እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ከአናርኪዝምሥርዓት የሚጠበቅየሽግግር የፍትህሥርዓት ዬለም።
እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ከአናርኪዝምሥርዓት የሚጠበቅየሽግግር የፍትህሥርዓት ዬለም።
"በውኑ እግዚአብሄር በወንዞች ላይ ተቆጥቷልን?"
"ቁጣህ በወንዞች ላይ መዓትህም በባህር ላይ ነውን?"
(ዕንባቆም፫ ቁ ፰)
ህግ ተፈፃሚነቱ ህግ ከሚያውቅ አካል ነው። ህግ ተከባሪነቱም ህግን ከሚያውቅ አካል ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ህግ ናት ሥል ተፈጥሯዋን እንጂ በትውስት ርዕዮት የሚዳክረውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ማለቴም አይደለም።
የኦነግ መሠረቱም፤ ድልዳሉም፤ ሂደቱም ዘሃ ግራውም #አናርኪዝም ነው። ይህ ማህበረ አናርኪዝም በእኛ ሰው አማኝነት ዕድሉን ሰጥተን እንሆ በፍርስራሻችን ላይ ሃዘን ላይ እንገኛለን። ይህ ቢቀር ይህ ይሻላል የማይባለው በዴሞግራፊ ፋሺዝምን በኢትዮጵያ እዬተረጎመ የሚገኘው ኦነግ መራሹ ሥርዓት ህግም፤ ተፈጥሮም፤ ኤቲክስም ሞራልም ያዩኛል ብሎ የማያስብ ዝልኝ መንፈስ ነው። ከተፈጥሯዊነት ውጪም ነው። በጭካኔ እና በጥላቻ በማን አንሼ መንፈስ ነው የተፈጠረው። ካለ ጭካኔ መሽቶ አይነጋለትም። ሥርዓት ተለወጠ ሲባል ጃኬቱን እዬቀያዬረ ተስፋ ተቀቀለ።
ኦነግ መነሻውም መድረሻውም ጭካኔ እና አረመኔነት፤ ጥላቻ እና የሰውን ልጅ ከክብሩ ዝቅ አድርጎ የሚጨፈላለቅ ማት ነው። በእያንዳንዱ ቀን ከመርዶ ዜና በስተቀር ያልተተረፈበት የሥልጣን ዘመን በወንጀልም የዘለበ ነው። የተቋማት መኖር ብቻውን የሚፈይደው የለም። "የአሳ ግማቱ ከጭንቅላቱ" እንዲሉ ከዚህ ሥልጣን ላይ ካለው ስብስብ የስኳር ቆቆር ታክል ፍትህ አይጠበቅም።
ጊዜም፤ ወረትም መንፈስም ሊባክን ፈጽሞ አይገባም። ቁርጥ ያጥጋባል ይላሉ ባለ ቅኔወች ጎንደሮች ሲተርቱ። እንቁረጥ። እግዚአብሄር ሊያደርግልን እንደሚችል እናምናለን። ፍትህ ግን ከፋሺዝም ሊታሰብ ፈፅሞ አይገባም። አቅማችን መጥኖ ማስተዳደር የዊዝደማችን ዋዜማም ነው። ለዚህ ነው ብዙውን ነገር እንዳላዬሁ እማልፈው። "ሙያ በልብ።"
ይህን የምጽፈውም ምን አልባት ቅኖች ከኖሩ ተስፋቸውን #ካልሆነ ቦታ ካለ አድራሻው እንዳያስቀምጡ ለማስገንዘብ ነው። ባለፈው እንደፃፍኩትም አገራዊ ምክክሩ ያሉ ወገኖቼን ባከብርም እሱም የጨነገፈ ትጥቅ አስፈቺ አዳንዛዥ ዕፀ ፋሪስ ነው። ዒላማው አማሎ አልቦሽ ለማድረግም ነው። በጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ የሴራ ቸረቸራ የተጠመቀ ማናቸውም መንፈስ ለኢትዮጵያ እና ለኢትዮጵያዊነት #ሳንክና #ብክልም ነው። ከሳቸው የሰናፍጭ ታክል የምጠብቀው የተስፋ ታዛ የለም። ኢትዮጵያ ለሳቸው ጥንችል ናት። መሞከሪያ ጣቢያ። ያልሻ።ጀማመሩት፤ ያልወጠኑት የድጥ ዓይነት የለም።
ይልቁንም ቀናቸው ደርሶ ከተሰናበቱ ከአሁኑ የከፋ ወንጀል ይፈፅማሉ በማለት #ስጋቱ #ሊገድለኝ ነው። ሰውነታቸው ሁሉ እዬተነነ እንደሚሄድ አስባለሁኝ። እኔ እንዲያውም መጽሐፈ ሄኖክ የወደቁ መላዕክት የሚላቸው አሉ። የዛ መንፈስ እስረኛ እንደሆኑ ይሰማኛል። የሊቀ ፒኮክ አምላኪ ናቸውና።
ነገረ ሥራቸው #ከእኛ #ለእኛ የሆነ አይደለም። ዝም ብላችሁ አጥኗቸው። መርምሯቸው። ቃናቸው አዲስ ቅይጥይጥ ያለ ትርጉም የለሽ ፋንታዚ መሞከሪያ ጣቢያ ኢትዮጵያ እና ህዝቧን ያደረጉ በደል ለመፈፀም #የማይደክሙ፤ ለፍርሻ ትጉህ እና ታታሪ፤ ለአዛኝነት እና ርህርህና ልግመኛ ሰው ናቸው።
የበጋ ስንዴ የሚሉት ማንን እንዲዋጋላቸው ይመስላችኋል። ጤፍን። ለዚህ ነው ዓራት ዓይናማው የጎጃም ገበሬ በማዳበሪያ ማዕቀብ የተቀጣው። በድሮን በኤሊኮፍተር ሰርክ የሚጨፈጨፈው። ምርት ማሳ ላይ በደቦ የሚያቃጥሉ፦ ትራፊው ለከብቶች መና እንዳይሆን የሚታገሉ፤ ንፁኃን እንሰሳት በገፍ የሚረሽኑ? ከእነኝህ ፍትህ??????
ስንት ነገር ተቀደደ?
ስንት ነገር ተተረተረ?
ከስንት ቁም ነገር ተፈቅዶ ተፈሰሰ??? ማለቂያም የለው።
ሲጠቃለል
#ሀ፦ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ከሥርዓተ አልበኛ መንግሥት የወጣ ስለሆነ ከመፈጠሩ በፊት ሬሳ ሁኋል።
#ለ፦ የሽግግር ፍትህ ከአሸባሪ እና ከቀውስ ፋፍሪካ የሚጠበቅ ህጋዊነት እና የርትህ ልዕልና የለም።
የእኔ ውዶች አብረን ቆዬን። ካለቀልኝ አውዲዮው እለጥፋለሁኝ። በስተቀር ደህና እደሩልኝ። ተስፋችን አምላካችን ብቻ ነው።
"ህግ ተላላፊወችን ጠላሁኝ።"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/11/2023
ፍትህ ከተፈጥሯዊነት ሥርዓት እንጂ ከፋሺዝም አልጠብቅም።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