#የድል አጥቢያ አርበኞች ወጋወግ። አቶ ጣሂር መሃመድ ተስፋ ከተጣለባቸው የአብን መሪወች አንዱ ...
አቶ ጣሂር መሃመድ ተስፋ ከተጣለባቸው የአብን መሪወች አንዱ .... ዬት እንደነበሩ አላውቅም። ግን ወደ ፊት ሲመጡ ተቃውሞ አልነበረኝም። እርግጥ ነው በአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ ውስጠት ያልነበሩ ሰብዕናወች ይሁን በሌላውም የትግል ዘርፍ አብረው ያልተነሱ ሰብዕናወች በኋላ ሲዶሉ ፋክቱም ሳይንሱም ችግር ፈጣሪ አንጃ ዓዋላጅ እንደሚሆኑ እሙን ነው።
የአብን ጉባኤ ሲካሄድም ባልደራስ ሲመሰረትም ዘለግ ባሉ ሙያዊ የአደረጃጀት ዕይታወቼን አጋርቻለሁኝ። ይህ አደጋ በአቶ ጣሂር መሐመድ ብቻ ሳይሆን በዬትኛውም ሁኔታ በሚመሀረቱ ተቋማት አዲስ ገቦች የችግር መፍቻ ከመሆን ይልቅ የችግር ጦስ ይሆናሉ።
አቶ ክርስቲያን ታደለ ታስሮ ነበር። ጉባኤው በዋዜማው አቅል አጥቶ ተካሄደ። በማግሥቱ አቶ ክርስቲያን እና ሌሎች የአብን አካላት ከእስር ተፈቱ። በዚህ ጉባኤ ዶር ደሳለኝ ጫኔ በፈቃዱ ለቀቀ አቶ በለጠ ሞላ ፕሬዚዳንት ሆኑ። ይስጥ የነበረው ቃለ ምልልስም የተነፋፋ እና በመታበይ የተባ ነበር። በምክትል እያሉ ያላሳዩት መንጠራራት ሊቀንበር ሲሆኑ መታበያቸው ይፋ ሆነ።
አንድ ጊዜ የአብን አባል ያልሆነ ስለኛ አስተያዬት የመስጠት ድርሻ ሊኖረው አይገባም የሚል የተንጠራራ፤ የተወጣጠረ ቃለ ምልልስ ሲያደርጉ ሁሉ ነበር።
የሆነ ሆኖ ከኦነጋዊው ኦህዴድ የምርጫ ዕውቅና በኋላ አቶ ጣሂር የአማራ ክልል የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሆኑ። ለምን ከዛ እንደተመደቡ ማስተዋል አብዝቶ የሰጣቸው ወገኖቼ ይረዱታል ብዬ አስባለሁኝ።
አቶ ጣሂር ጎንደሬ መሆናቸውን ያወቅኩት እንፍራንዝ ከተማ የምርጫ ጣቢያቸው መሆኑን ስለማ ነበር። የእኔ ትኩረት አቅም፤ ሥርዓት እና ክህሎት እንጂ የመንደር ዝርዝር ማዘርዘር ስላልሆነ። የሆነ ሆኖ ለምን አልተመረጡም ብዬ ከፍቶኝም ነበር። የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ አብዮት የተካሄደበት ጎንደር አንድ ወጣት መምረጥ እንዴት አቃተው ሁሉ ብዬ ጽፌያለሁኝ። ብቃትም አይ ስለነበር። የቢሮ አመዳደቡ ግን የጠቅላይ ሚር አብይ የሴራ ዳንቴል ነበር።
የጎንደር ከተማ ከንቲባ ከ7 ጊዜ ላላነሰ ተቀይሯል። አንድ ጥምቀት ዝግጅት ከተጠናቀቀ ወዲያው የከንቲባ ምደባ ጠሚር አብይ ያካሂዳሉ። ጎንደር በታሪኩ የሰከኑ ዶር ከንቲባ ሆኑ ሲባል ጎንበርን ለማልማት አሜሪካን አገር እንደሄዱ ሳይመለሱ ከከንቲባነት ወርደው የአማራ ክልል የቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ተደረጉ የጎንደር ከተማ ከንቲባ። ለፓርላማ እጩ እንዳይሆኑ ጎንደር ከተማ ላይ።
