሰነበትኩት። ዋሾ አልወድም እኔ። ድርጅታችሁ 100 ሚሊዮን ህዝብ ብቻ ሳይሆን ግሎባሉንም ዋሽቷለኝ። ኢትዮጵያን በመጫን እሷን በማፈራረስ ኦሮምያን አገር ለመመሰረት ነው እዬተጋችሁ ያላችሁት። ውጭ ጉዳይን ጠርንፋችሁ የያዛችሁትም ለዚህ መሰሪ ዓላማ ስኬት ነው። የውጭ ጉዞ እና ጉብኙቱ እኮ ከ ኦዴፓ በስተቀር ሌላ ሰው ትውር አይልበትም። አሁን ይልቅ ታማኙን አገልጋያችሁን አክላችሁበታል። 
  • የተደፋ ... 


ያን ይህል ክብር፤ ያን ያህል እልልታ ለኢትዮጵያ ንድት ነበርን? ለራሳችን ቅበረት ነበርን? ለጥቁር ልብስ ናፍቆት ነበርን? ለኢትዮጵያ አራሶች ኡኡታ ነበርን? ከዚህ በላይ ከቶ ምን ይሆን የሚፈለገው? ለለማ መገርሳ ታቦት ይቀርጽ አለን እኮ? ህሊናችን፤ ልባችን ነፍሳችን እኛነታችን - ዘውዳችን - ተክሊናችን - ዕንቋችን እኮ አለን ዘመርን፤ አዜምን። ምን የቀረ የመወድስ ዓይነት አለና ከቶ? ለናዚያዊ ሥርዓት እጮኛነት እረሳችን አሳልፈን ገበርን?

ልበ ክፍትነታችን፤ ቅንነታችን አያስወቅሰነም ሰው ስለመሆናችን፤ ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን ባለህሊና ስለመሆናችን ግን ያረጋግጣል - ያመሳጥራል። ልዩነቱ ይሄው ነው።   

ለመሆኑ በታሪክ እንዲህ ዓይነት ታሪካዊ ንጹህ ፍቅር የትኛው የፖለቲካ ሊሂቅ ነው ያገኘው? ማን? መቼ? ግን እናንተ ልባችሁ ፈጽሞ አይገኝም፤ ህሊናችሁም ንጹህ አይደለም። 

መሬት ለመሬት መሄድ የትም አያደርስም እዮር አለና። እዬር ፍርድና ዳኝነቱን ይሰጣል - ለቅኖች። ዕውነት እንዲህ ተከድታ በጠራራ ጸሀይ የተሰቀለችበት ዘመን አሁን ነው የታዬው። ዕውነትን ቅርጥም አድርጋችሁ ነው የባለችሁት። ማተብ የሚባል አልፈጠረላችሁም። ደግሞ ዝም ማንን ገደለ?! ዝም ብትሉ ከነገማናችሁ ምን አለበት?! አሁን ይሄ ምኑ ይሰተባበላል?

አሁን ይልቅ ባለ ሰባት ምሰሶ አዲስ ትልም ተልማችሁለኝ። ከእንግዲህ የሚሞኝ የለም። ሞኛችሁን ፈላልጉ። ለነገሩ በአዲስ ጃኬት ደግሞ ወደ ሲዳማ ዞር ብላችሁለኝ ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት። ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሜልን አቅም ለመፈታተሽ። 

በዚህ ለውጥ እኩልነት ሰፍኖ ያለ አድሎ የሚታዬው በደልዳላዋ ቀዳማይ እመቤት በወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ቢሮ ብቻ ነው። የእናንተ ነገርማ በበቃን ተከወነ። ከእንግዲህ አይደለም ለአማራ ለኢትዮጵያ ህልውናም እጅግ አስጊ ሁኔታ እንዳለ ነው እማስበው። የአቶ ሊበን ትንቢት „ኢትዮጵያ ካልፈረሰች ኦሮምያ አትኖር“ አዬን።

