የአዲስ አባባ ኮሚሸነሩ ጣሪያ የነካ መታበይ።

ዝል ዝል። እምምምምምምም!
„ተቸግሬያለሁ እና አቤቱ ምራኝ፤
ዓይኔም ከሃዘኔ የተነሳ ተፈጀች፤
ነፍሴም ሆዴም።“
መዝሙር ፳፱ ቁጥር ፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ
24.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ


  • ·       መግቢያ።

ምነው እታለም በአብይ ጨከንሽ አለችኝ አንዲት የዶር አብይ አህመድ አድናቂ እህቴ። የመጨከን አይደለም ዕውነትን የመወገን ነው። ሌላውም ይቅር ቅን የፖለቲካ ሊሂቅ ማግኘት ለ አላዛሯ ኢትዮጵያ የሰማይ ስጦታ ነው። እንኳንስ ሁሉ ያለው ሰብዕና። ችግሩ እንደ ቀደመው ጊዜ ከሥራ ሃላፊነት ሁሉንም ነቅሎ ሥር ነቀል ለውጥ አለመካሄዱ፤ እንደገናም የምናውቀው የውጭ አገሩ ፖለቲካ ካለልጓም በዝርግ እልፍኝ መለቀቁ ነው።

እናም የህግ የፍትህ ዝበት ሲኖር መግለጽ የተገባ ነው። መንፈሱን ይታደጋዋል፤ በሌላ በኩል ነፃነት ሆነ ዴሞክራሲ የሂደት ውጤትን ነው። ካለትችት የግል ኑሮም ንጥረ ነገር ይጎድለዋል። አሁን ስለምጽፋቸው ከፍተኛ መኮነን ምስላቸውን እንቅስቃሴያቸውን ብቻ በማዬት በበቀል እንዴት እንደሚንተከተኩ፤ እንዴት እንደሚወድቁ እንደሚነሱ፤ ምድር እንዴት እንደጠበባቸው ስታዩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ያለባቸውን ወስብስብ ችግር መረዳት ያስችላችኋዋል።

ለምሳሌ አቶ ተከለ ኡማን ተመልከቷቸው በሚሊዬነም አዳራሻ፤ የግንቦት 7 አቀባባል፤ እና የኦነግ አቀባባል ሰብዕናቸው ተለዋዋጭ ሆኖ ነው ያገኘሁት። ምን ያህል እንደተገለባባጡ እና የልዩ የሆነ ወገናዊ ፍቅር እንዳለባቸው መስጥረው መያዝ ይችሉ ነበር እሳቸውን ሪኮመንድ ያደረገውን አካል እንዲህ በአደባባይ ከሚያጋልጡ።

የምናከብራቸው አቶ ታዬ ደንአም እንዲሁ። ስለዚህ ሹመቱ የሰጣቸውን መንፈስ እና ጉዳዩን በምልስት እንድንመረምር ግድ አለን። አገር የገቡትን የፖለቲካ ድርጅቶች ሆነ አክቲቢስቶች ስታዩም ደስታቸውን በቁጠባ መያዝ አልተቻለቸውም። ድል አድርገው አልገቡም። ይህን ያውቃሉ።

በሌላ በኩል አዲሱ ካቢኔ በነበረው መዋቅር ስለመቀጠሉ እናም የተሸከሙት ችግር ላይበቃ ተጨማሪ ችግር ፈጣሪ ሆኑ። አንድ አካል ለዛውም አገር የመምራት መሻት ያለው መፍትሄ እንጂ ችግር ጨማሪ መሆን አይገባውም።

ዛሬም ያዩኋዋቸው የአዲስ አበባ የፖሊስ ኮሺነር መሰሉን ነው ያዬሁባቸው። በቃ አቅል ጠፋ። አደብ ጠፋ። እዮባዊነት የለም። አርቆ ማሰብ የለም። ስለዚህም አሁን ኢትዮጵያ መሪ አላት ብዬ ስለማስብ በግልጽነት የሚሰማኝነት እግልጻለሁኝ። እኔ ተስፋኛ ነኝ።

 በብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ምክንያት እሰጣ ገባ ከ2016 ከጎንደር አብዮት ጀምሮ ነበር። ትናንት እዮር መልስ ሰጠ። መዳኛችሁ ይህ ነው ብሎ ተንቀሳቃሽ ምልክት ሰማይ ላይ አንጅባራ ላይ መሰከረ። ይህ ምንድ ነው ብትሉኝ አብዩን የሚረዳ፤ የሚያግዝ አይዞህ የሚል መንፈስ እንዳለ ትገነዘባላችሁ።

ለዚህ ለፈቃደ እግዚአብሄር መንገድ እንዳያፈነግጥ ደግሞ ግድፈቶች ነቅሶ በማውጣት መናገር ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። አንዲት የዛፍ ተክል ከተቀጣች ብቻ ነው ቀጥ ብላ ማደግ የምትችለው። ከሁሉ በላይ እኔ ጫካ አይደለሁም የእኔ በምለው አምክንዮ ላይ ከድኝ ዘግቼ ቁጭ የምል። አሁን እኮ የአብይን ሌጋሲ የእኔ ብዬ ነው የማስበው። አንድ ሌላ ባይታዋር አድርጌ አይደለም እምመለከተው። የሆነ ሆኖ ፍትህ እና እውነት መደፈር አለበት።
  • ·       እውሃ ያልነካው ቲያትር በአዲስ አባባ ከተማ ኮሞሸነር።

የሚገርመው በጠራራ ጸሐይ አንድ ያገር ሀብት ገድሎ እራሱን ገደለ ያለ የፖሊስ ኮሚሽን አሁን ለሰብዕዊ መብት ተሟጋች ነኝ ይለናል። የቆሞስ እኒጂነር ስመኛው በቀለ ገዳይ ማነው?

ለመሆኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ስለ ድምጽ አላባዎቹ ህጻናት እና እናቶች የሚቆረቆር ህግ አለን? አዲስ አባባ ጠፋ - ተዘረፈ - ተገደለ የምትሉት መነሻና መድረሻውን ከራሳችሁ ጀምራችሁ መርምሩት? ለመሆኑ የሰኔ 16ቱ ድራማ ማነው የከወነው? መልስ አላችሁ? እኔ የማዬው ማባጨል ነው። ህዝብን ህግን መናቅም። 

በነገራችን ላይ ቅንጅት አዲስ አባባን ተረክቦ ቢሆን መሰሉን ለመከወን መሰናዶ እንደ ነበር በወቅቱ ሹክ ያሉኝ ነበሩ። አሁን የሆነውም እንደዛ ነው።
·       መነሻዎቼ እኒህ ናቸው። ማያዣም ይቀጥላል።
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄነራል ደግፌ በዲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የሰጠው መግለጫ
Published on Sep 24, 2018

Ethiopia አቶ ጀዋር 43 ሰወች ተገድለዋል ያሉት ሀሰት እንደሆነ / ኮማንደር ክፍሌ አሰፋ ተናገሩ

Published on Sep 20, 2018

ውዶቼ ቲያትሮች በረከቱ። አክተሮችም እንዲሁ። የመስከረም የ20ውን መግለጫ ለማስተባበል ነው ዛሬ አዲስ መግለጫ የተሰጠው። በስንት ዘመኑ ሲማጥ ተሰንብቶ ማስተባባያው በድንፋታ እነሆ ቀረበ? ድጋፉ ለአሸባሪዎች የበቀል ማወራረጃ ግርዶሽ ለማስራት ነው። እነሱን ለመሸፈን ነው ይህ ሁሉ ጥድፊያ።  „የምጣዱ ሳላ የእንቅቡ ተንጣጣ“ ነው። የሚገረመው እኔ አሁን የሚገባኝ የተለመደው ባለቤት የሌለው ወገን እንዳለ ነው። በጣም ይገለማል።

በዛ በበከተው፤ በወንጀል በጨቀዬው፤ ትውልድ ገዳይ የ27 ዓመት የወንጀሎኞች መሪነት ዘመን እና ሥርዓት ውጤት የሆኑ መከራዎች ሁሉ እኮ ናቸው ዛሬ የምናዬው ነገር ውጤት። በ11 ዲጅታል እድገቱም፤ ምጥቀቱም፤ የአፍሪካ ነበርነቱም እንዲሁ። 