ከምርጫ ማግሥት የጎንደር ከንቲባው የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ተነስተው አቶ ጣሂር ተመደቡ። በስፖርቱም ዘርፍ እንዲሁ ተከወነ። ከንቲባው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ይመስሉኛል።
የሆነ ሆኖ ልጅ ጣሂር ጥሩ ተግባር ለመከወን ጥረት እንደሚያደርጉ ያዬሁት በ2014 ዓም የጥምቀት በዓል ላይ ነበር። ክፍተቶች ቢኖሩም መልካም ነገር አልጠፋበትም።
በቀጥታ የተሳትፎዋቸው ሂደት ግን በአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ መንፈስ ሳይሆን የተዳበለ ፍልጎትን ሲያራምዱ ቆይተዋል። አሁን ዬጎሸው ጠርቶ ጠቅልለው የሞጋሳ ተጠማቂነታቸውን አና ማለታቸውን እያስተዋልኩኝ ነው። እነኝህ ከሥር የተለጠፋ በኽረ ጉዳዮች የአማራ የማንነት እና የህልውና ተጋድሎ የሚታገሉት እራሱ የአብን መንፈስ መሆኑ ያመሳጥራል።
"ከንቱ የከንቱ ከንቱ ሁሉም ነገር ከንቱ።"
ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ኑሩልኝ። አሜን። ቸር እንሁን። ቸር ያሰማን አሜን። ደህና እደሩልኝም። አደራ አንብቡት፤ ለታሪክም አስቀምጡት። ይበጃል። ኢትዮጵያዊ አማራነት ያሸንፋል። ተስፋችን አምላካችን።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17/11/2023
#ቅዱስ ብፁዕ ላሊበላ።
Amhara Culture & Tourism Bureau
"ዓለም ሁሉ ለኔ ብሎ በሚሳሳለት የላሊበላ ቅርስ ላይ ክፉ ነገር ማናፈስ እና መመኘት የነውር ጥግ ነው" የሰሜን ወሎ ዞን አስተዳደር
ባሕር ዳር: ሕዳር 01/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር የዞኑን ወቅታዊ ኹኔታ የተመለከቱ መረጃዎችን ለአሚኮ ሰጥተዋል። እንደ ዋና አሥተዳዳሪው ገለጻ የዞኑ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ተከስቶ የነበረው የሰላም እጦት ችግር እንዲቀረፍ ሰፊ ርብርብ ሲያደርግ ቆይቷል። በመኾኑም አሁን ላይ በሁሉም የዞኑ አካባቢዎች አንጻራዊ ሰላም ሰፍኖ ወደ መደበኛ የልማት ሥራ ተገብቷል ነው ያሉት። "
"ይሁን እንጅ ጽንፈኛ ታጣቂዎች ከሰሞኑ ወደ ላሊበላ ከተማ ገብተው የከተማውን ነዋሪዎች ወደ ዳግም ምስቅልቅል ሊያስገባ የሚችል ድርጊት ፈጽመዋል ብለዋል። በዚህም ምክንያት የሕዝብ መገልገያ ንብረቶች ወድመዋል፣ ተቃጥለዋልም ነው ያሉት። ይህም ሰላም ወዳዱን እና እሴቱን አክባሪውን የላሊበላ ሕዝብ ያስቆጣ ተግባር ነበር ብለዋል ዋና አሥተዳዳሪው።
"በመገዳደል የሚፈታ አንድም ጥያቄ አይኖርም" ያሉት አሥተዳዳሪው በቤተ እምነቶች ውስጥ የተጠለሉ ሰዎች ሳይቀር በግፍ ተገድለዋል ብለዋል። ይህ ድርጊት ከላሊበላ ነዋሪዎች እሴት የተጣረሰ፣ ከአማራዊ የሥነ ልቦና ውቅርም ያፈነገጠ ነውና መላው የሰሜን ወሎን ሕዝብ አሳዝኗል ብለዋል።"
