የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሃዊ እና ህጋዊ ብቻ ሳይሆን የትግሉ አስኳል እና "የአገራዊ ለውጡ" ቀንዲል

 

"ሁላችንም ሁልጊዜም አሸናፊዎች እስከምንሆን እንታገላለን!"
የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች
አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ
የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ/ም
አዲስ አበባ ሸዋ
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው እና የዞኑ ም/አስተዳዳሪ እና የሰላም እና ደህንነት ኃላፊ እንዲሁም የኮሚቴው ሊቀመንበር ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በተገኙበት በጎንደር ከተማ የካቲት 17/2015 ያካሄደውን ህዝባዊ ውይይት ተከትሎ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ከውይይት በኋላ በወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ በሚከተለው መልኩ አቋማቸውን ይፋ አድርገዋል:_
እኛ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የካቲት 17/2015 በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማችን ተሰባስበን "በፈተና እንጸናለን፣ በስራም እንገለጣለን"፣ "ዘላቂ የህግ አሸናፊነት" በሚል ርዕስ ከመከርን በኋላ የሚከተለውን ባለ አስር ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥተናል።
1) የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍጹም ፍትሃዊ እና ህጋዊ መሆኑን በማመን እስከ መጨረሻው ከወገኖቻችን ጋር ጸንተን ለመቆም ተስማምተናል።
2) ከዚህ በፊት እንዳደረግነው ሁሉ ከዚህም በኋላ ለሚደረገው የወልቃይት አማራ ማንነት ትግል የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ እና ማንኛውንም ተልዕኮ ለመቀበል ቃል እንገባለን።
3) የወልቃይት ጠገዴ ትግል ዛሬ የተጀመረ ሳይሆን በመቶ ሽህዎች የሚቆጠሩ አማራዎች ሰማዕት የሆኑበት መሆኑን በመረዳት የትግሉን ሰማዕታት አደራ ለመጠበቅ እንተጋለን።
4)
የማንነት ትግሉ ፍጹም ፍትሃዊ እና ህጋዊ በመሆኑ ሌሎች ፍትህ ወዳድ ኢትዮጵያዊያን የጥያቄው ተጋሪ እንዲሆኑና ከፍትህ ጎን እንዲቆሙ እውነታውን ለማስገንዘብ
እንሰራለን።
5)
የማንነት ትግሉ ፍትሃዊ እና ህጋዊ በመሆኑ ሌሎች ሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት እውነታውን ተገንዝበው ከፍትህ እና ከእውነት ጎን እንዲቆሙ እንሰራለን።
6)
ትግሉ ለጥቂት ግለሰቦች የሚሰጥ እና የውስን ጊዜ እንዳልሆነ እንገነዘባለን።
ስለሆነም የማንነት ትግሉ የሁላችንም የሁልጊዜም እና አሸናፊ እስከምንሆንበት የምንቀጥልበት መሆኑን በማመን እያንዳንዳችን የትግሉ መሪ ተዋናኞች መሆናችንን በተግባር እናረጋግጣለን።
7)
አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው ፍትህ ሲሰፍን ነው።
ስለሆነም የትግራይ ወራሪ ኃይል ነባሩን የወልቃይት ጠገዴን አማራ አፈናቅሎ ያሰፈራቸውን፣ በህዝባችን ላይ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ወንጀል የፈጸሙ አካላት የሚመጡት ለፍርድ ካልሆነ በስተቀር ወንጀለኞች በተፈናቃይ ስም ተመልሰው ዳግም ህዝባችንን እንዲጨፈጭፉ የማንፈቅድ መሆናችንን እንገልጻለን።
8
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሃዊ እና ህጋዊ ብቻ ሳይሆን የትግሉ አስኳል እና "የአገራዊ ለውጡ" ቀንዲል በመሆኑ
ገዥው ብልጽግና ፓርቲ እና የሚመራው የኢፌድሪ መንግስት በእጁ ያሉትን የህግ ማዕቀፎች እና ሌሎች አስፈላጊ ሀቆችን ተቀብሎ ለጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ እስከመጨረሻው የምንታገል መሆኑን እናረጋግጣለን።
9)
ወራሪው ኃይል በተደጋጋሚ ከስህተቱ ባለመማር እንደተለመደው በእብሪት ተነሳስቶ በህዝባችን ላይ ወረራ ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን በመገንዘብ ዋነኛው ሰራዊታችን ህዝባችን ነውና በሁሉም መዓዘን የሚኖረውን ህዝባችን አንቀሳቅሰን ከአሸባሪው ቡድን የሚፈጸምብንን ጥቃት እንዳመጣጡ ለመመለስ እና
ህልውናችን ለማስከበር እንሰራለን።
10)
የጎንደር ህዝብ በየዘመናቱ የጸረ እኩልነት እና ጸረ ፍትህ ኃይሎች ሰለባ ሲሆን የቆዬ ህዝብ ነው።
ስለመሆነም የግፈኞች የጭቆና ሰለባ በመሆናችን ሀገራችን ኢትዮጵያ አስተማማኝ ሰላም እና ሁለንተናዊ ልማት ሊረጋገጥ የሚችለው ፍትህ እና እኩልነት ሲረጋገጥ መሆኑን በማመን ሁልጊዜም ከፍትህ እና ከእኩልነት ጎን የምንቆም መሆናችንን እናረጋግጣለን።
ሁላችንም ሁልጊዜም አሸናፊዎች እስከምንሆን እንታገላለን!





  •  
    Shared with Public
    አባት ዓለም እንኳን አደረሰወት። እርስወ እኮ ድላችን ነወት።
    ክብሮቼ ደህና እደሩልኝ።
    ሥርጉትሻ አገልጋይ።

    አስተያየቶች

    ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

    ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

    እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

    አብይ ኬኛ መቅድም።