ዶር ለማ መገርሳ በሳቸው የፖለቲካ ሳይንቲስትነት፤ በሳቸው የሞራል አቅም የሚመጥን ተግባር ላይ አይደለም እየተጉ የሚገኙት። ወርደዋል ቁልቁል፤ ወድቀዋልም። ባለመታደል እሳቸው እኛም ሚስ አደርገዋል። እኛም እሳቸውን ሳንወድ ተገደን ሚስ አድርገናቸዋል። ምንም የመንፈስ ሃዲድ መልሶ አያገናኘም። ዘመን ጥላ ነው ያልፋል። ይህ መሬት የእኛ አይደለም። ለኩንትራት ኑሮ ይህን ያህል ጉድጓድ የሚያስምስ ምንም ነገር አልነበረም።

https://www.youtube.com/watch?v=G7TPLPCLizQ
„Dr. Abiy Mohammed ሕዝብን የሚያረጋጋ ንግግር ተናገሩ

„ኦህዲድ በእድገት ውስጥ ያለ ድርጅት ነው። በርካታ ቻሌንጆች እዬገጠሙት ያነን እዬፈታ የመጣ ድርጅት ነው። ችግር ባይኖር ኖሮ መሰብሰብ ባላስፈለገ ነበር። ኢትዮጵያ የፖለቲካ ችግር ባይኖራት ኖሮ 60/ 70 የፖለቲካ ፓርቲ ባላስፈለገ ነበር። መደማመጥ ስሌለ፤ መስማማት ስሌለ ነው እንጂ 60 ፓርቲ አያስፈልገንም ነበር። ይሄ ችግር ደግሞ የሚፈታው በማኩረፍ አይደለም። የእኔ ሃሳብ ካልተደመጠ ብቻ በማለት አይደለም። በመቀራረብ ነው። ማስተዋል የሚገባን ኦሮምያ 300 ሚሊዮን ህዝብ ማስተናገድ የሚያስችል ፖቴንሻያል አለው። የኢትዮጵያ ህዝብ 100 ሚሊዮን አይሞላም። እንኳን ብሄር ብሄረሰቦች ጁቡቲም፤ ኤርትራም ሱዳንም ቢመጡ በህግ፤ በሥርዓት እሰከ ሰሩ ድረስ አብሮ መኖር፤ አብሮ ማደግ አስፈላጊ ነገር ነው። ዱባይ ያደገችው ውሃ ኢንፖርት አድርጋ፤ አፈር ኢንፖርት አድርጋ፤ ድንጋይ ኢንፖርት አድርጋ፤ ሰውም ኢንፖርት አድርጋ ነው።“

ኦሮምያ ሶስት መቶ ሚሊዮን ይሸፍናል ስንባል አልነበረንም? ምነው አገር ምድሩ አልበቃ አላችሁ? ዘረፋውም፤ ገፈፋውም፤ ወረራውንም ሥልጣኑንም ልትጠግቡት አልቻላችሁም ታሥሮ የባጀ ምንትሶ ሆናችሁ? ሥልጣንም አብሯችሁ የኖረ አይመስልም። ብርቅ ሆነባችሁ ሁሉም ነገር? ትገርማላችሁ። ማለፉንማ … ያ እንዳለፈ ሁሉ ይህም ያልፋል።

„ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው“ በዚህ መሰል በዘገጠ ሃሞትማ ጠቃራ እንዴት ይጠቅለላል? ትንሽ እፈሩ! አንገታችሁን ድፉ! መዋሸት ለክርስትና ጣውንቱ እንጅ ክብሩ አይደለም! ምን ብለውን ነበር „ነፍስ ዜጋ የላትም ብለውን አልነበረንም ዶር ለማ መገርሳ?“ „ሥልጣን ይገልበጥ ኢትዮጵያ ትዳንልን ብለውን አልነበረንም?“ ስንት ዘመን ሊኖሩ ይሆን ዶር ለማ መገርሳ? ምን አደረግናቸው እንዳከበርናቸው ብንዘልቅ ... 

