በሴቶች እና በአብይ ዙሪያ ሥርጉተ በታህሳስ 26/2017 ምን ብላ ነበር?
አብይ ኬኛ! ክፍል ሦስት - ለቅኖች ብቻ። አብይ ለእኛም ለሴቶች አናባቢያችን Vowels ነው። „ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ማልዶ በተነሳ ጊዜ፤ አስቀድሞ ሰባት አጋንንት ላወጣላት ለመግድላዊት ማርያም ታዬ። እርስዋ ሄዳ ከእርሱ ጋር ሆነው ለነበሩት፤ ሲያዝኑና ሲያለቅሱ ሳሉ አወራችላቸው። እነርሱም ህያው እንደሆነ ለእርስዋም አንደታዬ ሲሰሙ አላመኑም። ከዚህ በኋዋላ ከእነርሱ ለሁለት ወደ ባላገር ሴሄዱ፤ በመንገድ በሌላ መላዐክ ተገለጠ። እንርሱም ሄደው ለሌሎች ሄደው አወሩ፤ እነዚያን ደግሞ አለመኗቸውም። ኋላም በማዕድ ሳሉ ለአስራአንዱ /ሐዋርያት/ ተገለጠ። ተነሥቶም ያዩትን ስላላመኗቸው፤ አለማመናቸውን የልባቸውን ጥንካሬ ነቀፈ። እንዲህም አላቸው፤ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፤ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። ያመነንም፤ የተጠመቀም፤ ይድናል። ያለመነ ግን ይፈረድበታል“ (የማርቆስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፮ ከቁጥር ፱ አስከ ፲፯። ዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፳ ከቁጥር ፩ ጀምሮ … ) የበለጠ ሚስጢሩን ለማዬት የዬሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፫ ከቁጥር ፩ ጀምሮ ያለውንም በጥልቀት መመልከት ይቻላል። በመንፈሳዊ ህያዊነት ቃለ ህይወቱ መረቡን በረቂቅነት በውስጣችን ይዘራል። ይሄም ነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሚስጢር። የክርስትናም። ዶር አብይ አህመድ አኮ የቅኔ ማዕዛ ናቸው። እሳ...