ልጥፎች

ከጁን 21, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

እኔ እንጂ ...

ምስል
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 22.06.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። „እኔ ዛሬ ብቀበል አንተም ነገ እንደምትቀብል እወቅ።“ (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፳፪)                        ሰማይን ሳይ …                     አሱም እኔን ሲያይ                  እንዳልደርስበት - እርቆ              የተፈጠረ - ተመርቆ           ሁሌ ላይ ሆኖ ልቆ።        ታች ሆኖ - መች ደቆ እንዳይመጣልኝ - መች ሥራ አጠቶ?! ተግበረ ቢሷ - እኔ እንጂ …..  በሰጠኝ ጸጋ - ዕንባ አውራጂ …     በግፍ ሠራዊት ተነጂ …      ጠላቴን የማልከካ በመጂ …        መከራዬን የማልቀቅል በመገፈጂ።  ተጣፈ።        ሀምሌ 2 ቀን 2002 ዓ.ም ሻፍሃውዝን ሲዊዘርላንድ 2002 ተስፋ መጽሐፌ ላይ ገጽ 15። ሆኼሃት ፈቃድ ነው እርሱ። ስለዚህ እንደ ፈቃዳቸው ነፃነታቸውን ሳልጫን ከፈለጉበት ቦታ ጭብጣቸው ይቀመጣል። ትንሽ ፈንገጥም ወጣም ያለ ነው። እያነበብኩኝ ስለምጽፈው ምቱ ዜማ ነው ቦታውን የሚሠጠው ...  ትሁቶቹ ታዳሚዎቼ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

ናፍቆቴን ለማን ልስጥ?

ምስል
    … ለማን   ...  ?              ከሥርጉተ  ©  ሥላሴ 22.06.2018 (ከገዳሚዋቷ ሲዊዘርላንድ።)                           „ኃጢአትን ተዋት እደ ልቦናህን አቅናከኃጢያት ሁሉ አንጻ።“                               (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ  ፴፰ ቁጥር ፲) ናፍቆቴን ለማን ልስጥ?      ስስቴን ለማን ልስጥ?         እንደ ወጣሁ፣ ብቀር …                 … እንደ ተዘጋ በር።                       በፍልሰት ብቀበር? አደራ አውጪው ማን ነው?!                            ማንስ ነው ተረኛው?!                        ዬት ላይ ላስቀምጠው!?                የሚወስደው ማን ነው?! አንገት አንጀት ያለው! ተፃፈ።    ሀምሌ 2 ቀን 2002 ዓ.ም   ቪንተርቱር /ሲዊዘርላንድ/ ተስፋ መጽሐፌ ላይ ገጽ 15።   ፎቶ ምንጭ ጉግል።  ቅኖቹ ክብረቶቼ ኑሩልኝ - አክብሪያችሁ። መሸቢያ ጊዜ። 

የተስፋ ጣዝማ!

ምስል
ከሥርጉተ  ©  ሥላሴ 22.06.2018 ከጭምቷ ሲዊዚዬ                    "የደጋግ ሰዎች ልጆች ስሙኝ በረድኤት ታደሱ፤ አበባ በምድረ በዳ ጠል                      እንዲአብብ እንደደሱ አብቡ"(መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ  ፴፱ ቁጥር ፲፫)        የተስፋ ጣዝማ             የእ ማማ                ማዛማ                   ለዛማ                          ውብ ሸማ                                    ልዩ ግርማ                                              ወርቃማ                                                       ረርጣማ! ሀምሌ 5 ቀን 2002 ዓ.ም ቪንተርቱር፤ ተስፋ መጽሓፌ ላይ ገጽ 14።  የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

የንብ ዓውራ!

ምስል
ከሥርጉተ  ©  ሥላሴ 22.06.2018 (ከገዳማዊቷ ቅድስት ሲዊዝዬ።)          „ዳግመኛ አስቤ እናገራሉሁኝ።“ ( መጽሐፈ   ሲራክ   ምዕራፍ፴፱   ቁጥር   ፲፪ ) ድረስ በቶሎ …. አደራ!                  አንተ ብራ ሁሉን ግራ። ሚስጢር እንዲመራ እኔነት እንዲያፈራ … ። ማንነት እንዲያበራ ….                               ለይ ጎራ፤ ሕዝበ ጠቀም የንብ ዓውራ! ተጣፈ።   ጥቅምት 4 ቀን 2002 ዓ.ም  ክላይነአንደልፊንግን /ሲዊዝ/ ተስፋ መጽሓፌ ላይ ገጽ 10። ምስጋና ለጹሑፌ ታዳሚዎች።  ጌጦቼ እጅግ አድርጌ ከልቤ ከነፍሴም እወዳችሁአለሁኝ።  ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

የብርሃን ቃል!