„እኛ እንደምንፈለገው የባከነ ትውልድ ሆነህ እንድናይህ እንፈቀዳለን“ የተባለው ኢትዮጵያዊ ወገን  „ወንጀለኛ፤ ወሮበላ፤ ቦዘኔ“ እዬተባለ የድርብ ቂም መወጣጫ ሆኖ እያዬን ያለነው። ለነገሩ ለነፃነቴ ክብሬ የተባለው ተፎካከሪ ፓርቲ ሊሂቃንም ቃሉን ሳያፍሩ ይጠቀሙበታል። 

ወንጀሎችን አደራጅቶ የሚፈጽመው ማነው? ወንጀል ተከላካዩስ የት ነበር? ሰው ሲገደልስ ነፍስ ሲጠፋ የምንን ጎፈሬ ያበጥር ነበር? ወንጀልን ማን አስፋፋው?
በቅድሚያ ወንጀለኛው ማን ነው? „አህያውን ሲፈሩ መደላድሉን“ አሉ። እስኪ የኢትዮጵያ መንግሥት አቅሙ ካለው ወደ ትግራይ ጎራ ብሎ ወንጀሎኞችን ይያዝ እና ለህግ ያቅርብ እዚህ ይህን ያህል ከሚፎክርብን? የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች እኮ ነው ይህን ትውልድ እንዲህ አድርገው አባክነው የቀረጹት።

እኔ እንዲህ ያለ ኮሚሸነር በመታበይ ለዛውም ህግ አስከባሪ አካል አይቼም ሰምቼም አላውቅም። የኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሸነሩ ሸከም፤ የአዳማው የሚያብጭሉ፤  የአዲስ አባባው ደግሞ የሚነጥሩ ዝል ዝል የሚሉ አደብ የነሳቸው ቂም፤ በቀል የናፈቃቸው፤ ስልጣናቸውን ለማሳዬት የቋመጡ? ተሳህለነ!

„አንቺ አገር ኢትዮጵያስ“ የአብዩ ግጥምስ አሁን ነው። ምነው ወንበሩ እንዲህ ያነጥራልን? እንዲህ ዓይነት ንዝረት እኔ ያዬሁት፤ የሰማሁት እና የሞከርኩት ፊትነስ ስቴዲዮ ላይ ነው። ልምምድ ሳደርግ። ምን እንጡርብ ያዘልላል? ማን አይዞህ ስላለ ይሆን? አሳዬን የተባለ መንፈስ ይመስላል? ጦላይ ድረስ እንደተሄድ ሰማን።፡አጀብን ነው „አንቺ አገር ኢትዮጵያ።“ ከዛ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ወጠምሻ ይጠብቃቸዋል።

ከአንዱ መከራ ወደ ሌላው ሰቆቃ። ከ አንዱ ዕንባ ወደ ሌላው። ሰውም እርም የለውም። ልብም የለውም። እኔ ታስሬ ከተፈታሁ በኋላ አንዲት ድርጅት ትውር አላልኩኝም። ማህበር የሚባል እንኳን እንኳንስ የፖለቲካ ድርጅት። አሁን ቀጣዩ በዚህ የመረጃ ውልብልቢት መሰረት ወሎ ጎንደር እና መቱ መሰለኝ የታጩት …  

የሆነ ሆኖ ይህን ያህል ዝላይ ስለምን አስፈለጋቸው የአዲስ አባባው ፖሊስ ኮሚሽን ሚጄር ጄኒራል ደግፌ በዲ፤ ስለማን ነው የቆሙት? ስለህጉ ወይንስ ስለ በቀል? ምንድ ነው ይህን ያክል ድንፋታ? ይህ አገር እኮ የሁሉም ነው። የሳቸውም የሌላውም።

