ልጥፎች

ከኖቬምበር 12, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ከዶር ለገሰ ቱሉ ዘለፋ፤ የአቀራረብ ዝበት፤ የኃላፊነት ዝንፈት፥ ዬችሎታ ኩስመት ፥ የሰብዕና ክሳት ሌላው ከዚህ ...

ምስል

SAVE LALIBELA .

ምስል
 

"እሱበእሱ ድርድር ለክፋ ቀን የተቀመጠው የጫካው ኦነግ የኢትዮጵያመሪ ሆኖ ሊመጣ? አይሰማ ጉድ የለም ።

ምስል
  እሱበእሱ ድርድር ለክፋ ቀን የተቀመጠው የጫካው ኦነግ የኢትዮጵያመሪ ሆኖ ሊመጣ? አይሰማ ጉድ የለም ። "የመከራን ቀን ዝም ብዬእጠብቃለሁ።" (ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍም፫ ቁ ፲፯) አንድ አብይዝም ከራሱ ጋር ሽብሩን ይደራደራል። "ከንቱ የከንቱ ከንቱ።" ጠቅላይ ሚር አብይአህመድ በርከትከት ያሉ ሥውር ታጣቂወች፤ አፋኞች አላቸው። አዲስ አበባም አፓርታማ አላቸው ይህን መሰል ጉዳይ የሚያስፈፅሙበት። #ህገ ወጡ 1) ቄሮ ለማፍያ ተግባር የተመረጡትን ብቻ ይመለከታል። 2) ፎሌ 3) አባቶርቤ 4) "ሸኔ" የጫካው የኦነግ ክንፍ በሙሉ መረጃ እና ሎጅስቲክ ኢትዮጵያን ዘነዘናዋን ያስቀረው። ይህ ህገ ወጡ አደረጃጀት ነው። #ህጋዊው 1) ልዩ ኮማንዶ 2) ሪፓብሊካን ጋር ከአሜሪካ የተወረሰ፤ 3) ልዩ ኮማንዶ ከራሺያ የተቀሰመ ይመስለኛል፥ 4) ኢሊት ሠራዊት ከእስራኤል በቀጥታ የተቀዳ፤ የተኮረጄ፦ 5) የኦሮምያልዩ ኃይል፤ አሁን አሁን ደግሞ ከአማራ ፋኖ መግነን ጋር የኦሮምያ ሚሊሻም አይቅርብን ብለዋል፦ ቅናቱም ያብተከትካቸዋል። 6) መደበኛው ዬኢትዮጵያ የፖሊስ ኃይል የቀደመው ባህር፤ ምድር እና አዬር ኃይል አላቸው። 7) በደህንነቱ ዘርፍ ኢንሳን ጨምሮ በሲቢሉ፤ በወታደራዊው በሙሉ አቅሙ አለ። የህገ ወጡም፤ የህጋዊውም ጠቅላይ አዛዡ ሌኮ/ አብይ አህመድ ናቸው። ሁሉንም አቅደው ለተፈለገው የሽብር ተግባር ያሰማራሉ። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ትናንት የተፈጠረችው ደቡብ ሱዳን ሳትቀር ክንድ እንለካካ እያለች ነው። በባዕታችን ወረዳም ሰይማለች።ስሜን ሱዳንም ጦርነቱ ገታት እንጂ አና ብላ ገብታ ለም መሬታችን አፈራጣ ይዛለች። እንዲያውም ሱዳን እርስበርስ ጦርነት ባይኖርባት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቅጣቱን በጎንደር በኩል ያንዶለ

