ዳኛህ
በሰው ልጅ የመኖር ፈተና ውስጥ ግዙፋ ፈተና ባልተረጋጋ መንግሥት ሥር የታፈነ ህዝብ ዕጣ ፈንታ ግራጫማ መሆኑ ነው። ያስፈራል። ይቀዘቅዛልም።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/03/2021
በሰው ልጅ ፈተና ውስጥ እራስን መከዳት የመሰለ የሞት መንገድ የለም። እራሳቸውን ያመኑ ጭምቶችም፣ የስኬት ጎዳናም ናቸው። ትውልድ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/03/2021
በነደደ መከራ ውስጥም ቢሆን ፈጣሪህ እንዳለ እሰብ። መድህንህ ነውና። ማብረዱ ይቻለዋልና።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/01/2021
ስኬትህ ቅንነትህ ይሆን ዘንድ ፍቀድለት። ህሊናዊነት የሚገኘው በቅንነትህ ልክ ነውና።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/03/2021
ዳኛህ ተግባርህ ነው።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/03/2021
ዕውነት ክንንብህን ገልጣ እርቃንህን ታሥቀርኃለች። በሦስት ዓመቱ ጉዞ "ኢሱ" እና አብይዝም አልተዋወቁም። ከእንግዲህ ግን በደርበቡ ነው። ትንታ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
29/03/2021
#ክፋነት #በምድራችን #የሚተንበት #የተፈጥሯዊነት# #የነፃነት #ዘመን #ይናፍቀኛል #በጣሙን!
ሥርጉትሻ2024/03/29
ክፋወች ክፋት አያልቅባቸውም። ማምረቻቸው ግዙፍ ፦ጎታቸውም ሰፊ ነው ለክፋት ክዘና። ጥሪታቸው ክፋት እና ክፋነት ስለሆነ።
ደጎች ደግሞ የክፋት ጎተራ ስሌላቸው በክፋት እረገድ መናጢ ደሃ ምስኪኔታ ናቸው። ታድለው።
ውቦቼ በሉ ቸር ሁኑልኝ፦ ቅንነት ስንቃችሁ #ቀናነት ጥሪታችሁ ይሁንልኝ። አሜንወአሜን።
ሥርጉትሻ 2024/03/29
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