በራስ ወገን ላይ ይህን መሰል የተቀነባባረ ዲስክርምኔሽን? እንዲህ አይደረግም ነውር ነው። ወንጀልም ነው እኮ ይሄ። የእናንተ ገማና ደግሞ የሚገርመው እራሱ ሌላው ቅን ዜጋ ሲራዳቸው ተጎጂዎችን ማዬት እንኳን አትሹም? ምን ዓይነት ፍጥረት ናችሁ? ከቶ ከምን ይሆን የተሠራችሁት? ይህ ነው የኦሮሞ ማህበረሰብ የጉደፊቻ እና የሞጋሳ ባህላችሁን? እንኳንስ ልትረዱ ሰው የሚራዳንም ማዬት አቅም አቅልም አልሰራላችሁም። የሰው ሰው እርዳታ እራሱ ይሰቀጥጣችሁዋል? ለውጡን እዬቀለበሳችሁት ያላችሁት እራሳችሁ ኦዴፓዎች ናችሁ። ፍርሻ የለመደባችሁ ስለመሆኑ ቀደምት የታሪክ አዋቂዎች እዬጻፉት ነው። ደርግም ባልተፈገ አቅጣጫ የነጎደው በዛው እርስ በራሳችሁ በፈጣራችሁት መናቆር ነው? ለመሆኑ ቀድሞ ነገር ትስማማላችሁ እናንተ? ተደማመጣላችሁን? ትዋዋጣላችሁን? 

ያን ጊዜ በወርሃ መስከረም  የአዲስ አባባን መልካም አድራጊዎች የተበቀላችሁት፤  በአደባባይ የረሸናችሁት እኮ ለቡራዩ ተጎጂዎች ስላዘኑ ስለረዱ ነበር። እያንዳንዱ የአካሌ ክፍል ይቆረሳል ይህን መሰል ጭካኔ ሳዳምጥ። እኔ ሴት የካቢኔ አባል ብሆን በፈቃዴ ሥልጣኔን እለቃለሁኝ። ከዚህ በላይ አረመኔነት የለም እና።

Ethiopia : የጠሚ አብይ መንግስት ቤት ያፈረሰባችውን ዜጎች አሁን ከተጠለሉበት ቤተክርስትያን ውጡ እያለ በግፍ ማባረር ጀመረ Abiy Ahmed


አቤቶ አቶ አዲሱ አረጋ ምንም የትርጉም ስህተት የለበትም ዶር አብርሃም አለሙ ደራሽ ፓለቲከኛም አይደሉም። እጅግ እርግጠኛ ሆነው በራሳቸው ፌስ ቡክም ትክክል ስለመሆኑ ሙሉውን ቪዲዮ ለጥፈው መልስ ሰጥተውበታል። ለነገሩ እርስዎ አቶ አዲሱ አረጋን ማለቴ ነው በኢትዮጵያዊነት ውስጥም አልነበሩም፤ ወደፊትም አይኖሩበትም። ኢትዮጵያን የሚያዋት እንደ ጣውንት ነው። 

ስለማን እና ስለምን እንደሚተጉ ቀደሞውንም አሳምረን እናውቃልን። ሞግቼወታለሁም በተለያዬ ጊዜ። ለነገሩ የጠ/ ሚር አብይ ወደ ስልጣን መምጣት አንገብግበዎታል። ልቅው መውጣቸውም አቃጥሎወታል። ይህ አንዱ ህክምና ሊሄዱበት የሚገባዎት ጉዳይ ነው። ቅናታም ነውት።

ብቻ በዚህም በዛም ብሎ እንደለመዳችሁት እንደ ወረሳችሁት ኢትዮጵያዊነት አላጋጣችሁብት። ሚሊዮኑን ቅን መንፈስ ከዳችሁት። ኢትዮጵያዊነትን ማገዶ ነው ያደረጋችሁት፤ የጠ/ሚር አብይ አህመድን ብቃት እና ክህሎትም እንዲሁ የጭራሮ ማቀጣጠያ ነው ያደረጋችሁት፤ በስልታችሁ ሰተት ብሎ ገብቶ የዶግ አመድ እዬሆነ ነው።

በግርዶሽ ነበር የጀመራችሁት፤ ቅኖችን አስነስቶ እንሆ ሰማናው የወል ጉዳችን። እድሜ ለዶር አብርሃም አለሙ። ሌሎች ኢትዮጵያ ሲሉ የነበሩት ሁሉማ የኦሮሞ አክቲቢስቶችማ ተርጉሞው አልነገሩንም ነበር እነ መስፍኔ። ሰሞኑን ድራሻቸው ጥፍት ብሏለኝ።
  
