ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 24, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጋንቤላ ምርጥ ልጆቹ ለጋንቤላ ህዝብ መፍትሄው ናቸው!

ምስል
ጋንቤላ ምርጥ ልጆቹ ለመፍትሄው ቁልፍ ናቸው።  „አንተ ለእኔ መሸሸጊያ ነህ ከጣርም ትጠብቅኛለህ፤ ከከበቡኝ ታድነኝ ዘንድ ደስታዬ ነህ“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፩ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ©ሥላሴ 24.99.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ።   ·          እ ፍታ ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ። አንድ አስተያዬት ተልኮልኛል። እኔ እኮ በደረቅ ወንጀል ላይ እርምጃ መወሰዱ የተጋባ አይደለም ማለት አለንበረም ዕይታዬ፤ ፖሊስ የተደራጀበት ምክንያት እኮ ለህግ አስፈጻሚነት ነው።  እንዲያውም ይህን መሰል እርምጃዎች እምፈልጋቸው ናቸው። በወጣቶች ቀረጻ ላይ ልዩ አትኩሮትም ስለ አለኝ። ነገር ግን አሁን ስለምን ይህ ወቅት ተመረጠ ብቻ ሳይሆን የቀደመው የላፍቶ ከተማ ፖሊስ ቢሮ መግለጫ እና የአሁኑ አዲስ አባባው ኮሚሸነር መግለጫ አልተገናኘልኘም። ቶኑም አልተመቸኝም።  መረጃው ልጥ እና ልሙጥ ነው የሆነው። የሆነን አካል ወንጀል ለመሸፈን ተብሎ የተሰናዳ ነው - ለእኔ። እጅግም ዘግይቷል።  ሌላው ለወንጀልኝነት ለናሙና የቀረቡት ጎንደር፤ ወሎ እና አርባምንጭ ደግሞ ጉዳዩን ስለምን እንዚህ ከተሞች ላይ ወንጀለኞች ቀረቡ? ሌሎች ከተሞች ወንጀለኞች የሉንም ያሰኛል፤ ለዛውም የሰው ልጅ ተገድሎ ተዝቅዝቆ ተሰቅሎም እያዬን ነው። ይህን ሁሉ መፈናቀል እና ዝርፊያም ኦሮምያ ላይም እያዬን ነው።  ይህ እውነቱን ለማናገር ጓደኛ ፍለጋ ብቻ ሳይሆን በቀጣይ በእንዚህ ከተሞች ሆን ተብለው ስትራቴጅካዊ የማጥቃት ትልም እንዳለ ያሳያል። በጠቅላላው ለእኔ ታማኝ መረጃ አይደለም። መረጃውም ወጥ አይደለም። ...

የአዲስ አባባ ኮሚሸነሩ ጣሪያ የነካ መታበይ።

ምስል
ዝል ዝል። እምምምምምምም! „ተቸግሬያለሁ እና አቤቱ ምራኝ፤ ዓይኔም ከሃዘኔ የተነሳ ተፈጀች፤ ነፍሴም ሆዴም።“ መዝሙር ፳፱ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ 24.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·        መግቢያ። ምነው እታለም በአብይ ጨከንሽ አለችኝ አንዲት የዶር አብይ አህመድ አድናቂ እህቴ። የመጨከን አይደለም ዕውነትን የመወገን ነው። ሌላውም ይቅር ቅን የፖለቲካ ሊሂቅ ማግኘት ለ አላዛሯ ኢትዮጵያ የሰማይ ስጦታ ነው። እንኳንስ ሁሉ ያለው ሰብዕና። ችግሩ እንደ ቀደመው ጊዜ ከሥራ ሃላፊነት ሁሉንም ነቅሎ ሥር ነቀል ለውጥ አለመካሄዱ፤ እንደገናም የምናውቀው የውጭ አገሩ ፖለቲካ ካለልጓም በዝርግ እልፍኝ መለቀቁ ነው። እናም የህግ የፍትህ ዝበት ሲኖር መግለጽ የተገባ ነው። መንፈሱን ይታደጋዋል፤ በሌላ በኩል ነፃነት ሆነ ዴሞክራሲ የሂደት ውጤትን ነው። ካለትችት የግል ኑሮም ንጥረ ነገር ይጎድለዋል። አሁን ስለምጽፋቸው ከፍተኛ መኮነን ምስላቸውን እንቅስቃሴያቸውን ብቻ በማዬት በበቀል እንዴት እንደሚንተከተኩ፤ እንዴት እንደሚወድቁ እንደሚነሱ፤ ምድር እንዴት እንደጠበባቸው ስታዩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ያለባቸውን ወስብስብ ችግር መረዳት ያስችላችኋዋል። ለምሳሌ አቶ ተከለ ኡማን ተመልከቷቸው በሚሊዬነም አዳራሻ፤ የግንቦት 7 አቀባባል፤ እና የኦነግ አቀባባል ሰብዕናቸው ተለዋዋጭ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ምን ያህል እንደተገለባባጡ እና የልዩ የሆነ ወገናዊ ፍቅር እንዳለባቸው መስጥረው መያዝ ይችሉ ነበር እሳቸውን ሪኮመንድ ያደረገውን አካል እንዲህ በአደባባይ ከሚያጋልጡ። የምናከብራቸው አቶ ታዬ ደንአም እንዲሁ። ስለዚህ ሹመቱ የሰጣቸውን መንፈስ እና ጉዳዩን በምልስት እንድን...

