ልጥፎች

የሽብርቀን ለማኝ። ልብ ወለድ በ1980ዎቹ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የተጠፈ።

ምስል
እንኳን ደህና መጣችሁልኝ። „ፈሳሾች በዙሪያው ነበሩ፤ ማዕበልህ ሞገዱ ሁሉ በላዬ አለፉ።“ ትንቢተ ዮናስ ፬ ቁጥር ፪ የሽብርቀን             ለማኝ። ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 07.04.2019 ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ እንዴት ናችሁ ክብረቶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ጉዑዝ ነገር ያናገርኩበትን ስለ አራት እግሩ እንጨት እና ስለ የሽብር ቀን ለማኝ አገር ቤት እያለሁኝ የፃፍኩትን አፈላልጌ እለጥፋላሁኝ ብዬ ቃል ገብቼ ነበር። አንዱ ስለተገኜ እንሆ … ኮምኩሙ … መቅድም ። ህዳር 14 ቀን 1985 እ.ኢ.አ በሥነ - ጸሑፍ ኮርስ ላይ እያለሁ መምህሬ አቶ አበበ ኬሪ የሰጠኝ የቤት ሥራ ነበር። የቤት ሥራውን የጣፍኩበት ዕለት ደግሞ  ህዳር 14 ምሽት ከ1.30 እስከ.1.57 ነበር። script ስክሪፕቱን በ16 ዓመቴ ከእኔ ከተለዬ እንሆ ዘንድሮ ከእጄ ገባ /ከእጄ ከገባ ወደ አራት // አምስት ዓመት ሆነው/። …. ገና አፍላ ዕድሜ ብቻ ሳይሆን የሥነ - ጥበብ ፍቅረኛነቴም ወጣት በነበረበት ወቅት የተፃፈ ነው። ምን ያህል እንደ አደኩኝ እንደ በሰልኩኝ ወይንም ቁልቁል አሰኝቶኝም ከሆነ መዝኑት - ክብረቶቼ … ቅኖቹ። ቅንነት መልካም ነው ሁሉን እንደተፈጥሮው ስለሚያስተናግድ። ይጀመር። በእጅ የተጻፈ ስለነበር በዘመንኛው ይቸክቸክ - እሺ! መኖር ድጉ እሱም እኔኑ ሲውዝ ድረስ መጥቶ ሊያኝ ይህን ሁሉ ወጪ ማፈሰሱን አደንቅኩለት። ያ የናዋዘው አዬር እሱንም ወግሮት ጥቁርቁር ብሏል።     የእንኳን ደህና መጣህ አቀባበል ይደረግለት ብዬ ይሄው ዕለተ ሰንበት እንደ ነጮቹ በ31.08.2014 ወግ ደረሰው። - መሸቢያ - መስተንግዶ እንግዲህ -----  ጭማሪ - ምራ

መነቀስ>>>>>> እኛበእኛ።

ምስል
እንኳን ደህና መጡልኝ። „ተነሡ፤ መልዕከተኛ ወደ አህዛብ ተልኮ፣ --- ተነሡ፤ በላይዋ በሰልፍ እንነሣ ብሎአል።“ ትንቢተ አብድዩ ምዕራፍ ፩ ቁጥር ፩ መነቀስ >>>>>>    .  እኛበእኛ። ከሥርጉተ © ሥላሴ Sergute©Selassie  06.04.2019   ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ። እንዴት ናችሁ የኔዎቹ ? ደህና ናችሁ ወይ ? መነቀስ ዘመኑን የሚገልጠው ይመስለኛል።   ዛሬ የረባ ነገር ሳልሰራ ነው የዋልኩት። ዝም ብዬ ስለመነቀስ   እኛበእኛ ሳስበው፤ ሳስበው አልገፋ ሲለኝ ነው ወደ ብራናዬ መጣሁት። ዝም ብዬ ሳስበው ይህ ከጣና ኬኛ ጀምሮ ያለውን ሁነት ፊልም ልስራው ቢባል   ምን እና ምን ሊሆን እንደሚችል የ ጭብጡ ታሬና ቁንጮ ቁጭ አድርጌ አወያዬሁት።  እሱ ጥሩ አድማጭ እኔ ደግሞ ተናጋሪ ሆኜ፤   … የዛሬን አያድርገው እንጂ የወጣልኝ ተናጋሪ ነበርኩኝ … ጥሩ አድምጭም ... የሁሉም ወረርሽ እንዲህ ሊሆን ሁሉም ሊደርሰው ማለቴ ነው ዛሬ ላይ እኔ ሰለባው ነበርኩኝ የመነቀስ … አሳዛኙ ቀጣይነቱ ቢሆን ዛሬ የእኔ የኖርኩበትን ሰቀቀን የሚጋሩ የእውነት አርበኞች የግንባር ሥጋዎች በርከት ብለዋል መታዬታቸው ነው፤ ቀደም ባለው ጊዜ ነጠል ብለው ቢወጡም ሸፋኝ፤ ጋራጅ፤ አለን የሚሉት ጥግ ነበራቸው፤ ዛሬ ግን ያው የእኔ ቢጤ ነው የሆኑት ...ብዬ አስባለሁኝ … ዘመድ ተገኜ እንደማለት ...  ·        እምታን በነፍሰጡር እይታ … ያጠፋነውን ጊዜ፤ ያበከነውን መንፈስ፤ ሳይባክን የተተረፈረፈበት ሁኔታ፤ ሳይንቦጀቦጅ የተገኘውን የመንፈስ ጥሪት ሚዛናዊ አድርጎ በማ