ለእኔ በምርጥ ዜግነት ዶር አብርሃም አለሙ እና ዶር ደረሰ ጌታቸውን በዘመን መሃል የተገኙ ዕንቁዎች መሆናቸውን አረጋግጫለሁኝ። ዶር ጌታቸው ደረሰም ቁልጭ አድርገው በበሰለ በሙያ በበቀለ አምክንዮ ድርጊቱን ገለጥለጥ አድርገው ፓለቲካዊ ዕድምታቸውን ገልጠዋለኝ። በዚህ አጋጣሚ ለሁለቱንም ከፍ ያለ ምስጋና አቀርብላቸዋለሁኝ። ቁስለታችን፤ ምግለታችን አሳታገሰሉን። ፈወሱን። ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ዕውነትን ደፍሮ ያስወግናል። እናንተንም ለዚህ ያበቃችሁ፤ ይህን መሰል የፍቅር ሸማ ያጎናጸፋችሁ ጀግናው ኢትዮጵያዊነት እንጂ ኦሮሞነትማ 40 ዓመት ተዳክሮ በቅንድብ ጸጉርነት ነበር የተወራረደው። አሸናፊው ኢትዮጵያዊነት አንበርክኮ "ሱሴ አስበለ" አሁንም የኢትዮጵያ አምላክ ፍርዱን ይሰጣል። ወላድ በድባብ ትሂድ ... 

·       መኖር ማለት እብለትን የሙጥን በማለት? እእ …  

አቶ አዲሱ አረጋ አሁን ያላችሁ ይመስላችሁዋልን? በዘነዛናቸውሁን ነው የቆማችሁት፤ ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል እና። በቃችሁ ውሸቱ! በቃችሁ ማስመሰሉ! በቃችሁ ሽንገላው! በቃችሁ በኢትዮጵያዊነት ሥም መነገዱ!

አብሶ ብአዴንን ከዳችሁት። ብአዴንን አንጋላችሁ አርዳችሁ አቃጣላችሁ ነው የሞቃችሁት። ለዚህ አጋፋሪው ደግሞ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ናቸው። በታሪክ እንዲህ ዓይነት ሸፍጥ ተከውኖ አያውቅም። ከሊቅ እስከ ደቂቅ አቄላችሁት። ግን መስሏችሁ ነው። መሬት አፈር ናት። ፍርድና ዳኝነት ደግሞ የእዮር ጉዳይ ነው። ሰው ምን አቅም አለው፤ በመከራ የደቀቀቀን ህዝብ ተበቀላችሁት ፍቅር በሰጠ በበቀል በቋሳ በተስፋ ማጣት አንገረገባችሁት።

ይህም ሆኖ ደግሞ የሚገረመው ማስተባበያው ነው። ለዚህ ምንም ማስተባባያ አያስፈልገውም። አማርኛ ቋንቋ የአፍ መፍቻ ቋንቋችን ነው። ትርፎም ይናኛል። ባለቅኔነቱን ማን ወስዶብን ነው አስተርጓሚ የሚያስፈልገን? አስተርጓሚ አያስፈልገንም። ቀጣዩ እንግዲህ ፍላጎታችሁን በጠበንጃ ለማስፈጸም እንደምትተጉ እንጠብቃለን። 

አሁንም በለጋጠፎ ለገዳዲ የመረጃ ጋዜጠኛን ደብድባችሁል። ነገ ደግሞ በመርዝም በአፈናም ቀጣዩ ዕዳ ይወራረዳል። ለዚህ ነበር እኔ ከቆሞስ ኢንጂነር ስመኛው በቀለ ህልፈት በኋዋላ አገር እንገባለን ሲባል በቁጠባ ይሁን ያልኩት። 

የሆነ ሆኖ ጥጋብን በልክ መያዝ ይገባል። እናንተ ዘመነኞች ናችሁ። ግን ዘመንተኞችን የሚቀጣ ንጹህ አምላክ ደግሞ እንዳለ አትርሱ፤ በበረድ፤ በተባይ፤ በመሬት መራድ፤ በቃጠሎ፤ በአውሎ በብዙ ነገር የሚቀጣ። ክህደት አያበረክትም። ካዳችሁት 100ሚሊዮን የኢትዮጵያ ህዝብን። አማራንም ጎንደር ላይ ቀጥታችሁታል። ያ ሆን ተብሎ ታቅዶ የተከወነ ነው። ንጹህ የ ኦሮሞ ማህበረሰብን ቅራኔ ውስጥ ሰተት አድርጋችሁ ከተታችሁት።  

