የነገረ ግብጽን እና ሱዳን ጉዳይ በሚመለከት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር #ከፈጠረው #ቅንነት እና #ደግነት በላይ ናት።

 

የነገረ ግብጽን እና ሱዳን ጉዳይ በሚመለከት ኢትዮጵያ እግዚአብሄር
#ከፈጠረው #ቅንነት እና #ደግነት በላይ ናት።
 
አቤቱ አምላኬ ሆይ! "በቸርነትህም ምራኝ።"
 
 May be an image of map and text that says 'SAUDI ARABIA RED REDSEA SEA SUDAN ERITREA Asmera Sanaa YEMEN Debre Bahir Dat Mekalo Maychew. Alamata Weldya Dase Debre Markos Kambolcha fithe Oire OrHo Finchas Nekante Addis Ababa Dembide Metu Akaki* Nazret GoreApera&ia Asela® Wenji ETHIOPIA Sodo, Goba :ingaAlem Alem irga ArtaMinch® Arda *KitreMengiat Harer SOUTH SUDAN SOMALIA UGANDA KENYA Equator'
 
ዕውነት ለመናገር አገረ ግብጽን በሚመለከት የኢትዮጵያ መንግሥታት ሁሉ በባዛ #ቅንነት፤ በገዘፈ #ትዕግስት መጠኑን ባለፈ #የመቻል አቅም ነው ኢትዮጵያ የገጠማትን፤ የሚገጥማትን ችግር ሁሉ ያስተናገደችው። እንዲያውም ሥልጣን ላይ የነበሩ፤ አሁንም ያሉ የፖለቲካ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ኢሊቶች ለተፎካካሪያቸው ሆነ ለተቃዋሚ የፖለቲካ #ዕሳቤወች ሆነ #ተቋማት በዚህ ያህል ቅንነት፤ በዚህን ያህል ትዕግስት፤ በዚህ የመቻል አቅም #ጥያቄወቻቸውን ለማስተናገድ እንደምን እንዳልቻሉ፤ እንደማይችሉም ግርም ይለኛል። የሃሳብ ልዩነት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ለሞት፤ ለእስራት፤ ለመገለል፤ ለመሰወር ይዳርጋል።
 
ዕውነት ለመናገር ለግብጽ ኢትዮጵያ #የእናት ያህል ነው ጥያቄወቿን ሁሉ ስታስተናግድ የኖረችው። የአባይ ግድብ ከሃሳቡ እስከ ፍፃሜው እጅግ በሚደንቅ፤ በሚያስደም ብልህነት ነው ኢትዮጵያ የከወነችው። 
 
ይልቅ ኢትዮጵያ ማድረግ ያለባት የገለልተኛ አገራትን ባለሙያወች በህይወት እያሉ በክብር ጋብዛ #መሸለም እንዲሁም የምስክርነት ተመክሧቸውን ቃለ - ምልልስ በማድረግን በፍጥነት ልትከውን ይገባታል ባይ ነኝ።
 
አጤ አባይን በሚመለከት ያን የመሰለ #የህሊና በሳል ቅድመ ዝግጅት እና #ስኩን ክንዋኔም በዶክመንተሪ በፍጥነት ዘገባው ሊሠራ ይገባዋል ባይ ነኝ። ለዕውነት #ፈጣን መሆን ያስፈልጋል። ውሸት ሲደራረብ ዕውነት ይመስላል እና። በዘንድሮው የተመድ ጉባኤም ሆነ ከዛ በፊት በማደምጣቸው ጉዳዮች በግብጽ በኩል ኢትዮጵያ #ተጫኝ፤ ውሃን በሚመለደት የዓለም ዓቀፍ ህግጋትን #የማታከብር ብቻ ሳይሆን የውስጡን የክሱን ዕድምታ ቢመረመር ግብጽ ኢትዮጵያን #በሰባዕዊ መብት ጉዳይም አተኩራ አያታለሁኝ። 
 
የብልጽግናው መንግሥት የአባይ ግድብን በሚመለከት ፕሮፖጋንዲስት አያስፈልገውም። እኔ #ሰላማዊ ሰልፎች እራሱ የነበረውን የገዘፈ አገራዊ፤ ብሄራዊ ስሜት #አቀዝቅዞታል ባይ ነኝ። ደረጃውንም ዝቅ አድርጎታል ባይ ነኝ። የመካሪ #ማጣት እንጂ በፍጹም ሰላማዊ ሰልፋ #አስፈላጊ አልነበረም። 
 
የተናጋሪወች ስንኛት እራሱ "ሙያ በልብን" የጎንደሮችን ብሂል ያልጠበቀ ነበር። የፈጸመ አካል ስኬቱን በጸጥታ፤ በአርምሞ፤ በጸሎት፤ በሱባኤ፤ በድዋ ድልዳል በመሥራት ጥበቃ ሊያደርግለት ይገባ ነበር። ዓለም ዓቀፍ ፍጥጫ ላይ #የተጣደ ስኬት በንግግሩ፤ በአረማመዱ ጥንቃቄ ይጠይቅ ነበር። አንዳንድ አገላለፆች ያልተገቡ ነበሩ። ለዚህም ነበር እኔ ኢትዮጵያን እንኳን ደስ አለሽ ስል፤ ደስታን በጥንቃቄ #የማስተዳደርን አስፈላጊነት በአጽህኖት የገለጽኩት። 
 