ውደቼ እኔ ሳድግ ጫት መልኩ ምን እንደሚመሰል አላውቀውም። ሺሻ የሚባለውንም እንዲሁ። ይህ የወያኔ ዘመን ነው ያመጣው የበከተ ባህል ነው። ለነገሩ የቤተሰብ ዕሴትም እኮ ከስሟል። ስለሆነም የሥርዓቱ ነቀርሳ እራሱ ሥራዓቱን በመንቀል እንጂ የዛ ሰለባ የሆነውን ህዝብ በማሰቃዬት ምክንያት ፈልጎ በመበቀል አይደለም። ብቻ የተጎዳ ይጎዳል።

ኤዲቲንግ ፈጽሞ የማይደረግበት እንደዛ የወጣቶችን ሥነ - ልቦና ድቅቅ አድርጎ ከሚያሳድገው የተለያዬ የወንጀል ማምረቻ የአማርኛ ፊልም ነው እኮ ነው ሁሉም ነገር የሚመረተው… ። ሽሻ የሚባለውን እኔ ራሴ ያዬሁት ከዛ ነው። ፈጽሞ እኮ ኢትዮጵያ አትመሰልም ፊልም ስትመለከቱ።

በኤርትራ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ አቀባበሉ ላይ ወጣቶችን ሳይ ለዛቸው በተፈጥሯቸው ውስጥ ነው። ያልሆኑትን እንዳይሆኑ ተገርተው ያደጉ ወጣቶችን ነው ያዬሁኝ። እኔ በጣም ነው የቀናሁት። እራስን መሆን።

የሺሻ ፕሮጀክት ከፍተህ፤ የጫት ንግድ ፈቅደህ፤ የሥርዓት አልበኝነት ፊልም ፈቅደህ እንዴት ዓይነት ትውልድ ይጠበቅ ኗሯል? የንግድ ፈቃድ የሚሰጣቸው ቀድሞ ነገር እንማን ናቸው? ማነው ኮንትሮባንዲሰቱ?

እዛ አገር እንመራለን ያሉ ቱቦ ጫተኛ፤ ቦንዳ ሺሸኛ፤ ወዘተረፈ ዘራፊ እና ዘማዊ አስቀምጠህ ምስኪንን ጊዜ ጠብቀህ የበቀል ማወራረጃ ታደርጋለህን? እስኪ ወንድነቱ ካለ ይህን ውል አስይዙት። ይህ ይደመጥ።

https://www.youtube.com/watch?v=AaIVlfG1dLM

ESAT Yesamintu Engeda B.General Melaku Shiferaw part 2 August 2018

 

ኢትዮጵያ ውስጥ የአገርን ሉዕላዊነት የሚያሰከብር ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ድርጅት እኮ ለወንጀል ህጋዊ ሽፋን የሚሰጠው እንብርቱ እሱ ነው መከላከያ። የደላሎች ብዛት የአንድ ብሄረሰብ አባል መሆን፤ ውሉይነራል፤  ክፍያው ይፈጸማል ግን ፕሮጀክቱ የውሃ ሽታ ነው። 

 

እና እነዚህን የተሸከመች አገር ነው አሁን ወንጀለኞችን አዲስ አባባ ከተማ እያጸዳሁ ነው የምትለን? ልብ ከኖረ የገማው ጭንቅላቱ ይደፈር።

 

መዝረፍ ዋነኛው መርህ ነው። እነዛን የዛቀጡ ግለሰቦችን ተሸከምህ፤ በልቶ ለማደር የተሳነውን ትለቀማለህ። ፎቶ ቢዲዮ ቃለ ምልልስ ማስረጃ አለን ይባላል። ያ የተለመደ ነው። ምን ምርጫ አላቸው አስገድደህ፤ አስይዘህ ፎቶ ታነሳለህ። አስገድደህ „ነኝ“ ታሰኛለህ። ዕውነቱ ሲመጣ እማ ታዬ እኮ እራሱን አጠፋ፤ ለሌላ ቀጠሮ ተቀጠረ ወዘተ ወዘተ፤ አራጅን ከብክበህ ሥሙን እንኳን ለማንሳት ተቸግረህ ትጠመለመላለህ … እና በሌላ ማለከክ የተገባ አይደለም። 