"አሁን ላይ ወደ ላሊበላ ከተማ የዞኑ የጸጥታ አካላት እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ገብተው ሕግ የማስከበር የዘወትር ሥራቸውን እያከናወኑ ስለመኾኑም አሥተዳዳሪው ገልጸዋል። የከተማው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች እና ነዋሪዎች ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር ተከታታይ የሰላም ውይይቶችን እያደረጉ ስለመኾኑም ገልጸዋል። ሕዝብን አሳዝኖ ያለፈው ድርጊት ዳግም እንዳይከሰት ነዋሪዎች ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በቅርበት እየሠሩ ነው ብለዋል። "
"ያልኾነውን ኾነ በማለት ስለላሊበላ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው የሀሰት መረጃ መበራከቱንም ዋና አሥተዳዳሪው ገልጸዋል። በተለይም በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ላይ ጉዳት እንደደረሰ በማስመሰል በርካታ የሀሰት መረጃዎች እየተናፈሱ ነው ብለዋል።
"ላሊበላ እንኳንስ ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ሃብት ነው፤ በመኾኑም ጥብቅ ጥበቃና ጥንቃቄ እየተደረገለት ነው" ሲሉ አሥተዳዳሪው ተናግረዋል። "ስለላሊበላ ከተማ እና ቅርሶች በማኅበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው ወሬ ሁሉ ፍጹም ከእውነት የራቀ ነው" ሲሉም አረጋግጠዋል። "
"ከኢትዮጵያም አልፎ ዓለም ሁሉ ለኔ ብሎ በሚሳሳለት የላሊበላ ቅርስ ላይ ክፉ ነገር ማናፈስ እና መመኘት የነውር ጥግ ነው፤ በመኾኑም እንዲህ አይነት ከእውነት የራቀ ወሬ ሊቆም ይገባል" ሲሉም አሥተዳዳሪው አስገንዝበዋል።
በከተማው አሁን ላይ አንጻራዊ ሰላም ሰፍኖ ነዋሪዎችም በነጻነት እየተንቀሳቀሱ፣ የንግድ ተቋማትም የተለመደ አገልግሎታቸውን እየሰጡ ነው። ማኅበረሰቡ ሰላም እንደሚበጅ ስለሚገነዘብ ተከታታይ ውይይቶችን እያደረገ፣ አጥፊዎችንም እየመከረ፣ ከዚህ ያፈነገጡ ካሉም በሕግ አግባብ እየጠየቀ ነው ብለዋል ዋና አሥተዳዳሪው። "
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን! «
#ከቤቱ ድረስ ሄዶ ስለሚፈጀው የኦነግ ሠራዊት።
«የአማራ ህዝብ የተደቀነበት አደጋ ሊፈታ ከሆነ መፍትሄው ግጭት ወይም ግድያ ሊሆን አይችልም፡
=======
"ይህም ዘመኑን ያልዋጀ ኋላ ቀር የትግል ስልት ነው፡፡
ዛሬ የአማራን ህዝብ አንድነት በማጠናከር መሪዎቹን በመደገፍና የመታገል አቅማቸውን በማሳደግ አማራ እንደአማራ ያለበትን ችግር ከመቅረፍ አልፎ ለአገራዊ ችግራችን ዓይነተኛ ሚና እንዲጫወት በማድረግ ከተመልካችነት ወደ ዋና ተጨዋችነት ማሸጋገር የሚቻልበትን እድል ማምጣት እየተቻለ ህዝቡን በመከፋፈል የአማራ ህዝብ መቆሚያ ለሌለው መከራ እያደረገው ያለው አንዱና ዋነኛው ኃይል ይህ ኃይል ነው፡፡"