ምስል
             ከሥርጉተ  ©  ሥላሴ 22.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንደ።)                  ጥበብስ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች።                         (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ፴፱ ቁጥር ፩) ቃል - ቃል - ቃል - ቃል - ቃል ፍስ ----- ስ     ፍስ ------- ስ                 ምል -------- ስ               ቅልስ የማይል             ቃል ልበ ወርቅ - ሰንደቅ ድን ----- ቅ             ዳማ ------ ቅ        አፍለቅልቅ             ብር --------- ቅ የማይሰርቅ - የማያሰርቅ     የማይር ---------------- ቅ        የሚዘል ----- ቅ              የሚያዘል --------- ቅ !                    ፍልቅልቅ የሃቅ ልቅ - የሚያደምቅ      የሚ - ያስፈልቅ፡           የሚናፈቅ                   የማይረቅ                         ወርቅ ያልሆነ ብርቅርቅ - ቅብ ድቅድቅ።         የኪዳን ማሰሪያ ውል የአባት አደሩ - ድልዳል የዕምነት ዕዳ ጓል ቃል ቃል ቃል - ቃል ቃል ቃል ይውላል ያድራል ከተግባር - ቤቱ፣ ከቃል።                                                    መታሰቢያነቱ ... ለንጉሦች ንጉሥ ለአፄ ቴወድሮስ ግንቦት አንድ ቀን 2001 ዓ . ም ሄርሽን ሆቴል ሲዊዘርላንድ ተስፋ መጽሐፌ ላይ ገጽ 10። የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።

ረዳት / ፕ ነብዩ ባዬ ሹመት የብዕር የነፃነት አዋጅ ነው - ለእኔ።

ምስል
ለረዳት ፕ / ነብዩ ባዬ የሎሬቱ  ዓይን የትወፊት ዘብ አደር።     ከሥርጉተ - ሥላሴ 21.06.2018 (ከመንኩሲያዋ ሲዊዘርላንድ) „ ጽዮንም ሆይ ለአምላክሽ እልል በይ፤ የደጅሽን መወርወሪያ አፅንቷልና   ልጆችሽንም በውስጥሽ ባርኳልና መዝምሩ ዳዊት ምዕራፍ“ (፻፵፯ ቁጥር ፪) ·        እፍታ ጥበብ አለፈላት። የእውነት ጥበብ አለፈላት። አብይ ኬኛ! ላይ ለሥነ - ጥበብ ሰዎች ዶር አብይ አህመድ የተለዬ ልዩ አቅም እንዳላቸው ገልጬ ጽፌ ነበር። ከሥነ ጥበብ ቤተኝነታቸው ከፖለቲካ ሊቃን የተለዬ ጸጋም እንዳላቸው ጽፌ ነበር። በዛን ጊዜ ጥሪዬ ይህን መንፈስ የሥነ ጥበብ ቤተኞች ድጋፍ ለማሰባሰብ ነበር ሃሳቡ። መቼም እግዚብሄር ይስጣው ሳተናውም ተባብሮኝ ሃሳቤን ለቅንች አድርሻለሁኝ። አንድ ሙሴ ሲመጣ ተጠቃሚው በሚገባ ሊውቀው ስለሚገባ ነበር ዘርዝር አድርጌ እስከ ክፍል ስድስት የሠራሁት። ባለቅኔው ጠ/ ሚር ለሥነ ጥበብ ቤተኛ ናቸው። ሚስጢሩን ያውቁታል። ሰው የሚታነጽበት ጥበብ ያለው ከዚህ ማህጸን ነውና። ውዶቼ   ከሥር ተጨማሪ ነገሮችን አክላለሁኝ እስከ ምርኩዙ።   ዛሬ አንድ ዜና ስከታታል ታላቅ የምሥራች ሰማሁኝ። ዘመኑ የሎሬቱ ነው ብዬም በተለያዬ እርሰ ጉዳይም ጽፈያለሁኝ፤ ዛሬም እምለው ይህንኑ ነው። በጥበብ ውስጥ ሰው መኖር ሲፈቅድ ጥበብን ንጽህናዋን ተቀብሎ ነው። የዛሬው የነፃነት ቀን የብዕር እና የብራና፤ የመድረክ እና የድምፆዋ የነፃነት ቀን ነው። ·        ጥበብ እና ነፍሷ! ጥበብ ምቀኞችን አትወድም። ከሁሉም በላይ ጥበብ ምቀኝነትን ትጠላለች ትጸዬፈውማለች። ከሁሉም በላይ