የነገረ ግብጽን እና ሱዳን ጉዳይ በሚመለከት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር #ከፈጠረው #ቅንነት እና #ደግነት በላይ ናት።
የነገረ ግብጽን እና ሱዳን ጉዳይ በሚመለከት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር #ከፈጠረው #ቅንነት እና #ደግነት በላይ ናት። አቤቱ አምላኬ ሆይ! "በቸርነትህም ምራኝ።" ዕውነት ለመናገር አገረ ግብጽን በሚመለከት የኢትዮጵያ መንግሥታት ሁሉ በባዛ #ቅንነት ፤ በገዘፈ #ትዕግስት መጠኑን ባለፈ #የመቻል አቅም ነው ኢትዮጵያ የገጠማትን፤ የሚገጥማትን ችግር ሁሉ ያስተናገደችው። እንዲያውም ሥልጣን ላይ የነበሩ፤ አሁንም ያሉ የፖለቲካ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢሊቶች ለተፎካካሪያቸው ሆነ ለተቃዋሚ የፖለቲካ #ዕሳቤወች ሆነ #ተቋማት በዚህ ያህል ቅንነት፤ በዚህን ያህል ትዕግስት፤ በዚህ የመቻል አቅም #ጥያቄወቻቸውን ለማስተናገድ እንደምን እንዳልቻሉ፤ እንደማይችሉም ግርም ይለኛል። የሃሳብ ልዩነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ለሞት፤ ለእስራት፤ ለመገለል፤ ለመሰወር ይዳርጋል። ዕውነት ለመናገር ለግብጽ ኢትዮጵያ #የእናት ያህል ነው ጥያቄወቿን ሁሉ ስታስተናግድ የኖረችው። የአባይ ግድብ ከሃሳቡ እስከ ፍፃሜው እጅግ በሚደንቅ፤ በሚያስደም ብልህነት ነው ኢትዮጵያ የከወነችው። ይልቅ ኢትዮጵያ ማድረግ ያለባት የገለልተኛ አገራትን ባለሙያወች በህይወት እያሉ በክብር ጋብዛ #መሸለም እንዲሁም የምስክርነት ተመክሧቸውን ቃለ - ምልልስ በማድረግን በፍጥነት ልትከውን ይገባታል ባይ ነኝ። አጤ አባይን በሚመለከት ያን የመሰለ #የህሊና በሳል ቅድመ ዝግጅት እና #ስኩን ክንዋኔም በዶክመንተሪ በፍጥነት ዘገባው ሊሠራ ይገባዋል ባይ ነኝ። ለዕውነት #ፈጣን መሆን ያስፈልጋል። ውሸት ሲደራረብ ዕውነት ይመስላል እና። በዘንድሮው የተመድ ጉባኤም ሆነ ከዛ በፊት በማደምጣቸው ጉዳዮች በግብጽ በኩል ኢትዮጵያ #ተጫኝ...