"በየቤተክርስቲያኑና በየገዳማቱ የመደበቅን የፈሪ የትግል ስልትን ተግባራዊ በማድረግ በእምነታችን ላይ ሌላ ጠባሳ ለመፍጠር የሚያደርገው እንቅስቃሴ ሊወገዝና እንዲያቆም ሊደረግ ይገባዋል፡፡ ይህ ካልሆነ በተበታተነ መልኩ የሚደረግ ጩከት በአማራ ትግል ውስጥ ምንም ውጤት የማያመጣ ከመሆኑም በተጨማሪ ዕውቀት አልቦ የትግል ስልት በመሆኑ ሁሉም በያለበት ቆሞ በማሰብ እንደ አማራ በአንድነት በመቆም ለዘላቂ ውጤት መነሳሳት ይኖርብናል፡፡ የአማራ ህዝብ ካለበት ሁለንተናዊ ትግል አኳያ መደማመጥ፣ ልዩነትን አክብሮ በጋራ መቆምና ራስን ከተመልካችነት ወደተገዳዳሪነት ለማምጣት ይህን የተሳሳተ የትግል ስልት በመቀየርና በዕውቀት፣ በመደማመጥና መሪና ተመሪን በማክበርና ለችግሮቻችን የተለያዩ አዋጭ መንገዶችን በመቀየስ እንጂ አማራን በወንዜነትና በአካባቢያዊ ስሜት በመከፋፈልና መሪዎችን በመግደል የሚመጣ አንዳችም ለውጥ ሊኖር አይችልም፡፡"
"በመጨረሻም የአማራ ህዘብ ካለው የአስፋፈር ባህርይ አኳያ በመላ አገሪቱ የሚገኝ በመሆኑ የፖለቲካ ስልታችን ጥላቻን የሚያስቀድምና ጽንፈኝነትን እንደ ስልት የሚከተል ሊሆን አይገባውም፡፡ ይልቁንስ አማራ ያለውን እውነተኛ የአቃፊነት ባህል በማሳደግና ህብረ ብሄራዊነትን ይበልጥ በማጉላት እንዲሁም ከተበታተነ አስተሳሰብና ተግባር በመውጣት በአንድነት ቆመን በአማራ ህዝብ በተናጠል በኢትዮጵያ እንደአገር እየደረሰብንን ያለውን ጫና ለመመከት በጋራ ልንቆም ይገባል ለማለት እንወዳለን፡፡"
ስለሞጋሳነት ጠቃሚነት እና ብልህነት¡¡¡¡
«ከብልጠት ይልቅ በብልሃት እስከ ችግር ፈቺ ብስለ!
**************************************
"የፓርቲያችን ተቀዳሚ የሀሳብ መሰረቱ ሰው ተኮር መሆን ወይም ልከኛ ሰው መሆንን በስራ በመገለጥ ማሳየት ነው።
ፓርቲያችን ብልጽግና እንደ እሳት በሚጋረፉ እንደ ሚንተከተክ የሴራ ፍም ሃገርንና ህዝብን ወደ ማጥ በሚያነቅፉ ፈተናዎች አልፏል። በኢትዮጵያ የፖለቲካ መልክአ የእኔ ብቻ በሚል የትናንት ትርክት ላይ የቆሙ ፍላቶች ብልጽግናን የበለጠ እያበሰሉት እንጂ አያደክሙትም። ብርታት የሆነዉም ብልጽግና በብሀሪዉ ከእኔነት ይልቅ እኛነት ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ነዉ።"
"ብልጠትና ብልሃት ተቃርኗቸው ሰፊ ነው። ብልጠት ምክኒያታዊ ያልሆነና ከሚፈላው ውኃ ሙቀት የበለጠ ሃይል በማውጣት የሚደረግ ችግርን የሚያላምድ እንጅ መፍትሄ የማይበይን ሰንካላ ውሳኔ ነው። ብልሃት ደግሞ ከብልጥነት በብልህነት የተዋጀ ችግርን ከመላመድ ይልቅ ፈተናን ከመቋቋም እስከ ማለፍ ከማለፍ ደግሞ ልምድ ቀስሞ እስከማሻገር የሚደርስ ነው። ብልሃት በስልታዊነት የሚጠነጠን የስልጡንነት መለያ ቀለምም ነው።"
