"እሱበእሱ ድርድር ለክፋ ቀን የተቀመጠው የጫካው ኦነግ የኢትዮጵያመሪ ሆኖ ሊመጣ? አይሰማ ጉድ የለም ።

 

እሱበእሱ ድርድር ለክፋ ቀን የተቀመጠው የጫካው ኦነግ የኢትዮጵያመሪ ሆኖ ሊመጣ? አይሰማ ጉድ የለም ።
"የመከራን ቀን ዝም ብዬእጠብቃለሁ።"
(ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍም፫ ቁ ፲፯)
አንድ አብይዝም ከራሱ ጋር ሽብሩን ይደራደራል።
"ከንቱ የከንቱ ከንቱ።"
May be an image of 2 people and beard

ጠቅላይ ሚር አብይአህመድ በርከትከት ያሉ ሥውር ታጣቂወች፤ አፋኞች አላቸው። አዲስ አበባም አፓርታማ አላቸው ይህን መሰል ጉዳይ የሚያስፈፅሙበት።
#ህገ ወጡ
1) ቄሮ ለማፍያ ተግባር የተመረጡትን ብቻ ይመለከታል።
2) ፎሌ
3) አባቶርቤ
4) "ሸኔ" የጫካው የኦነግ ክንፍ በሙሉ መረጃ እና ሎጅስቲክ ኢትዮጵያን ዘነዘናዋን ያስቀረው። ይህ ህገ ወጡ አደረጃጀት ነው።
1) ልዩ ኮማንዶ
2) ሪፓብሊካን ጋር ከአሜሪካ የተወረሰ፤
3) ልዩ ኮማንዶ ከራሺያ የተቀሰመ ይመስለኛል፥
4) ኢሊት ሠራዊት ከእስራኤል በቀጥታ የተቀዳ፤ የተኮረጄ፦
5) የኦሮምያልዩ ኃይል፤ አሁን አሁን ደግሞ ከአማራ ፋኖ መግነን ጋር የኦሮምያ ሚሊሻም አይቅርብን ብለዋል፦ ቅናቱም ያብተከትካቸዋል።
6) መደበኛው ዬኢትዮጵያ የፖሊስ ኃይል የቀደመው ባህር፤ ምድር እና አዬር ኃይል አላቸው።
7) በደህንነቱ ዘርፍ ኢንሳን ጨምሮ በሲቢሉ፤ በወታደራዊው በሙሉ አቅሙ አለ።
የህገ ወጡም፤ የህጋዊውም ጠቅላይ አዛዡ ሌኮ/ አብይ አህመድ ናቸው። ሁሉንም አቅደው ለተፈለገው የሽብር ተግባር ያሰማራሉ። የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ትናንት የተፈጠረችው ደቡብ ሱዳን ሳትቀር ክንድ እንለካካ እያለች ነው። በባዕታችን ወረዳም ሰይማለች።ስሜን ሱዳንም ጦርነቱ ገታት እንጂ አና ብላ ገብታ ለም መሬታችን አፈራጣ ይዛለች። እንዲያውም ሱዳን እርስበርስ ጦርነት ባይኖርባት ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ቅጣቱን በጎንደር በኩል ያንዶለዱሉት ነበር። ነገር ቤርሙዳ ትርያንግል እንዲህም፤ እንዲያም ነው።
#ነገረ ምርጫ እና የሽብር ስኬቱ መቋጫነት።
ምርጫው በህጋዊ ሂደት ተፈጠመ የሚሉ አሉ። እኔ ግን አልተቀበልኩትም። ያ ሁሉ መንግሥታዊ ሽብር አደራጅተው እና መረተው ህዝባችን እንዲሰጋ፤ እንዲርድ አድርገው ያላገጡበት የእርግጫ እና የፍጥጫ ሂደት ነበር። Dዲሞክራሲ ዱብ አለ ተብሎም የዲፕሎማሲው ማህበረሰብ ዶላሩን ሆጪ አድርጎ ደግፏል። የምርጫ ቦርድ ልዕልታን መሃያቸው በዶላር ነው አሉ።
