የሽብርቀን ለማኝ። ልብ ወለድ በ1980ዎቹ እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር የተጠፈ።

እንኳን ደህና መጣችሁልኝ።
„ፈሳሾች በዙሪያው ነበሩ፤ ማዕበልህ
ሞገዱ ሁሉ በላዬ አለፉ።“
ትንቢተ ዮናስ ፬ ቁጥር ፪

የሽብርቀን  
          ለማኝ።

ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
07.04.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ


እንዴት ናችሁ ክብረቶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ትናንት ጉዑዝ ነገር ያናገርኩበትን ስለ አራት እግሩ እንጨት እና ስለ የሽብር ቀን ለማኝ አገር ቤት እያለሁኝ የፃፍኩትን አፈላልጌ እለጥፋላሁኝ ብዬ ቃል ገብቼ ነበር። አንዱ ስለተገኜ እንሆ … ኮምኩሙ …

መቅድም

ህዳር 14 ቀን 1985 እ.ኢ.አ በሥነ - ጸሑፍ ኮርስ ላይ እያለሁ መምህሬ አቶ አበበ ኬሪ የሰጠኝ የቤት ሥራ ነበር። የቤት ሥራውን የጣፍኩበት ዕለት ደግሞ  ህዳር 14 ምሽት ከ1.30 እስከ.1.57 ነበር። script ስክሪፕቱን በ16 ዓመቴ ከእኔ ከተለዬ እንሆ ዘንድሮ ከእጄ ገባ /ከእጄ ከገባ ወደ አራት // አምስት ዓመት ሆነው/።

…. ገና አፍላ ዕድሜ ብቻ ሳይሆን የሥነ - ጥበብ ፍቅረኛነቴም ወጣት በነበረበት ወቅት የተፃፈ ነው። ምን ያህል እንደ አደኩኝ እንደ በሰልኩኝ ወይንም ቁልቁል አሰኝቶኝም ከሆነ መዝኑት - ክብረቶቼ … ቅኖቹ። ቅንነት መልካም ነው ሁሉን እንደተፈጥሮው ስለሚያስተናግድ።

ይጀመር። በእጅ የተጻፈ ስለነበር በዘመንኛው ይቸክቸክ - እሺ! መኖር ድጉ እሱም እኔኑ ሲውዝ ድረስ መጥቶ ሊያኝ ይህን ሁሉ ወጪ ማፈሰሱን አደንቅኩለት። ያ የናዋዘው አዬር እሱንም ወግሮት ጥቁርቁር ብሏል። 
  
የእንኳን ደህና መጣህ አቀባበል ይደረግለት ብዬ ይሄው ዕለተ ሰንበት እንደ ነጮቹ በ31.08.2014 ወግ ደረሰው። - መሸቢያ - መስተንግዶ እንግዲህ -----

 ጭማሪ - ምራቂ ቆራጣ ነገር አይረገበትም። እንደ ወረደ ቃላቶቹ ተኮልኩለዋል። ስለምን? እናንተን ሊሞጨሙጩ ጓጉ … መሰላችሁ? ቅን ስለሆናችሁ፤ ታድላችሁ!
እንሆ …

·       የሽብር ቀን ለማኝ

ወይ ጉድ! „አይጣልን …“ አሉ። ዛሬ እኮ ነው እያዩ ከማያዩት ተነጥሎ ልበ ብርሃን ሆነ ስለመፈጠሩ የተገነዘበው ማለት ይቻላል። አቅጣጫ የለሹ የጥይት ሩምታ ለአፍታ አካባቢውን ፀጥ እረጭ አደረገው። ሁሉም ነፍሴን አውጪን ጥግ - ጥጉን ያዘ። ተግ እስኪልለት … እኔም ወንድሜም …

