ናፍቆቴን ለማን ልስጥ?
… ለማን ... ?
ከሥርጉተ © ሥላሴ 22.06.2018 (ከገዳሚዋቷ ሲዊዘርላንድ።)
„ኃጢአትን ተዋት እደ ልቦናህን አቅናከኃጢያት ሁሉ አንጻ።“
(መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፲)
ናፍቆቴን ለማን ልስጥ?
ስስቴን ለማን ልስጥ?
እንደ ወጣሁ፣ ብቀር …
… እንደ ተዘጋ በር።
በፍልሰት ብቀበር?
አደራ አውጪው ማን ነው?!
ማንስ ነው ተረኛው?!
ዬት ላይ ላስቀምጠው!?
የሚወስደው ማን ነው?!
አንገት አንጀት ያለው!
- ተፃፈ።
ሀምሌ 2 ቀን 2002 ዓ.ም
ቪንተርቱር /ሲዊዘርላንድ/
ተስፋ መጽሐፌ ላይ ገጽ 15።
- ፎቶ ምንጭ ጉግል።
ቅኖቹ ክብረቶቼ ኑሩልኝ - አክብሪያችሁ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