በጄኒራሎቻችሁ እና በአቶ ንጉሡ ጥላሁን አጋፋሪነት ጎንደርን አሳምራችሁ ቀጣችሁት " የ ኦረሞ ደም ደሜ ነው ስላለ፤ በቀለ ገርባ መሪዬ ነው ስላለ" ለዛ ማዘናጊያ ደግሞ ሌላ የሊቃውንት ጉባኤ ደግሞ አካሄዳችሁ? ብቻ ታያችሁ ዓመት ሳይሞላ አላስችላችሁ ብሎ ስትቁነጠነጡ …

ክብር ሞገስ ይሁን ለዶር አብርሃም እና ለዶር ጌታቸው ደረሰ አሁን የጨለማው ጉዞ አክትሞ ፊት ለፊት ተጋጥማችሁዋል- ከቅኑ ኢትዮጵያ ህዝብ ጋር። ወረራ ጀምራችኋዋል ቀጥሉ … ይመርባችሁ … እኛም በጸሎት እንተጋለን መቼስ ተስፋ አታግኙ ተብለን የተረገምን ሰዎች ነን እና።

እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድን ብሆን ግርዶሹን ገልጬ ወጥቼ ሥልጣኔን እለቅ ነበር፤ ያው ናዚያዊ መንፈስ ለሚያሳብደው ለአንዱ አስረክቤ በሥሜ ግን ኢትዮጵያን የሚያጠፋ ጉዳይ ሲፈጸም ማዬትን እጠዬፈው በነበር … ለምኑ? ለዬትኛው ጊዜ? 

ቀድሞ ነገር አብይ መንፈሱን የተቀበለው ሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንጂ  የኦሮሞ ማህበረሰብ አይደለምና … ወደፊትም አይሆንም። ቢያንስ በቅደመ ሁኔታ የተያዙትን ጉዳዮች ገልጦ መናገር ይጠበቅባቸዋል ጠ/ሚር አብይ አህመድ እቀጥላለሁ ካሉ። በስተቀር በፍቅሩ ልክ ድንጋይ፤ የበሰበሰ እንቁላል አይቀሬ ነው። ንግዱ በሳቸው ሥምም ስለሆነ „ወራጅ አለ“ ማለት ይገባል እንደ ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ …

ግርባው ብአዴንም ለጥ ብሎ ያደግድግላችሁ ለሎሌነት ነፍሱ ከሳፈራችው፤ ኢትዮጵያም እንደፈረደባት ውስጧ ተከፋፍቶ እምትሆነውን ነገር አማኑኤል / አላህ ይሁናት

 … ግን ትንሽ ለመደበቅ ሞክሩ … ሃፍረት ይኑራችሁ! … ያን መሰል ጉዳይ ወንጀል መሆኑን እወቁ፤ የሰብዕዊ መብት ረገጣ መሆኑ እመኑ! በተባበሩት መንግሥታት  የሰብዕዊ መብት ህግጋትም የሚያስጠይቅ። ስለምን ይሆን ዓለም ናዚን ያወገዘው? እስኪ አደብ ግዙ እና ታሪኩን መርምሩት አካሄዳችሁ መሰል ስለሆነ …

እኔ ብርቱ ታታሪ ደጋፊያችሁ እራሱ ስለ እናንተ እምነተቢስነት አቅም አጥቼ 3 ቀን በሱባኤ ነው የሰነበትኩት። አላዛሯ ኢትዮጵያም አሳዝናኝ … መከራ ተሸካሚዋ አገሬ ብቻ ሳትሆን ድምጽ አልባዎቹ የኢትዮጵያ እናቶችን ያሳዝኑኛል … ቢያንስ እፈሩ! … ቢያንስ ተደበቁ! ከሚዲያም ተሰወሩ …! ሚዲያችሁ የሚተዳደረው እኮ በጸረ ኢትዮጵያ በተካነ ነፍስ በጀት ተደመድቦለት ጎበለል እያለ ነው። የናንተው ደግሞ በዛ ... 

