#የድል አጥቢያ አርበኞች ወጋወግ። አቶ ጣሂር መሃመድ ተስፋ ከተጣለባቸው የአብን መሪወች አንዱ ...
#የድል አጥቢያ አርበኞች ወጋወግ። አቶ ጣሂር መሃመድ ተስፋ ከተጣለባቸው የአብን መሪወች አንዱ .... ዬት እንደነበሩ አላውቅም። ግን ወደ ፊት ሲመጡ ተቃውሞ አልነበረኝም። እርግጥ ነው በአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ውስጠት ያልነበሩ ሰብዕናወች ይሁን በሌላውም የትግል ዘርፍ አብረው ያልተነሱ ሰብዕናወች በኋላ ሲዶሉ ፋክቱም ሳይንሱም ችግር ፈጣሪ አንጃ ዓዋላጅ እንደሚሆኑ እሙን ነው። የአብን ጉባኤ ሲካሄድም ባልደራስ ሲመሰረትም ዘለግ ባሉ ሙያዊ የአደረጃጀት ዕይታወቼን አጋርቻለሁኝ። ይህ አደጋ በአቶ ጣሂር መሐመድ ብቻ ሳይሆን በዬትኛውም ሁኔታ በሚመሀረቱ ተቋማት አዲስ ገቦች የችግር መፍቻ ከመሆን ይልቅ የችግር ጦስ ይሆናሉ። የሆነ ሆኖ አቶ ጣሂር በመጀመሪያው ጉባኤ አልነበሩም። እሳቸው በሁለተኛው ጉባኤ ጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ለመፈንቅለ አብን ከአደራጇቸው ወጣቶች አንዱ ሁነውህዝብ ግንኙነትን ይመሩ ዘንድ ተመረጡ ሳይሆን ተመደቡ ብል ይሻለኛል። በፖለቲካ ውሳኔ። አብን መራራ ስንብቱ ከዓላማው ጋር የተከወነውም ያን ጊዜ ነበር። አቶ ክርስቲያን ታደለ ታስሮ ነበር። ጉባኤው በዋዜማው አቅል አጥቶ ተካሄደ። በማግሥቱ አቶ ክርስቲያን እና ሌሎች የአብን አካላት ከእስር ተፈቱ። በዚህ ጉባኤ ዶር ደሳለኝ ጫኔ በፈቃዱ ለቀቀ አቶ በለጠ ሞላ ፕሬዚዳንት ሆኑ። ይስጥ የነበረው ቃለ ምልልስም የተነፋፋ እና በመታበይ የተባ ነበር። በምክትል እያሉ ያላሳዩት መንጠራራት ሊቀንበር ሲሆኑ መታበያቸው ይፋ ሆነ። አንድ ጊዜ የአብን አባል ያልሆነ ስለኛ አስተያዬት የመስጠት ድርሻ ሊኖረው አይገባም የሚል የተንጠራራ፤ የተወጣጠረ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ሁሉ ነበር። የሆነ ሆኖ ከኦነጋዊው ኦህዴድ የምርጫ ዕውቅና በኋላ አቶ ጣሂር የአማራ ክልል የቱሪዝም ቢሮ ኃ...