ልጥፎች
ከሴፕቴምበር 5, 2024 ልጥፎች በማሳየት ላይ
የማከብራችሁ ጉግል ላይ ለተወሰደ ፎቶ ጉግል ራሱ እያጠፋው ነው። ሃክ ብሎጌ እንደሆን አላውቅም።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#ቸር አስበን #ቸር እንሁን። #ቅን አስበን #ቀና እንሁን።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
#ቸር አስበን #ቸር እንሁን። #ቅን አስበን #ቀና እንሁን። መጪው ዓዲስ ዓመት የሰላም፦ የምህረት፤ የፍቅር እንዲሆን ፈጣሪን እማፀነዋለሁኝ። በቃችሁ እንዲለን። የማያስማማንን #ክፋ #ሃሳብ አስወግዶ እንደ አንድ የአገር ልጅ በአንድ ቅዱስ #ማዕድ እንታደም ዘን አማኑኤል ይርዳን። አሜን። #አይዞን ። #አይዞን ። ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ያልፋል። #አይዞን ። ተስፋችን አምላካችን። ተስፋችን አላኃችን። ደህና ሁኑልኝ። ደህና ሰንብቱልኝ። አይዞን። ኑሩልኝ። አሜን። በምዕራፍ 14 እስክንገናኝ ድረስ ደህና ሁኑልኝ። አሜን። ትህትናችሁ ሁልጊዜ ቁሞ ያስተምረኛል። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። አሜን። በእሰው እጅ ያሉትን ወገኖቻችን እንሰብ አንርሳ። ሰው ባይከተለን አቤቱታችን አምላክ ያዬዋል። ይዳኛዋል። ዋጋውን እሱ በመፍትሄ በክብር ያስከብረዋል። ከቻላችሁ ብቻ ሳብስክራይብ አድርጉ። እግዚአብሄር ይስጥልኝ። https://www.youtube.com/channel/UCJEQXw86u_NG4A1FVC1j2qg Sergute©Selassie ሥርጉተ©ሥላሴ Kebebushe L/work Media ደህና ሰንብቱልኝ። አሜን። ኑሩልኝ። አሜን። ሥርጉትሻ አገልጋይ2024/09/05
ትውልድ እና መንግሥት በምን ይጣመሩ? የህዝብ ውዴታ ወይንም ፈቃድ ሸቀጥ አይደለም። አየሩ #ያቃሰተ #ማቃት ላይ ነው።
- አገናኝ አግኝ
- ፌስቡክ
- X
- ኢሜይል
- ሌሎች መተግበሪያዎች
ትውልድ እና መንግሥት በምን ይጣመሩ? የህዝብ ውዴታ ወይንም ፈቃድ ሸቀጥ አይደለም። አየሩ #ያቃሰተ #ማቃት ላይ ነው። የምዕራፍ 13 ማጠናቀቂያ ፁሁፍ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" ትውልድ እና መንግሥት በምን ይጣመሩ?? " #ይጣመሩ " ከባድ ኃይለ ቃል ነው። ግን ይደፈር። መድፈር ተስፋን የሚገናኝ ወይንም #የሚያቀራርብ ከሆነ። ትውልድ እና መንግሥት መጣመር ቀርቶ ለመቀራረብ ጋዳ ሆኗል በኢትዮጵያ ፖለቲካ። ምክንያት ……… #የዕውነት ፤ #የመርህ ፤ #የኃላፊነት ፤ #የተጠያቂነት ውህደት አራባ እና ቆቦ ስለሆነ። #ትዝብቴን በስሱ …… 1) አንድ ሥርዓት በስሜት የሚመራ ከሆነ? 2) አንድ ሥርዓት በቅጽበታዊነት የሚተዳደር ከሆነ? 3) አንድ ሥርዓት ጭካኔን ምራኝ ካለ? 4) አንድ ሥርዓት ለህዝብ ዋስትና ለመስጠት አቅም ካነሰው፦ 5) አንድ ሥርዓት በገባው ቃል ልክ መሆን ከተሳነው፦ 6) አንድ ሥርዓት በፋንታዚ የሚጋልብ ከሆነ፦ 7) አንድ ሥርዓት ምን ግዴ ከሆነ፦ 8) አንድ ሥርዓት የሚመራውን ህዝብ አክብር መነሳት ከአቃተው፦ 9) አንድ ሥርዓት ከማድመጥ ዲስኩር ካዘወተረ፥ 10) አንድ ሥርዓት ለዕውቀት ደንታ ቢስ ከሆነ፦ 11) ሰው ወጥቶ በሰላም መግባት አቅቶት ሞት የዕለት ጉርስ ሲሆን፦ 12) አንድ ሥርዓት የትውልድን ውስጥ ማወቅ ከቸገረው፦ 13) አንድ ሥርዓት ለህዝብ ዕንባ ደንታ ቢስ ከሆነ በትውልዱ እና በእሱ መካከል ያለው የውስጥነት ሃዲድ #እክል ይገጥመዋል። እክሉ #የፖለቲካ #ኢንፍሌንሽን ይገጥመዋል። ይህን ጊዜ አናርኪዝም ያቆጠቁጣል። አሁን በኢትዮጵያ እኔ እማስተውለው ይህን ነው። በኢትዮጵያ ፖለቲካ የተሻለ ዕድል ያገኘው ክስተት #ጭካኔ እና #አረማዊነት ነው። ሰውኛ እና ተፈጥሯዊነት ተሰደዋል ወይንም ተ...