ልጥፎች

ከፌብሩወሪ, 2023 ልጥፎች በማሳየት ላይ

የቦረና ዞን የድርቅ ሁኔታ ****

ምስል
ከአቶ አሻግሬ ጌታቸው ዬተገኜ ነው። የቦረና ዞን የድርቅ ሁኔታ ****   በቦረና ዞን ወራጅ ወንዝ ሆነ የተፈጥሮ ሐይቅ የለም፡፡ የአካባቢው ማህበረሰብ እርሻ እና የመጠጥ ውሃ ምንጭ ከዝናብ የሚገኝ ብቻ ነው። በ2013 እና በ2014 ዓ.ም በተከታታይ ሁለት አመት የዝናብ ወቅቶች በማለፉ የተፈጠረ ድርቅ ነው፡፡ የመጀመሪያው አመት በእንስሳት ላይ ነበር ጉዳቱ የደረሰው ዘንድሮ ግን በሰው ህይወት ላይ ጉዳት ማድረስ ጀምሯል። 1) ምሳሌ በአንድ ቀበሌ ውስጥ የምግብ ድጋፍ ማግኘት የሚገባቸው ሰዎች ውስጥ ለግዜው እርዳታ እየቀረበ ያለው ከ30 ቤተሰቦች ውስጥ 5 ቤተሰብ ብቻ ነው፡፡ 2) ሕፃናት፣ አረጋውያን፣ ነፍሰ ጡር፣ የሚያጠቡ እናቶች በምግብ እጥረት ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ ይገኛል ለዚህ እየተሰጠ ያለው ድጋፍና የአልሚ ምግብ አቅርቦት ያነሰ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች ገልጸዋል፡፡ 3) በ2014 ዓ.ም ህጻናት ተማሪዎች 3,166 ወንዶች እና 2,743 ሴቶች በድምሩ 5,809 ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ አይደሉም፡፡ 4) አርብቶ አደር የሆነው ማህበረሰብ ለከብቶች ሳር እና ውኃ ፍለጋ፣ ከፊሉ ቤተሰብ ይዞ ከፊሉ ደግሞ አጎራባች ዞኖች ተሰደዋል፣ ወይም ወደሌላ ክልሎች ሂደዋል እስከ ጎረቤት ሀገር ኬንያ የተሰደዱ እንዳሉ ይገለጻል፡፡ 5) እስከ ሐምሌ 2014 ዓ.ም ድርስ በዞኑ 117,422 ሕፃናት እና 9,591 ነፍሰ ጡር (አጥቢ) እናቶች የምግብ እጥረት አጋጥሞቸዋል። **** የሶማሌ ክልል መረጃ ደሞ ከክልሉ ቢሮ ጠይቀን እናቀርባለን  

"በአማራ ክልል የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር፤ በከተማይቱ ያሉትን ተፈናቃዮች ማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አስታወቀ።