የሆነ ሆኖ ዓለም ዓቀፋ የፍትህ ሥርዓት የሰወች ስብስብ ስለሆነ ኢትዮጵያ መረጃወቿን ከገለልተኛ ተሳታፊ አገሮች #ምስክርነት ጋር አዋዳ፤ የህግ፤ የውሃ ጉዳይ ባለሙያወቿን አቀናጅታ ከሠራች ግብጽም ሆነ የሱዳን አንዱ ክንፍ #ይሸነፋል። እንዲያውም ኢትዮጵያ ግብጽ ሆነ ሱዳን ግድባቸውን ሲሰሩ ከመረጃ፤ ከፈቃድ ውጪ መሆኗን ልትጠይቅ ይገባታል። ልባም ህሊና ከተገኜ።
 
በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ለህዝቡ የገባችውን #ቃል የመፈጸም ግዴታን ለይደር አለመቅጠርም ወሳኝ ጉዳይ ይመስለኛል። የገረመኝ ግብፆች "#ታግሰናል" ያሉት ጉዳይ ነው። ከተፈጠሩ ጀምሮ በግብጽ የፖለቲካ ኢሊቶች ኢትዮጵያን #ከመነሰት፦ አብዝተው #ከመቀናቀን የታቀቡበት ዘመን ቢፈለግ የሚገኝ አይመስለኝም። አቨይ አባቴ ገና ልጅ ሆኜ ነበር ይህን ይነግረኝ የነበረው። የሆነ ሆኖ ጠንቃቃ፤ እላፊ የማይሄድ ሰብዕና ለዚህ ፕሮጀክት ስንቁ ሊሆን ይገባል ባይ ነኝ። የBBC ዘገባ እንሆ ……… #ፎቶው የእኔ ምርጫ ነው።
 
