#እርህርህናዬን #አልወቅሰውም።
#እርህርህናዬን #አልወቅሰውም ። "የቤትህ ቅናት በላኝ።" አገር እያለሁኝ ከቤተሰብ ጉዳት ከደረሰ ለተጎዳ ሳይሆን እሷ ምን ትሆናለች ነው ጭንቁ። እግዚአብሄርን ባገኜው የምጠይቀው ውስጤ በምን #እንደተሠራ እንዲነግረኝ ነው። ስልክ እማልወደውም፦ እማላነሳውም በፍራቻ ምክንያት ነው። የቤቴ ደወልም በጣም ነው የሚቀፈኝ። ውጭ አገር ለሚኖሩ ቤተሰቦቼ የሚልኩልኝን ዕቃ በአደራ ደብዳቤ እንዳይልኩ ሁሉ ነው እምነግራቸው። የቤቴ ደወል በፖስተኛ እንዳይጨናነቅ። የሆነ ሆኖ ፈንጠዝያ አያጓጓኝም። ፈንጠዝያም ውስጥ ኑሬ አላውቅም። የምመርጠው ከተቻለ ጸጥታ። … … ካልሆኑም ጉዳት በደረሰበት አካባቢ መገኜት እና የድርሻዬን መሞከር ነው። በምሞክረው ውስጥ ብቻ #ሐሤት አገኛለሁኝ። ሐሴት ከደስታ በላይ ነው በእኔ ፍልስፍና። ለነገሩ የአደኩበት ቤተሰብ በልደት #ነዳያን #ድንኳን ጥሎ #አደግድጎ ታጥቆ #ከሚያደግፍ ከሊቀ ሊቃውንታት ደጋግ ቤተሰብ ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን የተፈጠርኩበት ዕለት እና ሳይንቲስቶች የሚሉት የደም ዓይነቴም ሊሆን ይችላል በተጎዳ አካባቢ ብቻ ህሊናዬ እንዲያተኩር የሚሆነው። ለዚህም አምላኬን አመሰግነዋለሁኝ፦ ይህን ስለሰጠኝ። እጅግ ብጎዳበትም። ከተሰደድኩኝ አንድም የቤተሰብ መርዶ በቅጡ ነግሮኝ የሚያውቅ ደፋር የለም። ህልሜን አምናለሁኝ። በህልሜ ራሴን አርድቼ የሃዘን ጊዜዬን በመጨመት ይከወናል። ከሠርግ ቤት - ሃዘን ቤት፤ ከወል የፌስታ - መሰናዶ የታመመ መጠዬቅ ይቀናኛል። ይህን ፈጣሪዬ መርቆ ስለሰጠኝ አመሰግናለሁኝ። ብጎዳበትም ግን የውስጤ እርካታ ምንጩ ይህ በመሆኑ #ርህርህናዬን #መቼውንም #ቢሆን #አልወቅሰውም ። አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ተጠለፋ ሲባል ከ2 ወር በላይ ጥቁር ለብሻ...