ምስል
#አሳረኛው አማራ።   ከአቶ እናት እና አባቴ ዬተገኜ ነው። "አስመሳይነት እና ከፍሎ አዛኝነት" "አስመሳዩ አክቲቪዝም የዘነጋቸው፣ ከ26 ሺህ የሚበልጡ የፋሺስቱ የኦሮሚያ አገዛዝ ተፈናቃዮች!" "በአማራ ክልል የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር፤ በከተማይቱ ያሉትን ተፈናቃዮች ማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አስታወቀ። ከሁለት ሳምንት ወዲህ ወደ ከተማይቱ የሚገቡ አዲስ ተፈናቃዮችን መቀበልም ሆነ ወደ መጠለያ ማስገባት ማቆሙንም የከተማይቱ አስተዳደር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል። ከአዲስ አበባ 130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የደብረ ብርሃን ከተማ፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከመንፈቅ ባሉት ጊዜያት በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ አራቱም የወለጋ ዞኖች እንዲሁም ከአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ስታስተናግድ ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በከተማይቱ በሚገኙ በስድስት ጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ 26 ሺህ ገደማ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ ከከተማይቱ አስተዳደር የተገኘ መረጃ ያመለክታል። ከምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ሲቡ ሲሪ ወረዳ ተፈናቅለው ለአንድ ዓመት ያህል በከተማይቱ ተጠልለው የሚገኙት አቶ አህመድ መሐመድ፤ ባለፉት 15 ቀናት ወደ ደብረ ብርሃን የመጡ ተፈናቃዮች መጠለያ ሳያገኙ መቅረታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። የከተማይቱ ኃላፊዎች “ህዝቡ ሲጨምር አንመዘግብም ብለዋል” ሲሉም ባለፉት ሁለት ሳምንታት ካሉበት መጠለያ ጣቢያ ሆነው የታዘቡትን አስረድተዋል። አቶ አህመድ ከተፈናቀሉበት ምስራቅ ወለጋ ዞን፤ ጉቡ ሰዮ ወረዳ የመጡት አቶ አስናቀ ጋሻው ይህንኑ አረጋግጠዋል። በግብርና ስራ ይተዳደሩ የነበሩት አቶ አስናቀ፤ በጸጥታ ችግር ምክንያት የመኖሪያ ቀያቸውን ለቅቀው ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ ከመ

ተረኝነት! ሲጠነዛ! የውጭ አገር ዩኒቨርስቲዎች ለኢትዮጵያ 30 የፒኤች ዲ ትምህርት እድል ይሰጣሉ።

  ተረኝነት! ሲጠነዛ! የውጭ አገር ዩኒቨርስቲዎች ለኢትዮጵያ 30 የፒኤች ዲ ትምህርት እድል ይሰጣሉ። የምልመላና የስፖንሰርሺፕ ሂደቱ እና ስምምነቱ በትምህርት ሚኒስቴር እና በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በኩል ነው የሚከናወነው። የዘንድሮው ስኮላርሽፕ የተሰጠው በሙሉ ለኦሮሞ ተወላጆች ብቻ ሲሆን የሁለቱ መስርያ ቤት ዋና ኃላፊዎች ሳያውቁ የተፈፀመ ነው። ከኦሮሞ ብልፅግና ሰዎች ውጭ ማንም እንዳያውቀው ተደርጓል። "የኦሮሞና ብሔር ብሔረሰብ ሲኖዶስ" ብለው ያዋቀሩት ከዚህ አንፃር ትንሽ ለማስመሰል ሞክረዋል። የትምህርት እድል የሰጡት አንድም የሌላ ብሔር ተወላጅ የለም። በአደባባይ ለማይወጣው አይናቸውን በጨው ያጠቡ ስግብግቦች ናቸው። አንድም ከሌላ አያሳትፉም። አንድም! ብሔር ብሔረሰብ እንጅሩ! ኬኛ ብቻ!