በዶር አብይ አህመድ ድጋፍ ላይ ያን ያህል መተመመህ አቃጥሎናል እንበቀልሃለን ማለቱ አይቀለም። ያው ኦሮምያ ላይ ያለቸው ድጋፍ እናውቀዋለን። ውጪም የደከመነው እኛው ነን።


ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን ራሱ ሥርአቱ እኮ ዘራፊ ነው። ራሱ ሥርዐቱ ወንጀለኛ ነው። በዘረፋ ላይ ሩሁ የተንጠለጠለ ሥርዓት እኮ ነው ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው። ራሱ ሥርዓቱ ወንጀልን ቀርፆ፤ አበጅቶ ነው ህይወቱን የሚያስቀጥለው።

አሽዋ ሞልቶ ዓለም አቀፉን ህብረተሰብ ያታለለ እኮ ነው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ማለት። በዛ የደነደነ የሰባ የወንጀለኝነት መንፈስ አሁን አንደበት አለኝ ብሎ ይህን ያክል ተሻሚው ሁሉ ይፏልላን? ማነው ወንጀለኛ ትውልድ የፈጠረው? ማነው ሲሰኛ ትውልድ የፈጠረው? ንገሩን ባዮች።

የሚገርመው የኦቦ በቀለ ገርባ እና የአቶ ጃዋር መሃመድ ቶን እና የሜ/ ጄ ደገፌ ቶን ብቻ ሳይሆን የተጠቀሙበት ቃሉ እራሱ አንድ መሆኑ ነው። የወንድ እናቱ አንድ ናት ነው የሚባለው። የት ሄደ ፖሊስ ተብዬው ይህ ሁሉ ወንጀል ሲሰራ? ራሱ ፓሊስም እኮ ወንጀል ሠሪ ነው። ሞገድ መጽሐፍን ማንበቡ መልካም መሰለኝ።

 

ደግሞስ 27 ዓመት ተኑሮ አሁን ነው ለማመካኛ ወንጀለኛን በመዲና የማጥራት ዘመቻ ምንትሶ ቅብጥርሶ የሚባለው? ስንት ዘመን ታታልሉ። ሌላው አሁንስ ይህ ሁሉ ህዝብ ከመኖሪያ ቤቱ የሚፈናቀለው ወንጀል ተሠርቶ አይደለምን፤ በወንጀለኞች እና በወንጀል ተከላላካዮች ትብብር አይደለምን የራስ ወገን በ አገሩ መሬት ብትን አፈር ያጣው? በእጅ የተሠራ ወንጀል እኮ ነው በሚሊዮን የሚቆጠር ዜጋ በዬለቱ የሚፈናቀለው። ያው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ መምራት አይችልም ለማለት።

 

https://ethioexplorer.com/%E1%89%A0%E1%88%83%E1%8C%88%E1%88%AD

በሃገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር ኢትዮጵያ ከዓለም በአንደኛ ደረጃ ላይ እየመራች ትገኛለች።

የትኛው አገር ወሯት ነው ኢትዮጵያ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ  በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ይህን ያህል ተፈናቃይ የኖራት? ከዓለም እኮ የአገር ውስጥ ተፈናቃኝ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛለች? የት ነበረ መንግስታዊ ፖሊስ ኮሚሽን? ቀድሞ ነገር እስከ ዛሬስ የት ነበራችሁ? ዛሬ ነው ሃሺሽ ቤት፤ ጫት ቤት ወዘተ የሚታያችሁ …

 

አሁን ነው ፓርቲዎች አገር ውስጥ ግቡ ተብለው ሲገቡ በአንድ ሳምንት ይህ ሁሉ ሽሻ ቤት እና ጫት ቤት የተከፈተውን? አሁን ነው? ወደዬት ለመግፋት ነው የሚፈለገው? ወንጀለኛው እኮ ራሱ ሥርዓቱ ነው።

 

ከዛ አካልዴማ ድራማ ተወጣ ተብሎ እኮ ነው አዲስ ለውጥ፤ በአዲስ መንፈስ የተባለው። ይገርም ነው እናንተ እቴ! አሁንም እዛው ዱቅ እንዳላችሁ ነው። ይህንማ ተኖረበት እኮ። „ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማው“

 

