አልገባኝ ያለው ነገር
አልገባኝ ያለው ነገር ለምንድን ነው #በብርቱካማው ክስተት የሰይጣን ጆሮ ይደፈን እና ኢትዮጵያ #በጠላት የተወረረች ይመስል ይህን ያህል የአብይዝም ሥርዓት የታወከው?! ትክክለኛው ዳኝነት ያለው በህዝብ ህሊና ነው።
ለምን ግራ ቀኙን አጥንቶ ህዝብ ዳኝነቱን እንዲሰጥ አይተውትም። ትምህርት ሚኒስተር እራሱ #መግለጫ እንዲሰጥ ተደረገ። ፈጽሞ ሊገባኝ አልቻለም። የአማራ ህዝብን በሚመለከት ከደቃቁ እስከ ገዘፈው ጉዳይ ድረስ ያለው ነገር እራሱን የቻለ #የምርምር #ተቋም ያስፈልገዋል።
ሰሞኑን እኮ 100 ተጓዦች በሁለት ዙር ከ፬ ኪሎ አፍንጫ ሥር ታግተዋል። ህዝብ በአውሮፕላን ካልሆነ በዬብስ መጓጓዝ አቁምም ነው መልዕክቱ። ሹፌሮችም #የጎዳና ላይ ኑሮ ይቅናችሁ ነው። የሰው ልጅ ተገድሎ ተዘቅዝቆ ሻሸመኔ ላይ ተሰቅሏል - ተገድሎ ተቃጥሏል - ታስሮ ተገድሏል። ያልታዬ ማዕት አለን በምድሪቱ? ምነው ኢትዮጵያ አንደበት በነበራት????
ሥርጉትሻ 2025/03/29
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