የሆነ ሆኖ በሽብር ነበር ምርጫ የተከወነው። አጣዬ በተደጋጋሚ ነዳ፤ ሻሸመኔ ሽዋ ሮቢት ዝዋይ አርሲ ነገሌ ተረምጠው። የአማራ ልጅ ተረሽኖም፤ ታፍኖም ታስሮ በገፍ። ባልደራስ እስኪበቃው ተወቅቶ። ይህን መሰል ትራጀዲ ለመፈፀም ነበር ይህ ሁሉ አሸባሪ ስውር ተቋማት በገፍ ዬተደራጁት። ኢሊት እና የባህር ኃይል ከሚለው ውጪ ያሉት በሙሉ አቅም እና ጉልበታቸው #ሽፍታው #የኦነግ #መንፈስ ህጋዊ ዕውቅና በምርጫ እንዲያገኝ ያስደረገ እጅግ ሰቅጣጭ ሂደት ነበር።
ከፍተኛውን ሮል የተጫወተችውም ወት ብርቱካን ሚዲቅሳ የወቅቱ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ነበረች። ሥርዓተ አልበኝነት ኢትዮጵያን እንዲመራት ተፈረደባት። አሁን ዓላማዋን ካሳካች በኋላ ደግሞ ለሌላ ተልዕኮ ለቀቅኩ ማለቷን አድምጫለሁ። ኢትዮጵያተቀብራ አፈር መልበሷ ሲረጋገጥ።
በኦነግ የጫካው ቡድን የተፈፀመው ከቅንጣቱ እስከገዘፈው አመክንዮ፤ ዘረፋ፤ ማፈናቀል፤ አፈና፤ ግድያ፤ የአማራን ዘር የማፅዳት ዘመቻ ሁሉም በስምምነት ከአራት ኪሎው ኦነግ ጋር የተፈፀመ ነው። ሲበቃቸው ይህን እንደሚያደርጉ የታወቀ ነበር። ኦነግ ከኤርትራ ሲገባ ተመሥጥሮ ከዚህ ተደረሰ። እዬገደለ የሚገድለው የአብይዝም መንፈስ አሳቻ ነው እምለውም ለዚህ ነው። ቤርሙዳ ትርያንግል እምለውም ለዚህም ነው።
ጠቅላይ ሚሩ ወንጀሉን ያቅዳሉ፤ ያደራጃሉ፤ ያከፋፍላሉ። አንዳንዱ ቲም ግዳጁን ከተወጣ በኋላ ወደ #ውጭ ይላካል። ወይንም ወደ ሰላማዊ ህይወት እንዲመለስ ይደረጋል። ዳጎስ ካለ ድጎማ እና ሹመት ጋር። ለምሳሌ ቲም ዶር አንባቸውን የጨፈጨፈው ኮማንዶ ደግሞ አልታዬም። የአርቲስት ሃጫሉንም ማንሳት ይቻላል። በመላ ኦሮምያ እና ቤንሻንጉል ሙሉ ፭ ዓመት የተፈፀመው ሽብር እና ስኬቱ ፈፃሚ እና አስፈፃሚወቹ በህግ በማይጠዬቁበት ሁኔታ ነው ተሰውሮ የሚቀረው። አንድም ሰው በህግ ፊት አልቀረበም። ከዛሬው በባሰ ነገ የወንጀለኛ አመራር ሰፍኖ በቀል ሲቸረቸር እናያለን።እኛ እስከተኛን ድረስ። ነቀላው በሁሉም መስክ ነው።ዴሞግራፊው በሁሉም ዘርፍ ነው። ዳር ደንበር ወሰን የለውም። ምንጠራ ላይ ናቸው።
አሁን ደግሞ ያ አረመኔእና ጨካኝ ቡድን ዓለም ዓቀፍ ዕውቅና ተሰጥቶት እራሱ በራሱ እራሱን #እያደራደረ ይገኛል። ይሳካልም ብዬ ነው እማስበው። የሚፈለገውን የአማራ እርድ ፈፅሟል። ኦርቶዶክስ ተዋህዶንም ፈትኗል። ኢትዮጵያንም ትቢያ አጎናጽፏል። ምን የቀረ ነገር አለና። የቀረው ፋሲል ግንብ፤ አክሱምእና ላሊበላ ናቸው። እነሱም ቀን የሚጠብቁ ናቸው እያልኩ በተከታታይ ስጽፍ ነበር። አዲስ አበባም አይሆኑ ሆና ማቅ ለብሳ ኩርምትምት ብላ በጠላት ሥር ወድቃለች።
#HR 128 ናልኝ እባክህ ውዴ
የርህርህና ገዴ
ተቆርቋሪ ጓዴ። May be an image of 3 people and beard
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
10/11/2023
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።
ለሥርነቀል ለውጥ እንትጋ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።