ቀድም ሲል ግንቦት 7፤ ኦነግ፤ ኦብነግ፤ ሻብያ ነበር አሁን ደግሞ የፖለቲካ ድርጅቱ ሥያሜ ሺሻ ቤት፤ ጫት ቤት ተብሎ ማሳበቢያ ተፈለገ። ቡራዩ፤ አስኮ፤ አሽዋ ሜዳ ኮልፌ ወዘተ በቀሉ አልበቃ ሲል ደግሞ የከተማውን ህዝብ እንዲሸበር፤ መረጋጋት እንዳይኖረው ስበብ ተፈልጎ እዬታፈስ ይገኛል።

 

ወንጀል እኮ የሚጠፋው የቀደሙት አናት ወንጀለኞች ለፍርድ ሲቀርቡ ነው። የትናንትና፤ የዛሬም ወንጀለኞች ለፍርድ አልቀረቡም። ራሱ ለይቶ ለመጥራት እንኳን አልተደረፈም። ቄሮ ጀግና ነው። ሁላችን ያስማማናል፤ ቄሮ ደግሞ ገዳይ ነው የሚለውን ምንም ማሰሪያ የሌለብን እኛ ብቻ ነፃ ሰዎች ነው የምንስማማበት። መጀመሪያ ይህ ይደፈር፤ አንድ ጥግ የሌላቸውን ከማሳደድ።

 

ኢትዮጵያ እኮ ህጋዊ ወንጀሎኞች ወንጀልን በህግ ጥስት አስደግፈው የሚመሩባት አገር ናት። ሽብረተኝነት ከብክባችሁ እንዳሻው እያዘበናናችሁ፤ ለበቀል የሚያመቻችሁን ታቤላ እዬለጠፋችሁ ሌት እና ቀን ድጋፍ የሰጠን፤ ደሙን የገበረ ወገንን ስታንገላቱ ትገኛለችሁ። ማተበ ቢስነት ነው ይህ። አንገለብጣችሁ አለን ብንፈልግ እያለ የመደነፋለችሁ እኮ እዛው አለላችሁ። ነገ ምርጫ ብለህ አትሰብ አትመረጠም እያለ እንደለቡ እዬፏለል … ብቻ ሚዛን እና እውነት ሲደፉ ይመረኛል።

 

በተለይ የ አዲስ አባባ ኮሚሽነሩ ቃል የተገባለዎት ቢኖርም ምነው ትንሽ አደብ ቢኖር፤ ይህን ያህል የደም ፍላት?  መጥኔ ለታምኝነት፤ መጥኔ ለይቅርታ ዘመን፤ መጥኔ ለፍቅር ዘመን፤ መጥኔ ለመቻቻል ዘመን፤ መጥኔ ለተስፋ ዘመን።

 

በእጅ ተጠፍጥፎ የተሠራ ወንጀል ነው ዓመቱን ሁሉ ንጹሃንን እያመሰ ያለው። ሰው ተገድሎ ተዝቅዝቆ የሚሰቀልበት አገር ይህ አደባባይ እንዲወጣ አይፈለግም? ከ15 ሺህ ያላነሱ ወገኖቻችን በግፍ ተፈናቅለዋል። ከ50 እስከ 60 የሚጠጉ ወገኖቻችን በግፍ ታርደዋል። ቁጥራቸው የማይታወቅ እጅግ በሚሰቀጥጥ ባርብርያን ሁኔታ ተቀጥቅጠዋል፤ ተገለዋል፤ ታርደዋል፤ ተዘርፈዋል፤ ተደፍረዋል ልጆቸቸቸውን፤ ንብረታቸውን ተነጥቀዋል። ያ ሁሉ ተጠያቂነት የለም።

 

ስለምን ብለው የጮኹት ደግሞ  በአደባባይ ተረሽነዋል … አታፍሩም ይህን መደለዣ ይዛችሁ ስትመጡ … ይህን ያህል ዝል ዝሉስ ምን ተፈለጎ ነው? „ጌታዋን የተማመነች በቅሎ“ አሉ?

