ሽሽትና መሸትሸት። በመከሰም ላይ ስላለው ዛሬ።
እንኳን ደህና መጡልኝ ሽሽት ና መሸትሸት። „አቤቱ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰው ተራራህ ማን ይኖራል?“ መዝሙር ፲፬ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 08.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ? አራት ዓመት ሙሉ ሞትን በዕለታዊነት ስትመገብ የባጀችው አላዛሯ ኢትዮጵያ በኬክ እና በድግስ፤ በፈረሰኛ ጉግስ እና በዲስኩር ዳንኪራ ስትሽሞነሞን ሰነበተች። እንግዲህ ይህን ስል 23 ዐመቱን የት ጥለሽው አትበሉኝ … ያ ይቀመጥ ከቅርቡ ብንነሳ እንኳን ለማለት ነው … አያድርግብኝ እንጂ እኔ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ብሆን ኖሮ የለውጥ ዓመት የማክበርበት ጊዜ አሁን ባልነበረ፤ ከሽሽት ላይ ተሁኖ፤ መሸትሽት ካለው ድንግዝ ተሁኖ አውደ ዓምት የለምና። በቂ እኮ ነበር ወደ ንግሥና ሲመጡ የሆነው ሥርዓት … https://www.youtube.com/watch?v=qbq8D_qBa1Y ባለፈው አንድ ዓመት በሀገሪቱ ውስጥ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ የተሰሩ ስራዎችና ያጋጠሙ ችግሮች ላይ ያተኮረ መድረክ OBN መጋቢት 13 ፣ 2011 https://www.youtube.com/watch?v=Wn3YcmL8FGk ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ አንደኛ ዓመት የመዘከሪያ ፕሮግራም ላይ የደረጉት ንግግር Fana Television Published on Apr 2, 2019 https://www.youtube.com/watch?v=lTSFGQMVWfk #etv ህፃን ያኔት በሚሊንየም አዳራሽ EBC Published o...