#የፊንጢጣ_ኪንታሮት

ምስል
  #የፊንጢጣ_ኪንታሮት ?? #በፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ሲያብጡ የሚፈጠር በሽታ ነው ይህ ችግር ከፍተኛ ህመምና ስቃይ አለው በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ የደም ቧንቧዎች ሲያብጡ ውስጣዊ ኪንታሮት ይፈጠራል በፊንጢጣ ቀዳዳዎች አካባቢ ሲያብጡ ደግሞ ውጫዊ ኪንታሮት ይፈጠራል፡፡ ሁለቱም አይነት ኪንታሮቶች በተመሳሳይ ጊዜ በአንድ ሰው ላይ ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡ በዳሌና ፊንጢጣ አካባቢ ያሉ የደም ቧንቧዎች ውጥረት ሲበዛባቸው ኪንታሮት ይፈጠራል፡፡ በፊንጢጣ ውስጥ የሚገኙ ጡንቻዎች በደም ይሞላሉ ይህም የአንጀትና ሆድ ዕቃ እንቅስቃሴን ለመቆጣጠር ያመቻል፡፡ ሽንት ቤት ውስጥ ለረጂም ጊዜ ተቀምጠን በምንቆይበት ጊዜ የውጥረት መጨመር በፊንጢጣ ጡንቻዎች ውስጥ ያሉትን የደም ቧንቧዎች እንዲያብጡና እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል ይህም ኪንታሮት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡ #የኪንታሮት_መነሻ_ምክንያቶች ኪንታሮት በአብዛኛው የሚከሰተው በዳሌና ፊንጢጣ አካባቢ የሚገኙ የደም ስሮች ላይ ጫና ሲጨምርባቸው ይፈጠራል፡፡ ግፊት በሚጨምርበት ጊዜ ደም ወደ ስሮቻችን ይገፋና እንዲያብጡ ያደርጋቸዋል፡፡ የሚከተሉት ልምዶች የደም ግፊትን በፊንጢጣ አካባቢ በመጨመር ኪንታሮት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፦ ሽንት ቤት ስንቀመጥ በጣም ማማጥና መቻኮል ቀጣይነት ያለው ተቅማጥ ወይም የሆድ ድርቀት ከመጠን ያለፈ ውፍረት በተለይ በሆድና ዳሌ አካባቢ እርግዝና እና ወሊድ በወሊድ ጊዜ ህፃኑን ገፍቶ ለማውጣት /ሲያምጡ በፊንጢጣ አካባቢ ውጥረት እንዲጨምር ስለሚያደርገው ለኪንታሮት ሊያጋልጣቸው ይችላል #የኪንታሮት_ምልክቶች በፊንጢጣ አካባቢ የማሳከክ እና የማቃጠል ስሜት ህመም ወይም ምቾት ማጣት በፊንጢጣ አካባቢ ማበጥ በፊንጢጣ አካባቢ እባጭ መኖር #ውስጣዊ_ኪንታሮት በፊ

እዮብያዊቷ እና ሚስጥሯ………

  እዮብያዊቷ እና ሚስጥሯ……… ከአቶ አዬለ ግዛቸው ያገኜሁት ነው። የዝዋይ ገዳም ኮሌጅ የተመሠረተው ለማን ነው ? --------------------------------- ( ታላላቅ ሊቃውንትን ያፈራ የቤተክርስቲያን ዐይን የሆነ የትምህርት ተቋም መሆኑን አውቃለሁ በዚህ ልክ ተዘርዝሮ በማየቴ ትልቅ ሥራ እየሠራ ያለ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሆኑን ተረድቻለሁ ሁሉም ሼር በማድረግ እውነትን ላልተረዱና ማወቅ ለሚፈልጉ አዳርሱ ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካሉ አምስት ኮሌጆች አንዱ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ ነው፡፡ ኮሌጆች ሲመሠረቱ ሀገር አቀፍና ዓለም ዓቀፍ ርዕይ ይዞ ነው የትኛውም ተቅዋም በቤ ክርስቲያን ሲመሠረት ምዕመናንን አድሬስ ያደረገና የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ አምልኮትዋ ሳይዘነጋ ነው የዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አጭር የታሪክ ዳሰሳ በሌላ ክታብ እንመለሳለን አሁን ግን ኮሌጁ እየሰጠ ያለውን ሰፊ አገልግሎት ለመጠቆም ነው የዝዋይ ገዳም በ1959 ዓ/ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የተመሠረተ ሲሆን በ1960 ዓ /ም ማስተማር ጀምሯል ። በ1966 የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ ተዘግቶ ቆይቷል በ1971 በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ አማካኝነት ዳግም ተከፍቷል ከዛን ጊዜ ጀምሮ በሺ የሚቆጠሩ መምህራንን ለቤተ ክርስቲያን አስረክቧል ገዳሙ ትንሿ ኢትዮጵያ ናት የገዳሙን ውሃ ጠጥቶ ስልጠናውን ወስዶ በሳል ሰባኪ ያልሆነ የለም በመላው ዓለም ያለችውን ቤተ ክርስቲያን በማገልገል ያሉ ሊቃነ ጳጳሳት ፡ ቆሞሳት ፡ሰባክያነ ወንጌል ፡ ካህናት ዲያቆናት ምስክር ናቸው በዝዋይ ገዳም ዘር ቀለም የለም በዝዋይ ገዳም የሚያድጉ ወላጅ አጥ ሕፃናት ከሁሉም ቤተ እምነት መጥተው ነው የሚያድጉት ቀደምት

የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሃዊ እና ህጋዊ ብቻ ሳይሆን የትግሉ አስኳል እና "የአገራዊ ለውጡ" ቀንዲል

  "ሁላችንም ሁልጊዜም አሸናፊዎች እስከምንሆን እንታገላለን!" የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው እና የዞኑ ም/አስተዳዳሪ እና የሰላም እና ደህንነት ኃላፊ እንዲሁም የኮሚቴው ሊቀመንበር ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በተገኙበት በጎንደር ከተማ የካቲት 17/2015 ያካሄደውን ህዝባዊ ውይይት ተከትሎ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ከውይይት በኋላ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ በሚከተለው መልኩ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል:_ እኛ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የካቲት 17/2015 በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማችን ተሰባስበን "በፈተና እንጸናለን፣ በስራም እንገለጣለን"፣ "ዘላቂ የህግ አሸናፊነት" በሚል ርዕስ ከመከርን በኋላ የሚከተለውን ባለ አስር ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል። 1) የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍጹም ፍትሃዊ እና ህጋዊ መሆኑን በማመን እስከ መጨረሻው ከወገኖቻችን ጋር ጸንተን ለመቆም ተስማምተናል። 2) ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ሁሉ ከዚህም በኋላ ለሚደረገው የወልቃይት አማራ ማንነት ትግል የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ እና ማንኛውንም ተልዕኮ ለመቀበል ቃል እንገባለን። 3) የወልቃይት ጠገዴ ትግል ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን በመቶ ሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ሰማዕት የሆኑበት መሆኑን በመረዳት የትግሉን ሰማዕታት አደራ ለመጠበቅ እንተጋለን። 4) የማንነት ትግሉ ፍጹም ፍትሃዊ እና ህጋዊ በመሆኑ ሌሎች ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የጥያቄው ተጋሪ እንዲሆኑና ከፍትህ ጎን እንዲቆሙ እውነታውን ለማስገንዘብ እንሰራለን። 5) የማንነት ትግሉ

የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበሩት አፄ ምኒልክ ከሰሯቸው ድንቅ ስራዎች መካከል የሚከተሉትን ለመጀመሪያ ለኢትዮጵያዊያን አበርክተዋል።አስተዋውቀዋል።

ምስል
  የኢትዮጵያ ንጉሥ የነበሩት አፄ ምኒልክ ከሰሯቸው ድንቅ ስራዎች መካከል የሚከተሉትን ለመጀመሪያ ለኢትዮጵያዊያን አበርክተዋል።አስተዋውቀዋል።   1835 ዓ.ም. ---------------------ወፍጮ 1882 ዓ.ም. ---------------------ስልክ 1886 ዓ.ም. ---------------------ፖስታ 1886 ዓ.ም. ---------------------ባህር ዛፍ 1886 ዓ.ም. ---------------------ገንዘብ 1886 ዓ.ም. ---------------------የውሃ ቧንቧ 1887 ዓ.ም. ---------------------ጫማ 1887 ዓ.ም. ---------------------ድር 1887 ዓ.ም. ---------------------የሙዚቃ ት/ቤት 1887 ዓ.ም. ---------------------የፅህፈት መኪና 1889 ዓ.ም. ---------------------ኤሌክትሪክ 1889 ዓ.ም. ---------------------ዘመናዊ ህክምና 1889 ዓ.ም. ---------------------ሲኒማ 1889 ዓ.ም. ---------------------የሙዚቃ ሸክላ 1889 ዓ.ም. ---------------------ቀይ መስቀል 1890 ዓ.ም. ---------------------ሆስፒታል 1893 ዓ.ም. ---------------------ባቡር 1893 ዓ.ም. ---------------------ብስክሌት 1896 ዓ.ም. ---------------------መንገድ 1897 ዓ.ም. ---------------------ፍል ውሃ 1898 ዓ.ም. ---------------------ባንክ 1898 ዓ.ም. ---------------------ሆቴል 1898 ዓ.ም. ---------------------ማተሚያ 1898 ዓ.ም. ---------------------ላስቲክ 1899 ዓ.ም. -------------