 

ዛሬ ታሪካችን በውጭ ዜጎች አይደለም የሚጻፈው እኛው እንጽፈዋለን። አብዩን ስላከበርን እንጂ እስከ አሁን ድረስ ስንት ቦታ በደረስን ነበር? አትፈንጩ! ልክ ይኑራችሁ! ለካ ጥጋብ እንዲህ ነው የሚያደርገው። እንከባባር!

·       የችግሩ ምንጩ ይህ ነው።

Ethiopia: ኦፌኮ ምክትል ልቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ OMN ጋር ያደረጉት ቆይታ

ጀዋር መሐመድ ዛሬ . ውስጥ ስለተፈጠረው ግጭት የሰጠው መግለጫ

 

ገራሚው ነገር ቋንቋውን እንኳን መቀዬር አልተፈለገም „ወሮባላዎች፤ ዱረዬዎች“ ሌላው የሚደንቀው ደግሞ „ምህረት የለንም“ አዎን! የበቀል ፖለቲካ፤ የጥላቻ ፓለቲካ፤ የበታችነት ፓለቲካ ምረተቢስ ነው።

 

ቀጣይ ስለመሆኑ እኮ እያዬን ገድለህም፤ ነቅለህም እርዳታ አይሰጠም አለበት። አርደህም፤ አሳደህም ስለምን ተጎጁ ተጠዬቁም አለበት። ለነገሩ ከግራኝ ዘመን ናፋቂዎች ምን ይጠበቅ ነበር? …. ይኸው ነው። የማይታወቅ አቅጣጫ እንዳይመጣ ስጋት አለኝ ስል የነበርኩትም ይኸው ነው።

 

ድንፋታውንም ጥጋቡንም በቀሉንም ተግ ማድረግ ይጠቅማል። የምድር ገዢነታችሁን የሚጥስ እዮራዊ ቁጣ ደግሞ መኖሩን ልብ በሉ። „ወልደው ሳይጨርሱ ግፍ … „ እንዳይሆን?

 

የምደግመው ሌላው ወንጀለኞች ለናሙና የቀረቡት አማራ እና ደቡብ ክልል ብቻ ነው ወንጀለኞች ያሉን?? ስንት ጊዜ ይለቀስ? ስንትስ ጊዜስ ይማጥ?

 

እኛ ግልጥልጥ አድርገን ነው የምንጽፈው እናንተም ገልጣችሁ ተናገሩት። ወንጀለኛ ነው የምትሉትን እከሌ የሚባል ድርጅት በሉ፤ ያው ገና የዛሬ ሁለት ዓመት ወንበር እናጣለን ነው ግብ ግቡ … በነበረው መልካምነት ድንቅንት ቢቀጥል እኮ ሥርጉተ ሥላሴ ራሱ በአብይ አክቲቢዝም ላይ ነው የምትተጋው።

 

ለነገሩ እነሱም ጅሎች ናቸው … ተፎካካሪ ተብዬዎች በወያኔ ማንፌስቶ ፋሽስታዊ ሥርዓት ውስጥ ያሉ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሄር  የግንባሩንም፤ የዲሞክራሲ ሚ/ር መ/ቤቱን ጉሮሮ ላይ እንደ ተቸከሉ እያዩ እንወዳደራለን የሚሉት … እዬፎከረም ነው የ አብይን ሌጋሲ እጎምደዋለሁኝ ብለው … እኔ የ አማላክ ፈቃድ ስላለበት አይችሉም ባይ ነኝ። አፍሪካ እራሱ አብይን ትፈልገዋለች።

 

ተፎካካሪዎች ግን ይልቅ መንፈሳቸውን እረብ እደረገው ቁርጣቸውን አውቀው በሰላም ወደ የግል ኑሯቸው ቢመለሱ መልካም ነው ተፎካካሪ ተብዬዎች። በተበላ ቁብ መድከሙ ሳይሆን ዛሬም እንደ ትናንቱ ከኢትዮጵያ ትቅደም ያለምንም ደም፤ ከይቅርታ መሻገር ወደ ደም ጨዋታው ተቀይሯል። „ምህረት የለነም“ ብለዋል  የአዲስ አባባ ፓሊስ ኮሚሸነሩ። እርግጡን ተናገረዋል። አዲስ አባባ ከላ አቶ ታከለ ኡማ መቼውንም ቢሆን አይታሰብም።

