ልጥፎች

ከዲሴምበር 19, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ነፍስ ይማር። አሜን!

ምስል
ነፍስ ይማር። አሜን! „ከምድር ስተገኘህ ወደ መጣህበት መሬት እስከትመለስ ድረስ  … እንጀራህን በፊትህ ትበላለህ፤ አፈር ነህና ወደ ዐፈር ትመለሳለህ“ ዘፍጥረት ፫ ቁጥር ፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie 19.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።                                                                     ዛሬ ኢትዮጵያ ብሄራዊ የሃዘን ቀን ነው። ይህ ብሄራዊ የሀዘን ቀን የታወጀበት ምክንያት ደግሞ የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ በስጋ ከእናት ምድራቸው በመለየታቸው ምክንያት ነው። ሟቹ ፕሬዚዳንት ግርማ ወ/ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህድ ቤተክርስትያን ወደ አንድ መምጣቷ ከስደሰታቸው የኢትዮጵውያ የፖለቲካ ሊሂቃን አንዱ ናቸው። እርቁን በንጹህ ህሊናቸው፤ በንዑድ መንፈስ ተቀብለውታል። ብጹዕን ቅዱስ ሊቀና ጳጳሳትን ጨምሮ 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፓትርያርክን ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀሪዮስንም ከቦታው ድርስ ተገኝተው ጠይቀዋል። እንኳን ደህና መጣችሁም በለዋል። የብፁዕ ወቅዱስ አባታችን የአቡነ መርቀሪዮስ ባዕለ ስመትም በብሄራዊ ደረጃ መከበር እንዳለበት ቃለ ምህዳን ሰጥተዋል። በባዕሉ ላይም በአካል ተገኝተዋል።     ብጹዐኑ ሊቀ ቤተክርስትያናት ከስደት ወደ አገራቸው መመለሳቸውን በሚመለከት ከቀደሙት የኢትዮጵያ ፖለቲካ መሪዎች በፍጹም በተለዬ ሁኔታ ብሥራተ ዜናውን በዬምሥራች መቀበላቸው ይህን እንዲያሳቸው እግዚአብሄር ዕድሉን መሰጠቱ ቅንነታቸውን ያሳያል። በሌላ በኩል በኢትዮ ኤርትራ ጉዳይም ሰላም ሰፍኖ ለማዬት ጉጉትም፤ የተለዬ ናፍቆት እንደ ነበራቸው የተለያዩ ዜናዎችን ስከታትል ኖሬያ