በዚያች ሰዓት ነፍስ በምድር ላይ ከእንቅስቃሴ የታቀበ ይመስላል።

ታዲያ ቀን የነፈገችው፣ ለአፍ መሻሪያ የምትሆን ፍርፋሪ እንኳን በአኮፋዳው ያልነበረችው ምስኪኑ የእኔ ቢጤ አውላላ ሜዳ ላይ ዬሚይዘውን የሚጨብጠውን አጥቶ እንደ ስልክ እንጨት ተገትሮ ቀረ። ልቡን አንኳኳ ብርሃን እንዲልክለት …

ግን … የለመደው ጎዳና እንደ እንግዳ ዶሮ አደናገረው። እንደ ተሰክቶላቸው ግን በሚሰናከሉት እግረኞች በተሻለ ኮብ … ኮብ … ይልበት የነበረው አቅጣጫ ውሉ ጠፋበት። መያዣ መገረዣ የጠፋበት ጉዞውን ትቶ ባለህበት ቁም የተባለ መስሎ ቀጥ እንዳለ ቀረ … ማድመጥ የሚወደው ብርሃናማ ልቡ ነው። ተግ ማለት ተፈጥሮውን ይገልጠዋል …

አዬሩን በርቀት ለሚያዩትማ - ተወው። ሁሉም ሰው መሆኑ እራሱ ያጠራጥራል። 

ከትንሽ ቆይታ በኋላ ያ ልበብርሃን ቁጭ እንደ ማለት ብሎ እንደ ገና ወደ መንበርከክ ቃጣው።

አሱም አልሆነለትም መሰል ለጠጠሩና ለአቧራው እሩኹን አደራ ሰጥቶ ጋደም አለ። ብቻውን ነው ያን አውላላ አስፓልት የሚዘናከትበት …

ጋደም ያለው ወለል ካለው አሳፕልት ላይ ነበር.. መዲናዋ ላይ … አናቱ … ተ አናቱ … ተ አናቱ … እኮ ነው … ረጭ ረጭ ጭጭ ጭጭ … ህም።

ይገርምሃል ይህን ጊዜ ነበር ደም አስክሮት የወደቀ መስሎኝ አንዲያ ፀጥታ ጓደኛው ያደረገውን ቦታ ጥሼና ኃይሌን አሰባስቤ ሄጄ ያነሳሁት።

እሱም ከውጪ ግቢ - ነብስ ተላቆና ኃይሉን አማክሎ በደመነፍስ ተነስቶ ከነዝክንትሉ ተጠመጠመብኝ። ፍጥርቅ አድርጎ ስለያዘኝም ለማላላት ባደረጉት ትግል ተያይዘን አብረን ወደቅን።

ቃናው በጠፋበት ድሪቶ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ ድረስ አፈነኝ። ሃቅ ከውዲህ ወዲያ ሰትራወጥም ካጠረው ትንፋችን ፈቅ ብለን አዬን አበረን ሁለታችንም ዓይናችን ከስለት ልጇ ሃቅ ጋር ከርተት አለ … እንዳለ።

ያን ጊዜ ነበር ነገረ ሥራዬን ከመሠረቱ ተቃውሞት የነበረው ወንድሜ ኡኡታውን እያቀለጠ ፈጥኖ ደራሽና ነፍስ አድን የሆነው። ከዛ በኋላማ ምኑን እነግርሃለሁ፤ ያቺ አውድ  ዬእረፍት ያለህ እስክትል ድረስ ድልቂያው … ጩኽቱ …. ትርምሱ … ውቂ ደብልቂው ጡርንባው …. ከአዲሱ የደም ትወና ጋር ተጋርተው ሁለንትናውን እንደ ገና አደሩት …. የደመም ኡኡታ አስጎተተ … አነጎተ።

ባትተን ግን የትገባች አለን አብረን በአንድ ልሳን እትጌ ሃቅ … ግን የእውነት የት ገደመች?ክንፍ አግኝቷት ይሆን? ወይንስ ጦሮ? ስታሳዝን … በጠራራ ጠሐይ … ትንትን አላት … እኔን … አፈር በበላኝ …

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

ቅኔቹ የኔዎቹ ኑረልኝ


መሸቢያ ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።