 

ብቻ ለዬዘመኑ የትወልድ ግብር፤ ለዬዘመኑ የሰው ልኳንዳ ቤት ታቅርብ የአላዛሯ ኢትዮጵያ እናት።

 

የሚገርመው ስንፈታቸው አስተምረን ነው ይላሉ ስሜታቸውን የሚገቱበት ማህለቅ ያልፈጠረላቸው የአዲስ አባባው ፖሊስ ኮሞሸነር ሜ/ ጄ ደገፉ፤ ለመሆኑ ማነው አስተማሪው? ያው በወንጀል፤ በስርቆት፤ በማጭበርበር፤ በግድያ፤ በህግ ጥሰት፤ በበቀል እና በጥላቻ ያልተዘፈቀ ማን አለና?

 

ትውልድን ለመገንባት ምን ዓይነት ተቋም ነው ያለው? ሰው ተገድሎ ተዘቅዝቆ በሚታሠርበት አገር? እምምምምም … ባንኮችን ለይቶ የ ኦሮሞ ወገኖቻችን ንብረት ጥፋትን የፈጸመውን ወንጀል ነው ለይቶ ለህግ ማቅበር ግን የተጋባ ነው። ምን አልባት እሱ በ እሱ ካልሆነ በስተቀር፧ ከዚህ ባለፈ ያለው ግን የበቀል ርምጃ መሆኑን "ለቃባሪው አረዱት" ነው የሚሆነው። 

 

የኔዎቹ በዬሰዓቱ መልካም ነገሮች ጋር መጪ እንዳላልን ሁሉ የአገር ግቡ ፊርማው ሳይደርቅ „እናሳያችሁ“ አለን ሆነ ጨዋታው ሁሉ … ከዬት ከዬት ነው የሚያመጧቸው … እንዲህ በወገነህ ለይ በቀልን ህጋዊ ለማድረግ ጫን ጫን የሚያሰተነፍስ ጉዱ ምኑ ይሆን“

 

የአዲስ አባባው ኮሚሸነር ደግሞ ከምኑ ሲኦል እንደመጡ እግዚኦ ያሰኛል። ትንሽ ብጣቂ ሰውኛ ጠረን የላቸውም? አሳዘኑኝ የውነት ዶር አብይ አህመድ ያን ሁሉ የደከሙበት የ100 ቀናት የሞራል ትምህርት ውሃ የባለው ቅል ነው ያደረጉላቸው በዬደረጃው ያሉ መሪ ተብዬዎች። ትንሽን ሰውኛ ቀርቶ ዶልፍኛ እንዴት ይጣፋል? ይህን ያህል ትዕቢት? ፐ¡

 

አቤቱ አንተ ዳኘው። እኔ ተስፋ ኦቨር ይሆንን ያሰኘኛል  … የአብይ ሌጋሲ ቅንነት ላይ አንድንዘመትበትም የተፈለገም ይመስለኛል። ምን እናድርግ? ግድ ይለናል እንዲህ ዳጥ የበዛበት ምጥ ሲጠና። የአቶ ጃዋር ቲም እና ሚዲያው ህልሙ ስለመሆኑ አሳምረን እናውቃለን። የወያኔ ሃርነት ትግራይም።፡

·       ክወና።

በሌላ በኩል አብዩን እንኳን የእኛ ሆንክ እንልና፤ ግን ከእኛ ለሚቀጠልው ትውልድ በተፈጠረክለት ነበርም እላለሁኝ። ካላዘመኑ የተፈጠረ።  ዶር አብይ አህመድ እስካንድንብያ ተፈጥረው ቢሆን የምለውም ለዚህ ነው። ብቻ ብቻ ነው … አገር ምድሩ የሴራ ትብትብ … „ነቅናቂ እያለ ማን ጥሩ ይጠጣል“ ነው። ለዛ በዕንባ ለኖረ ህዝብ በዬዕለቱ መከራ አጭቶ ማሳዘል? ለመሆኑ እኛ ምኖች ነን? ያልታደልን!

 

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

 

አዱኛዎቼ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

 

 




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።