 … አንድ ሰው ሁለት ሰው ሊዋሽ ሊጭበረበር ይቻላል እናንተ እኮ ግሎባሉንም አለም እኮ ነው እንዲህ አዬር ላይ መና ያደረጋችሁት … ግን አይቀፋችሁም?

·       ለቅኖች ለአውነት ደጋፊዎች እንደ መከወኛ።

የኔዎቹ ኑሩልኝ!ይህም ለመልካም ነው። በዚህ መከራ ጀርባ ሌላም ክብር ይኖራል። በዚህ ዶፍ ውስጥ ቅኖች ነጥረው ይወጣሉ። እኔ በጠ/ሚር አብይ አህመድ መንፈስ ውስጥ እቀባ እገዳ እንደተጣለበት ነው እማስበው ከሐምሌ ወር ጀምሮ ከስሜን አሜረካ ጉዞ በሆዋላ፤ የሰይጣን ጆሮ ይደፍን እና ሞተውላቸው ቢሆን ኖሮ ሊያደርጉት ያሰቡትን ነው እያሳዩን ያሉት ብዬ አስባለሁኝ።

ነገር ግን እሳቸው „አለባብሰው ቢያርሱት ባረም ይመለሱ“ ነውና ነገሮችን ገልጠው መናገር ይኖርባቸዋል። ሞትም ቢሆን መሰዋት ነው። ምክንያቱን በሳቸው ድጋፍ ለኦነግ መሥራት ወንጀል ነውና። ለ ኢትዮጵያ አንጡራ ጠላት እንዴት ድጋፍ ይደረጋል? 

ከኢትዮጵያዊነት በላይ አብይን መውደድ አይቻልም። ሰው አላፊ ነው አገር ነዋሪ ነው። ስለመካከለኛው ምስራቅ አፍሪካ ጉዳይ ሳይሆን አሁን ስለ ኦሮምያ እና ስለ ኢትዮጵያ ቀጣይ እጣ ፈንታ ቁጭ ብሎ አደብ ገዝቶ ፍርጥ አድርጎ መወያዬት ግድ ይላል። ደጋፊም፤ ተከታይም ከምንም ከማንም በላይ ኢትዮጵያን ከሚያጠፋ፤ ለሚያፍልስ መንፈስ ቅንጣት አቅም ማባከን ያለበት አይምሰለኝም“ አክ ወሬ“ አወዳደቁ አላማረም። ህዝብን ይዞ ገደል ነው የገባው ...  

ስንት መንፈስ በዛ ጹሑፍ አንደተዘናጋ፤ አዋዜ ሳይቀር ያን አጉልቶ አውጥቶ ስንት ሰው መስመሩን እንደሳተ ይታወቃል። በዚህም ስንት ወራት እንደተቃጠለ፤ ስንት ነፍስ እንደተፈናቀለ አደብ ገዝቶ መመርመር ይገባል።

ብልህ ሙሴ ኢትዮጵያ ማግኘቷ ላዛውም በኦዴፓ ድምጽ አግኝቶ ፈተና ነው። የተቀርኖው ምንጭ ይሄ ነው ቢገባን። ያለፈው አልፏል። አሁን ግን አደብ ገዝቶ ሁሉም ወደ ቀልቡ ተመልሶ ሁሉም ከሰከረበት ሐሴታዊ መንፈስ ወጥቶ በአንክሮ፤ በአርምሞ እውነትን ወግኖ መቆም ግድ ይላል።

ብአዴን ግልጽ የሆነ አቋሙን፤ ደቡብም ግልጽ የሆነ አቋሙን ለማሰለፍ አስቸኳይ የማዕከላዊ ኮሜቴ ስብሰባ ሁሉ የሚያስፈልግ ይመስለኛል። በቄሮ ትግል ነው ለድል በቃን የሚሉት ጸረ ኢትዮጵያ ሃይሎች። ስለሆነም ድላችን በኦሮሞ አገርነት ይረጋገጥ ነው ትግሉ፤ አብይም የወጣኸው የተመረጠከው በዚህ ተጋድሎ ነውና ይህኑኑ አስፈጽም ነው። ዶር ብርሃነመስቀለ አበበ እኮ ገልጠው ተናገረዋል "አብይ የኦነግ ወራሽ ነው" ብለው።