#አናባቢ #ሰዋሰው።

ምስል
#አናባቢ #ሰዋሰው ። "አድርገህልኛል እና አመሰግንኃለሁ"   ጌታ ብላቴ ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን በሥጋ ዬተለዬበት ዕለቱን ሲታሰብ ኢትዮጵያ በምን ሁኔታ ላይ ትገኛለች??? በአፀደ ነፍስ የቅኔው ልዑል፦ ፓን አፍሪካኒስቱ ጋሼ ፀጋዬስ በምን ሁኔታ ይገኝ ይሆን? #ይከፋል ። በሌላ በኩል ትውልዱ የቀደምትነት ቃናውን በመሻት ላይ ስለሚገኝ ይጽናናልም። የቅኔው ንጉሥን ጋሼ ፀጋዬን በሥጋ መለዬት መታሰቢያውን በሥሙ በተሰዬመው 15ኛ ዓመቱን በያዘው በሲዊዘርላንድ ዙሪክ ክፍለ አገር ከ20 በላይ ቋንቋወችን በሚያስተናግደው፦ ለ24 ሰዓት አገልግሎት በሚሰጠው በራዲዮ ሎራ በዕለተ ሃሙስ ክፍል አንድ መሰናዶ ቀርቧል። ክፍል ሁለት ደግሞ በቀጣዩ ጊዜ ከዓለም ዓቀፍ ዬሴቶች ቀን ማርች ስምንት ጋር ይቀርባል። ቀኑ ባይገጣጠምም መታሰቢያው ግን ቀድሞ ተከውኗል። ይህ ሳልደክም ለተከታታይ 16 ዓመት ሠርቸበታለሁኝ። www.lora.ch.tsegaye ፀጋዬ ራዲዮ በ97.5 መካከለኛ ሞገድ በወር ሁለት ጊዜ በዕለተ ቅዱስ ሃሙስ በወር ሁለት ጊዜ እኤአ ሰዓት አቆጣጠር ከ15.00-16.00 በአማርኛ ቋንቋ ይቀርባል። እጅግ ብዙ ፈተናወችን ትናንትም ዛሬም እያስተናገደም ይገኛል። ብቸኛው የኮሚኒቲ ራዲዮ በሎሬቱ ፀጋዬ ገ/ መድህን ዬሚጠራ ራዲዮም ነው። ፈተናውም ዝልቅ የሆነው ለዚህ ነው። ለትርፍ አይደለም የሚሠራው። እንዲያውም እዬከፈልኩ ነው የምሠራበት። የኢትዮጵያ መንፈስን ጥሪቱ ስላደረገ። መሰናዶው በብሄራዊ ጉዳይ ላይ ዬሚያተኩር ሲሆን በሰባዕዊነት ላይ አብዝቶ ያተኩራል። በታሰሩ ወገኖች ላይም ተግቶ ሙሉ 15 ዓመቱን ሰርቷል። አንድም ቀን በመሰናዶው የግለሰቦች ሥም አይጠራም። ከሚሞገተው ከኢትዮጵያ መንግሥት፤ ዬዬዘመኑ መሪወች በስተቀር። ዬፀጋዬ ራዲዮ እኤአ በ2008 በወርኃ