#መንግሥታዊ #አናርኪዝም።

ምስል
#መንግሥታዊ #አናርኪዝም ። "ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።"   የጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ መተንፈሻ ቧን ከኦሮሞ ሊቃናት ውጪ አይታሰብም። ፈፅሞ። ከሰሞኑም አንድ የኦሮሞ ሊቅ የጽህፈት ኃላፊ አድርገው ሹመዋል። ማንን ፈርተው። ሃግ የሚል የለም።እራስ እግሩ እሱበእሱ። የ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ዶር ሙላቱ ተሾመ በምንም አግባብ እና በምን ውክልና እንደሆን አይታወቅም በዬቦታው ተኮፈውሰው አያለሁኝ። የኢትዮጵያን መንግሥት ወክለው በሁሉም መስክ አራጊ ፈጣሪ ናቸው። በዘመነ ህወሃት ስለመኖራቸው ቱክም ሹክም ሳይሉ የኖሩት ዶር ሙላቱ ተሾመ በተመሰጠረ ሥልጣን አክቲብሊ እዬተሳተፋ ነው። ማን ተፈርቶ? ማንስ አለና። ሞቅ ሞቅ ሲላቸው ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ አሊ ለሚያለዙት፤ ለሚያደነዙዙት ተከታዮቻቸው " #ኦሮሞ እና አማራ ቁጥሩን ለውጊያ ያውለው" እያሉ ያባጭላሉ። እሳቸው እራስ እግሩን የራሳቸውን ወገኖች ሃብት ማማ፤ ፖለቲካ ማማ፤ አህጉራዊ እና ሉላዊ ዕውቅና መንበር ላይ አስቀምጠው። የማይቀረው ነገር ግን ይህ ዘመናይነት ይቀደዳል። እሱ ባለው ዕለት። #ያለለት ። መኖሩም መትነኑም ያልተነገረለት ከ98% በላይ የሆነው የኦህዴድ ኦነግ ፓርላማ ይህን መሰል አናርኪዝም ጉዞ ፀጥ ረጭ ብሎ በዝምታ ሙሉ ድምፁን ይሰጣል። መብቱ ተጥሶ የፈለገ ነገር ተከውኖ አጽድቅ ሲባል በሁካታ እና በጥድፊያ #እያውካካ ያፀድቃል። "ነገርን ነገር ያነሳዋል" እንዲሉ ጋዜጠኞቻቸውን የሸኙት የኢትዮጵያ ህጋዊ ፕሬዚዳንት ወሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ ግን አሉ? ወይንስ ዶር ሙላቱ ናኙበት። ለመሆኑ ተመለሱ? ለነገሩ ምን አገባን እኛን። ለበይ ተመልካችነት እንኳን ያልተፈቀደልን ዘመናይነታቸውን እንኳን ማዬትም መብት አይደለም ተብሎ ሠርክ በድ

እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ከአናርኪዝምሥርዓት የሚጠበቅየሽግግር የፍትህሥርዓት ዬለም።

ምስል
  እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ከአናርኪዝምሥርዓት የሚጠበቅየሽግግር የፍትህሥርዓት ዬለም። "በውኑ እግዚአብሄር በወንዞች ላይ ተቆጥቷልን?" "ቁጣህ በወንዞች ላይ መዓትህም በባህር ላይ ነውን?" (ዕንባቆም፫ ቁ ፰)     ህግ ተፈፃሚነቱ ህግ ከሚያውቅ አካል ነው። ህግ ተከባሪነቱም ህግን ከሚያውቅ አካል ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ህግ ናት ሥል ተፈጥሯዋን እንጂ በትውስት ርዕዮት የሚዳክረውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማለቴም አይደለም።    የኦነግ መሠረቱም፤ ድልዳሉም፤ ሂደቱም ዘሃ ግራውም #አናርኪዝም ነው። ይህ ማህበረ አናርኪዝም በእኛ ሰው አማኝነት ዕድሉን ሰጥተን እንሆ በፍርስራሻችን ላይ ሃዘን ላይ እንገኛለን። ይህ ቢቀር ይህ ይሻላል የማይባለው በዴሞግራፊ ፋሺዝምን በኢትዮጵያ እዬተረጎመ የሚገኘው ኦነግ መራሹ ሥርዓት ህግም፤ ተፈጥሮም፤ ኤቲክስም ሞራልም ያዩኛል ብሎ የማያስብ ዝልኝ መንፈስ ነው። ከተፈጥሯዊነት ውጪም ነው። በጭካኔ እና በጥላቻ በማን አንሼ መንፈስ ነው የተፈጠረው። ካለ ጭካኔ መሽቶ አይነጋለትም። ሥርዓት ተለወጠ ሲባል ጃኬቱን እዬቀያዬረ ተስፋ ተቀቀለ።    ኦነግ መነሻውም መድረሻውም ጭካኔ እና አረመኔነት፤ ጥላቻ እና የሰውን ልጅ ከክብሩ ዝቅ አድርጎ የሚጨፈላለቅ ማት ነው። በእያንዳንዱ ቀን ከመርዶ ዜና በስተቀር ያልተተረፈበት የሥልጣን ዘመን በወንጀልም የዘለበ ነው። የተቋማት መኖር ብቻውን የሚፈይደው የለም። "የአሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ" እንዲሉ ከዚህ ሥልጣን ላይ ካለው ስብስብ የስኳር ቆቆር ታክል ፍትህ አይጠበቅም።   ጊዜም፤ ወረትም መንፈስም ሊባክን ፈጽሞ አይገባም። ቁርጥ ያጥጋባል ይላሉ ባለ ቅኔወች ጎንደሮች ሲተርቱ። እንቁረጥ። እግዚአብሄር ሊያደርግልን እንደሚችል እናምናለን። ፍትህ ግን ከፋሺዝም ሊታሰብ ፈፅሞ አይ