ልጥፎች

ከጃንዋሪ 12, 2019 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ዝበት ወይንስ ስክነት?

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዝበት ? ስክነት ? „በዓመታት መካከል ትታወቅ፤  በማዓት ጊዜ ምህረትን አስብ“ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        ማነው ጥፈተኛው? ማነውስ ይቅርታ ጠያቄውስ? https://www.youtube.com/watch?v=a7aWV6r9Q6k&t=3s ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በሚነሱ ግጭቶች ላይ የምሁራን አስተያየት Fana Television Published on Jan 10, 2019 ጋዜጠኛ አቶ አዳም ታደስ /አወያይ/ ·        ማካሄጃ። "ፕ /" አባባው አያሌው በአማራ ቴሌቪዥን አሁን ከሆነ ይቀርባሉ ለቃለ ምልልስ፤ ያው እሳቸው የሚፈ ለጉ ት የአማራ ብሄርተኝንት ጎልቶ ሲወጣ ወይንም ዩንቨርስቲዎች ችግር ተከሰተ ሲባል ብቻ ነው። ከዚህ ያለፈ፤ ከዚህ ከፍ ያለ ቦታ ላይ ተወክለው አይተን አናውቅም። ሌላው ቀርቶ ከታሪክም ከጥበብም አንጻር ብርቱ ሰው በሚያስፍልጋቸው አገራዊ ጉዳዮችም እንዲሁ ያን የመሰለ በፍጹም ሁኔታ የሚመሰጠው ብቃታቸው እዬባከነ ነው የሚታዬው የተገባውን ቦታ አላገኝም እንደማለት። ውጭ ያሉ ሊቃናት አገር እንዲገቡ ሲፈለግ አገር ውስጥ ላሉት ሊቃነት ያላቸውን አንጡራ ሃብት ጥቅም ላይ ለማዋል ያለው ዕድምታ ፈተናው አይሎ አያለሁኝ። መሰረታዊ ምክንያቱ ብቃት አቅም እውቅት ሳይሆን መለኪያው የፖለቲካ ድርጅት አባልነት ስለሆነ፤ የኮታ ጉዳይ ስለሆነ፤ ይህ ብቻ ነው እንዳልል ደግሞ ከዚህ የወጡ ሹመቶች እና ዕውቅናዎች ሲሰጡ ደግሞ አያለሁኝ፤ ...

ዝቅዝቅ ቁንዳላ!

ምስል
 እንኳን ደህና መጡልኝ።  ዝቅዝቅ ቁንዳላ! „ ምንም እንኳን በለስም ባታፈራ፣ በወይን ሐረግ ፍሬ ባይገኝ፣   የወይራ ሥራ ቢጓል እርሾችም መብልን ባይሰጡ በጎችም ከበረት ቢጠፉ ላሞችም በጋጥ ውስጥ ባይገኙ   እኔ ግን በ እግዚአብሄር ደስ ይለኛል፤ በመዳህኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ። “ ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፯ ቁጥር ፲፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከእመ ዝምታ - ሲዊዘርላንድ። ·        ጠብታ የኔዎቹ አዱኛዎቼ እንዴት አላችሁልኝ? እኔ አምላኬ ክብሩ ይስፋ ይንሰራፋ ደህና ነኝ። ለዛሬ የመረጥኩት ቃለ ወንጌል የመከራ ወጀብ መቋቋም የሚያስችል የህይወት መንገዴ ነው። ቤተሰቦቼ የሥርጉተ ንብረት ይሉታል። አዎን የመንፈስ እርስቴ ነው።  በዚህ ቃለ ወንጌል አስተምህሮ ተስብሬ ሳልወደቅ፤ ግራቀኝ የማዕበል ሸክሙን፤ የመንፈስ ጭነት ቁሩን እና ሃሩሩን አደላድዬ እና አስመችቼ አስደስቼም የቅዱሱን ሰማዕት የወንጌል አርበኛውን የሐዋርያው ጳውሎስን „የይበቃኛል“ ምህንድስና ምራኝ ብዬ በሙሉ ሰብዕና፤ በሙሉ ሞራል፤ በሙሉ መንፈሳዊ አቅም በተፈጠርኩበት ልክ እና ቁመና መኖርን ደስ ብሎት እንዲኖር የተፈቀደበት ታላቅ የህይወቴ ክፍለ አካል ነው። ዛሬ ላለው እርእሴ የመረጥኩበት ወሳኝ ጉዳይም ስለአለ ነው። ·        እፍታ። ዛሬ ቅዳሜ ነው። ብራ ነው። ግን ጸጥታው ገኖ ወጥቷል። እናም ዛሬ ልሠራ ያሰብኩትን ጉዳይ ተግ አድርጌ እነሆ እናንተን አገኝ ዘንድ ወደድኩኝ። ቀደም ባለው ጊዜ ጉዳዩን አንስቼ በሳተ...