እዮብያዊቷ እና ሚስጥሯ………
እዮብያዊቷ እና ሚስጥሯ………
ከአቶ አዬለ ግዛቸው ያገኜሁት ነው።
የዝዋይ ገዳም ኮሌጅ የተመሠረተው ለማን ነው ?
---------------------------------
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካሉ አምስት ኮሌጆች አንዱ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ ነው፡፡ ኮሌጆች ሲመሠረቱ ሀገር አቀፍና ዓለም ዓቀፍ ርዕይ ይዞ ነው የትኛውም ተቅዋም በቤ ክርስቲያን ሲመሠረት ምዕመናንን አድሬስ ያደረገና የቤተ ክርስቲያንን ሁለንተናዊ አምልኮትዋ ሳይዘነጋ ነው
የዝዋይ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም አጭር የታሪክ ዳሰሳ በሌላ ክታብ እንመለሳለን አሁን ግን ኮሌጁ እየሰጠ ያለውን ሰፊ አገልግሎት ለመጠቆም ነው የዝዋይ ገዳም በ1959 ዓ/ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ የተመሠረተ ሲሆን በ1960 ዓ /ም ማስተማር ጀምሯል ።
በ1966 የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ ተዘግቶ ቆይቷል
በ1971 በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ አማካኝነት ዳግም ተከፍቷል ከዛን ጊዜ ጀምሮ በሺ የሚቆጠሩ መምህራንን ለቤተ ክርስቲያን አስረክቧል ገዳሙ ትንሿ ኢትዮጵያ ናት የገዳሙን ውሃ ጠጥቶ ስልጠናውን ወስዶ በሳል ሰባኪ ያልሆነ የለም
በመላው ዓለም ያለችውን ቤተ ክርስቲያን በማገልገል ያሉ
ሊቃነ ጳጳሳት ፡ ቆሞሳት ፡ሰባክያነ ወንጌል ፡ ካህናት ዲያቆናት ምስክር ናቸው በዝዋይ ገዳም ዘር ቀለም የለም በዝዋይ ገዳም የሚያድጉ ወላጅ አጥ ሕፃናት ከሁሉም ቤተ እምነት መጥተው ነው የሚያድጉት ቀደምት የነበሩ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በአካለ ሥጋ የሌሉ በነፍሳቸው ምሥክር ናቸው በአካል ያሉ በበረከት ሕዝቡን እየጠበቁ ያሉ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ከአሥር በላይ ናቸው፡-
ብፁዕ አቡነ ሉቃስ
ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ
ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ
ብፁዕ አቡነ ድዮስቆሮስ
ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ
ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል
ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዘአሜሪካ
ብፁዕ አቡነ መርሐ ክርስቶስ
ብፁዕ አቡነ በርናባስ
እኔ የማስታውሳቸው ብፁዓን አባቶቼ በአካለ ሥጋ ያሉት እነዚህ አበው ጥቂቶቹ ናቸው ሌሎቹንም ጨምሩ መምህራን:-
መጋቤ ሐዲስ እሸቱ ዓለማየሁ
ቀሲስ እሸቱ ታደሰ
ቀሲስ አሸናፊ ዱጋ
ቀሲስ ታደሰ ዱጋ
ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው
መልአከ ጽዮን ቀሲስ በላቸው
ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኰንን
መምህር ጳውሎስ መልክዓ ሥላሴ
ዶ/ር ታሪኩ
ዶ/ር አባ ጴጥሮስ ዘምስካዬ ኅዙናን
የትኛውን ጠርቼ የትኛውን ልተው ............
ብቻ ቤተ ክርስቲያንን በልዩ ልዩ መንገድ እየጠበቁ ያሉ በአሜሪካ በአውሮፓ በአረብ በአፍሪካ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም የዝዋይ ፍሬዎች የሌሉበት የለም፡፡ ይህ ማለት ገዳሙ ሀገር አቀፍም ዓለም አቀፍም ነው ማለት ነው ለዚህ በልዩ ልዩ ቋንቋ የሚያስተምሩ የገዳሙ ልጆች ምስክር ናቸው
በኮሌጁ ላይ ሰሞኑ ስለ ቀረበበት የሌለ ክስ ኮሌጁ ለማን ነው የተመሠረተው ? በቋሚነት የቤተ ክርስቲያንን ችግር ፈቺ ትውልድ ማፍራት ነው ዓላማው በተለይ የቤተ ክርስቲያን ሰው ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚቀድስ ቅኔ ማኅሌት ገብቶ ከመምህራኑ ጋር የሚያገለግል አውደ ምህረት ወጥቶ የሚሰብክ የሚያጽናና ቢሮ ገብቶ የሚያስተዳድር የሚመራ እንዲሆን ማድረግ ነው የዝዋይ መንፈሳዊ ተቋም ዓለማ ለዚህ ደግሞ የዝዋይ ገዳም ምቹ ዕድልን የፈጠረ ነው በገዳሙ የሚያድጉ ሕፃናት ፡ -
1ኛ ቁጥር ንባብ ዳዊት እንዲማሩ ይደረጋል
2ኛ በመቀጠል ዜማ እንዲማሩ ይደረጋል
3ኛ ቅዳሴ እንዲማሩ ይደረጋል
4ኛ ቅኔ እንዲማሩ ይደረጋል
5ኛ አቋቋም እንዲማሩ ይደረጋል
6ኛ ኮርስ እንዲሰለጥኑ ይደረጋል
7ኛ ዘመናዊ ትምህርት እንዲማሩ ሳይክል ተገዝቶላቸው ይማራሉ
8ኛ ወደ ልዩ ልዩ ተቅዋማት ገብተው ይማራሉ
9ኛ ወደ አገልግሎት ይሰማራሉ
ይህ ገዳም እነዚህን ትምህርቶች ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሰጥ ቆይቷል አሁንም እየሰጠ ይገኛል ይሄ መሬት ላይ ያለ ሐቅ ነው
ማሰልጠኛው ወደ ኮሌጅ ካደገ በኋላ ስንት ተማሪዎችን ተቀበለ ?