"በተቃርኖ የተቃኛ የፖለቲካ አሰላለፍ የሚፈታዉ በብልጠት ሴይሆን በብልሀት መሆኑን የተረዳዉ ብልጽግና ከችግሮች እና ከፈተናዎች ከፍ ብሎ የሚታይ አኩሪ ስራ ሰርቷል እየሰራም ይገኛል። ይህ አንኳር ተግባር በፓርቲ ፕሮግራም ብቻ የሚቀመጥ ሳይሆን ለዚህ አይነተኛ መፍትሄ መስጠት የሚችሉ መሪዎቹን ከፊት በማሰለፍ አይደለም ለወዳጅ ለጠላት ከሩቅ የሚታዩ አኩሪ ተግባራትን እየፈጸመ ይገኛል።
ብልጽግና በኢትዮጵያ ፓለቲከዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ መልክዓ በበርካታ ፈተናዎች ውስጥ አልፏል፣ እያለፈም ነው። እነዚህን ፈተናዎች ሲሻገር እኔነት ላይ ብቻ የተመሰረቱ ፍላቶች እንደ እሳት ቢገርፉትም መውጫ መንገዱን ያለውን ሁሉ ኃይልና ጊዜ ችግርን ተለማምዶ በመቆየት የቅርብ አዳሪ ግብት ሳይሆን ፈተናን የመቋቋም ስሪቱን ጊዜንና ኃይልን ከተገቢው ስልት ጋር ደምሮ ከፈተናው የመውጣት ዘመን የሚሻገር ብልሃት ነው። ይህም ብልጽግናን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎች የማያጠፉት ሳይሆን ያበሰሉት ፓርቲ አድርጎታል። "
"አሁንም ነገም በጠላት የሚሸረቡ ሴራዎች እና ፈተናዎች ፓርቲያችንን አያስፈሩትም። ምክኒያቱም የመጀመሪያውና በፓርቲው መሪነትም መሪዎችም የሚወሰደው ብልሃት ችግርን ቀድሞ መከላከል ላይ ያተኮረ በመሆኑ ነው። ከተፈጠረም በኋላ ችግርን በመለማመድ የከንቱዎች ብልጠት ላይ አያተኩርም። ይልቁንም የችግሩን መነሻና የተጽዕኖ መጠነ ዙሪያ ከማጥናት እስከ ማወቅ፣ ከማወቅም ተቋቁሞ እስከ መውጣት ባለ የብልሃት ማጠንጠኛ ውስጥ ይበስላል ለነገም መደላድል ይሰራል።
በዚህ ውስጥ የተሰጠንን ልዩ ችሎታ ብቻ ሳይሆን ያለንን ጊዜና ሃይል አውቆ በብልሃት መወሰን የመሪነት ጥበባችን የፊት ገጽ ላይ መንበር አለበት። "
"አሁን በአማራ ክልል የገጠመውን አይነት ፈተና ፓርቲው ከዚህ በፊት ገጥሞታልም አልፎታልም። የችግሩ መንስኤም ግራ ዘመም ብሄርተኝነትና የጽንፍ ፓለቲካ ነው። ለዚህ ደግሞ ፓርቲው ከብልጠት ይልቅ የብልህ መፍትሄ አስቀምጧል።
ከጽንፈኛ ብሄርተኝነት ይልቅ ሁሉን አቃፊ ወደ ሆነውና ህዝቦች የሚከባበሩበት፣ ሃገር የሚያፈርሱ ስሁት ትርክቶችን ሃገር በሚገነባ ታላቅና የጋራም ትርክት ወደ ሚሻሩበት ብሄራዊነት የመሻገር ጊዜ አሁን መሆኑንም ተረድቷል። "
"ይህን ብልሃትና ብስለት መጠቀም ሃገርና ህዝብ የባዕድ ጽንፍን እንዲላመዱ ሳይሆን ተቋቁመው ከፈተናው የሚሻገሩበት ነውና መላው የፓርቲው አመራርና ስላም ወዳዱ ህዝባችን ጽንፈኞችን በቃችሁ የሚሉበት ጊዜ አሁን ነውና በህብረት፣ በውጤታማነት አብረን እንቁም።
ይህ ብልሃት ደግሞ ዕዳውንና ምንዳውን የለየ ነው። የሚያሳርፋቸው ውሳኔዎች አዕማዳትም ስላምን የማስቀደም፣ ሃብትን ከመለየት በልህቀት እስከ ማስተዳደር የሚዘልቁ፣ ስሁት ትርክትን ሽረው የታላቅ ሃገር ትርክትን የሚበይኑ፣ የጊዜን ውጤት የዋጁ፣ ለቴክኖሎጂ ቀናኢ የሆኑና ለበጎ ለውጥ ጡብ የሚያስቀምጡ ናቸው።
ሰላም ከሁሉም፣ ሰላም ለሁሉም!!»
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