መርህ ራሱን ስላማይጥስ ያክመኛል።

ምስል
መርህ የሚመራት አገር ትናፍቀኛለች። „መተላለፉ የቀረችለት ሃጢአቱ የተከደነችለት ምስጉን ነው፤“ መዝሙር ምዕራፍ ፴፩ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 24.09.2018 ከጨምቷ ሲዊዘርላንድ። አዱኛዎቼ እንዴት አላችሁልኝ? አማን ነውን? ዛሬ ዛሬማ ለመርዶ መንፈሴን አዘጋጅቼ እዬጠበቅኩኝ ነው። ድንገተኛ አደጋ ወይንም በሰው እጅ የተሰራ መከራ … ባጀብን>>   አገር ህዝብ፤ ህዝብም አገር ነው። አገር ትውልድ፤ ትውልድም አገር ነው። ታሪክ አገር፤ አገርም ታሪክ ነው። ትውፊት አገር፤ አገርም ትውፊት ነው። አገር ትሩፋት፤ ትሩፋትም አገር ነው። አገር ነባቢት፤ ነባቢትም አገር ነው። ወገን አገር ነው፤ አገርም ወገን ነው። ማንነት አገር፤ አገርም ማንነት ነው ለመነሻ … መርህ መራሽ አገር ትውልድን ቀርፆ አገር ለማሰረክብ ዋንኛው መንገድ ነው። መርህ ተከታይ ትውልድ ፈተናን የመሻገር አቅሙ ብልህ ነው።  መርህ ብዙ ዓይነት ነው። መርህ ሃይማኖታዊ፤ መንግሥታዊ፤ ባህላዊ፤ ማህበራዊ፤ ብሄራዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ትውፊታዊ፤ ወጋዊ፤ ሙያዊ፤ አህጉራዊ፤ ሉላዊ፤ ልማዳዊ ሊሆን ይችላል። መርህ እንደ አማኞች የሃይማኖት ዶግማ እዮራዊ ነው።  መርህ እንደ ገሃዳዊ ዓለም ደግሞ ሰዋ ሰራሻዊ ግን ህጋዊ ነው። መርህ የህግም መንፈስ አለበት። በመርህ ውስጥ ሥርዓት በማከብር እና ባለማክበር አፈጻጸሙ ይለካል። መርህ በጹሁፍ፤ በምልክትም ሊገለጽ ይችላል። አሁን ይህ © ምልክት የባለቤትነትን መብት ገላጭ ነው። መኪና በማሸከርክርም መርህ አለ በምልክት። የተከለከሉ፤ የተፈቀዱ ነገሮች በምልክትም ይኖራሉ ሉላዊም ብሄራዊም።  የሰው ልጅ ምልክቶችን ሲይ ህግ መተላላፉን ተግ ያደርገዋል። ዘበኛ ...