ከማሰልጠኛ ወደ ኮሌጅ ያደገው በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከፍተኛ ደካምና ጥረት ሲሆን፡-
በ2010 ዓ/ም በጥቅምት ሲኖዶስ ነው
በ2011 ዓ/ም ያልተሟሉ ነገሮችን እያሟላ ቆይቶ
በ2012 የኮሌጁ አመራሮችን ከመደበ በኋላ ቅበላ ጀምሯል
እውነታውን እንመልከት
-----------------------------
በ2012 የተቀበላቸው 26 ናቸው
15ቱ ከኦሮሚያ ክልል ሌሎቹ ከልዩ ልዩ አህጉረ ስብከት
በ2013 የተቀበላቸው 21 ናቸው
10 ተማሪዎች ከኦሮሚያ ቀሪዎቹ ከሌሎች አህጉረ ስብከት
በ2014 የተቀበላቸው 22 ናቸው
10 ተማሪዎች ከኦሮሚያ ክልል ቀሪዎቹ ከሌላ
በ2015 የተቀበላቸው 22 ናቸው
12 ተማሪዎች ከኦሮሚያ ክልል ቀሪዎቹ ከሌላ
የኦሮሚያ ክልል ተወላጆች በቋንቋው ማስተማር የሚችሉ ማለት ነው የሐዲስ ኪዳን ተማሪዎችንና ከፍሬ ምናጦስ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወስኖ የገቡትን ሳይጨምር ያለውን የመደበኛ ተማሪዎች ዳታ ነው ያቀረብኩት ይህ ማለት በኮሌጁ የሚማሩ አብዛኛው ተማሪዎች ከኦሮሚያ ክልል አህጉረ ስብከቶች ተቀብሎ እያስተማረ እንደሚገኝ ማረጋገጫ ነው፡፡ ይህንን እውነታ የትም ልንፍቀው አንችልም የኮሌጁ ሬጅስትራር ክፍል መጥቶ መረጃውን መመልከት ይቻላል
በመስፈርቱ የተቀመጠው ፡- ቢቻል ቢገኝ ይመረጣል ተብሎ እንጂ
ከየትኛው የኦሮሚያ ሀገረ ስብከት ዲቁና እና 10 ኛ ክፍል ከ2:00 ነጥብ የያዘ ተማሪ ተልኮ ተመለሶ አያውቅም ይህ ደረቅ ውንጀላ ነው፡፡
የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስን የምሥራቅ ሸዋ ምድርና የገዳሙ ልጆች ይመስክሩ እኔን ባታምኑ ለሥራዬ እመኑ ብሏል ጌታ ሠርቶ ማሰየት እየተቻለ በተሠራው ላይ ጥላሸት መቀባት ግን ቤተ ክርስቲያናዊ ምግባር አይደለም አንድ ሰው ትልቅ ነው አስተዋይ ነው የሚባለው ለሚናገረው ሁሉ በመረጃና በማስረጃ ስያደርግ ነው ካልሆነ ግን ለጊዜው እንጂ ነገሩ ውሃ አይቋጥርም ዝዋይ ገዳም ለማን ተመሠረተ ለቤተ ክርስቲያን ልጆች ኮሌጁስ ለማን ተመሠረተ የቤተክርስቲያንን ችግር መፍታት ለሚችሉ፡፡
ቅዱስ ሲኖዶስ ይህንን ውሳኔ የወሰነው በኦሮሚያና በደቡብ ክልል ያለውን የምዕመናን ፍልሰት ለመታደግ የወሰነው ወርቃማ ውሳኔ ነው ሌላው ኮሌጁ በዝዋይ ገዳም እንዲሆን የተፈለገው ገዳሙ ካፈራው ፍሬ ተነስቶ ነው ሌሎቹ አባቶች በሀገረ ስብከታቸው የሚገባ ሥራ ሠርተው በምሁራን አስጠንተው ማሠልጠኛንም ኮሌጅንም መክፈት ይቻላል በዚህ መንገድ ስንጓዝ ነው ማትረፍ የምንችለው
በዝዋይ ገዳም ግን አሁንም ገና ተሠርቶ ያላለቀ ሥራ አለብን ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ባለ ራዕይ ናቸው ሌላ የትምህርት ማዕከል ለመመስረት እንቅስቃሴ ላይ ናቸው መሠረት ድንጋይ ጥለዋል በዝዋይ ከተማ G+3 መንታ ፎቅ ለመስራት ካቀዱ ቆዩ ይህ ተቅዋም በዝዋይ ከተማ ባለው ሰፊ የገዳሙ ይዞታ ላይ የሚሰራ ሲሆን በሲሚንቶ እጥረት ምክንያት ነው የዘገየው በቅርብ ይጀመራል፡፡
ቀዳማዊ አባታችን እንዳሉ
ሥራህን ሥራ
በመጋቤ ብሉይ ቆሞስ አባ አትናቴዎስ
የገዳሙ ርዕሰ መምህርና የኮሌጁ የቦርድ አባል
ምንጭ:- ሐመረ ተዋሕዶ ሚዲያ
ሼር በማድረግ እንተባበር !
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