ሥርጉትሻ 2025/09/30
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
"ግብፅ "የግድቡን ጉዳይ ወደ ዓለም አቀፍ የፍትሕ ፍርድ ቤት እወስዳለሁ" ማለቷን ኢትዮጵያ አጣጣለች"
"በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ ተወካይ ዮሴፍ ካሳዬ …."
"የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ በተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያ በታላቁ ሕዳሴ ግድብ ምክንያት "በታችኛው ተፋሰስ የሚኖሩ የሚሊዮኖችን ሕይወት አደጋ ላይ ጥላለች" ብለው በመክሰስ አገራቸው ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፉ የፍትሕ ፍርድ ቤት እንደምትወስድ ተናገሩ።
በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ ተወካይ ዮሴፍ ካሳዬ ለግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት ምላሽ፤ "ግብፅ ስለ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ያደረገችው ንግግር መሠረት አልባ እና አሳሳች ነው" ሲሉ አጣጥለዋል።
ግብፅ "ስለ ታላቁ ሕዳሴ ግድብ ተዓማኒ ያልሆኑ ክሶችን በተደጋጋሚ ወደ ተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት አቅርባለች" ሲሉም አክለዋል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፤ ኢትዮጵያ "በዓባይ ላይ የተናጠል እርምጃ ወስዳ ግድብ በመገንባት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የግብፅ እና የሱዳን ሕዝቦችን ሕይወት አደጋ ላይ ጥላለች" ብለዋል።
የተባበሩት መንግሥታት 80ኛ ጠቅላላ ጉባዔ በተካሄደበት ወቅት የሁለቱ አገራት ተወካዮች ጠንካራ ቃላትን ተለዋውጠዋል። ግብፅ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ እና በምሥራቅ ናይል ተፋሰስ "አፍራሽ የተናጠል ፖሊሲ" እየተከተለች ነው ስትል ከሳለች።
የሕዳሴ ግድቡ ግንባታ መጠናቀቅ ለታችኛው ተፋሰስ አገራት "አደጋ የደቀነ" ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። በተመድ የኢትዮጵያ ምክትል ቋሚ ተወካይ #ዮሴፍ ካሳዬ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ግድቡን በተመለከተ በተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ሕግና መርሕን በሠረት በማድረግ ምላሽ መስጠቷን አንስተዋል።
አምባሳደር ዮሴፍ "የኢትዮጵያ ዘላቂ የትብብር ፖሊሲ እና የግብፅ አዋኪነት ያላቸው ልዩነት ግልጽ ነው" ሲሉም አክለዋል። ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ያላት በአቋም ዓለም አቀፍ ሕግጋት እና በእኩል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ እንደሆነም ገልጸዋል።
የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በበኩላቸው "ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ሕግን መጣስ መርጣለች። በተናጠል ፖሊሲዋ የአፍሪካ ቀንድና የምሥራቅ ናይል ተፋሰስን እያወከች ነው" ብለዋል።
ግድቡ በተመረቀበት ዕለት ግብፅ ለተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ባስገባችው ይፋዊ ደብዳቤ ላይ ግድቡን "ሕገ ወጥ የተናጠል እርምጃ የተወሰደበት" በማለት ገልጻለች።
በደብዳቤው ላይ ግብፅ ለዓመታት ጉዳዩን "በዲፕሎማሲ እና እንደ ተመድ ባሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት አማካኝነት ለመያዝ" መሞከሯን ጠቅሳለች።
ግብፅ "ለዓመታት ትዕግስት ያሳየችው ደካማ ስለሆነች ሳይሆን በዓባይ ተፋሰስ አገራት መካከል በሚኖር ትብብር ስለምታምን ነው" በሚልም በደብዳቤው ተመልክቷል።
አምባሳደር ዮሴፍ ለግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሰጡት ምላሽ "ግብፅ ከቅኝ ግዛት ስምምነት የተወረሰ 'ታሪካዊ መብት' አለኝ በሚል የተፋሰሱን አገራት አግልላች" ብለዋል።
ኢትዮጵያ የዓባይን ወንዝ ለኃይል አቅርቦት፣ ለምግብ ደኅንነትና ለንጹሕ የመጠጥ ውሃ ተደራሽነት እንደምትጠቀም ጠቅሰው፤ ግብፅ ግን "ይህንን መብት ለመንፈግና በዓባይ ላይ በብቸኛነት ተጠቃሚ ለመሆነ ትሻለች" በማለት ከሰዋል።
ኢትዮጵያ የግድቡን ግንባታ በተመለከተ ከግብፅ ጋር ምክንያታዊ ስምምነት ላይ ለመድረስ በተደጋጋሚ ንግግር ማድረጓን አምባሳደሩ አጣቅሰዋል።
አያይዘውም ግብፅ ለቀጣናው አገራትን ሰላም እና ትብብር "ዋጋ እንደማትሰጥ" እንዲሁም በአጎራባች አገራት መካከል "አለመረጋጋት እንዲፈጠር የጦር መሣሪያ በማቅረብ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነትን እንደምታራምድ" ከስሰዋል።
የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጉዳይ "ዓለም አቀፋዊ" ለማድረግ እየሞከረች እንደሆነ የተናገሩት አምባሳደር ዮሴፍ፤ ግብፅ የተመድን መድረክ "ለጠባብ የፖለቲካ ግብ" እንዳዋለች እንዲሁም ይህንንም "ለአገር ውስጥና ቀጣናዊ ጉዳዮች ትኩረት እንዳይቸር ለማድረግ እንደምትጠቀምበት" ገልጸዋል።
ግብፅ በኃይል ከተሞላ አካሄድ ይልቅ ገንቢ በሆነ አካሄድ ላይ እንድታተኩርም አሳስበዋል። የግብፁ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አገራቸው በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ለግድቡ ጉዳይ እልባት ለመስጠት ዝግጁ ብትሆንም ኢትዮጵያ ለመተባበር ፈቃደኛ እንዳልሆነች ጠቅሰዋል።
"በዓለም አቀፍ ሕግ ለመዳኘት ዝግጁ ከሆኑ እኛም ጉዳዩን በሕግ ለመያዝ ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነን። እውነታው ግን [በኢትዮጵያ በኩል] እንዲህ ያለ ፍላጎት አለመኖሩ ነው" በማለት አክለዋል።
በተመድ ስምምነት እና በዓለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት ግብፅ ከዓባይ ወንዝ ጋር በተያያዘ ደኅንነቷን የማስጠበቅ መብት እንዳላት ተናግረዋል።
"ኢትዮጵያ በማዘናጋት የሚሊዮኖችን ሕይወት አደጋ ላይ ጥላለች። መብታችን ሲጣስ ዝም አንልም" ብለዋል ሚኒስትሩ።
ሱዳን በ2021 ግብፅ በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት በከፈተችው አቤቱታ ላይ የተቀላቀለች ሲሆን በ2025 ደግሞ ሱዳን በተናጠል ጉዳዩን ወደ ምክር ቤቱ ወስዳዋለች።
ከዚህ ቀደምም እአአ በ2020 ግብፅ የታላቁ ሕዳሴ ግድብን ጉዳይ ወደ ተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት መውሰዷ ይታወሳል።
በ2021 በግብፅ እና በሱዳን የጋራ ጥያቄ ምክር ቤቱ በግድቡ ዙርያ ውይይት አድርጓል። ኢትዮጵያ እየወሰደች ያለው "የተናጠል እርምጃ ለቀጣናው መረጋጋት አደጋ ነው" ሲሉ አገራቱ ከስሰዋል። የፀጥታው ምክር ቤት ውይይት ሦስቱ አገራት "የሦስትዮሽ ተቀባይነት ያለው አሳሪ ስምምነት" ላይ እንዲደርሱ ምክረ ሐሳብ ቢያስቀምጥም፤ አገራቱ ለዓመታት ያደረጓቸው ውይይቶች ውጤታማ አልሆኑም።"

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

የእኔ እማ ልዕልቴ እንዴት ነሽ?

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።