የፈለገ ነገረ ቢደረግላቸው አይረኩም። እነሱ አዲስ አበባን ዋና መናገሻ ከተማቸው አድረገው ኦርምያ አገርን መመስረት ነው። ጨዋታው ይሄው ነው። ለዚህ እንቅፋት የሆነ ሁሉ ይከላል። ይህ ካልሆነ ደግሞ በኦሮሞ ኢንፓዬር በናዚያዊ እርምጃ በመንግሥት ሃይልና በጀት ይቀጥላል ነው።

 ይህ ደግሞ እንደ ሰው ሆኖ ሲታሰብ ቀን ሊሰጠው የማይገባው ጉዳይ ነው። ምከሩ ወገኖቼ። ድርጭት ሆነው አብረው ሲዘክሩ የባጁትም የህውሃት እና የአማራ መገለል እንጂ እንዲህ ዓይነት መከራ ይመጣል ብለው ያሰቡበት ጉዳይ አልነበረም ተፎካካሪ የሚባሉት አብሮ አደሮች። 

በሌላ በኩል ጠ/ሚር አብይ ከመነሻቸውም የአማራ ብሄርተኝነትን ተቃውመው በመነሳታቸው የልብ ተገኜ ብለው አብረው ሲዶሉቱ ነበር የባጁት የልቦቹ የተፎካከሪ ድርጅት ሊቀመንባርት ምርጥ ዘሮች፤ አሁን ግን ቀስ እያለ እራስንም ማጣት ግድ ይላል።

 በጨፌው ስብሰባ ግልጽ የሆነ አቋም ነበር የተንጸባረቀው። ጉዳዩ ገፋ የተደረገበት አካል አለ። መስከረም ላይም ፍንጩ ነበር። አላዬነም አልሰማነም ካልተባለ በስተቀር ፍቅሩ ያለቀ ይመስላል። አይዋ አማራ ቅንነቱ እንዲህ ነው ... 

የሆነ ሆኖ ትናንትም እውነትን እንጂ ጭብጨባን የማትጠጉ ወገኖች ዛሬም እውነትን ወግኖ አገር የማዳን ታሪካዊ ድርሻ ፊት ለፊት አፍጧል። አብሶ አማራ ታገድሎውን መቀጠል አለበት። አማራ ዘመድም ወገንም ረዳትም የሌለው ግን ፈጣሪ ያረሳው ነውና ሚዛኑን ለማስጠበቅም ትልቁ ክንድ ያለው እሱ ዘንድ ስለሆነ እጅግ በበሰለ፤ በረጋ፤ ከስሜታዊነት በራቀ ሁኔታ እራሱን በሁሉም መስክ እስከ መጨረሻው ደረጃ ማሰናዳት ይኖርበታል። ቀደም ባለው ጊዜ ብአዴን ማጠናከር እንደ አንድ ስትራቴጂ አዬው ነበር።

ብአዴን አቶ ንጉሡ ጥላሁን እስካቀፈ ድረስ ግን አማራ ከጃዋርያን ጋር መወገን አገርን የመገደል ያህል ስለሆነ፤ ኦነግን የመደገፍ ስለሆነ አቅምን አላግባብ ማበከን ከቶውንም አይገባም። አብን አጠናክሮ መቀጠል ግድ ይላል። 

አብን ደግሞ በማስተዋል መጓዝ ይኖርበታል። ከኦሮሞ የመንግሥት ግዛት ጋር አላስፈላጊ እሰጣ ገባ ማቆም ይጠበቀብታል። ወጀብን ዝቅ ብሎ ማሳለፍ። ከብአዴን ጋርም ቢሆን  ከአቶ ንጉሡ ጥላሁን ባሻገር ባሉ ጉዳዮች በብልህነት መራመድ ይገባል። አቶ ንጉሡ ጥላሁን ለኢትዮጵያም ግማድ ናቸው። ለለውጡም ፍዳ!
 
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው!


ማለፊያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።