ዋው! ሴት ርዕሰ ብሄር!

የመጀመሪያዋ ሴት ርዕሰአምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ 4ኛው የኢትዮጵያ ርዕሰ ብሔር ሆኑ።

„አቤቱ ጸሎቴን አድምጥ ልመናዬንም ቸል አትበል።“
መዝመረ ዳዊት ፶፬ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
25.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ



ሰሞኑን ሲያወዛግብ በባጀው የፕሬዚዳንትነት ቦታ ላይ ክብርት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ-ኢትዮጵያ ሴት ርዕሰ ብሔር መሾማቸውን ቢቢሲ ዘገበ።

አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ-ኢትዮጵያ ሴት ርዕሰ ብሔር አገኘች

ይህ እንግዲህ ቦታው ብዙም የረባ ፓለቲካዊ ድርሻ ባይኖረውም ሴቶችን ወደ ፊት ለማምጣት መደፈሩ ግን ለእኔ መልካም እና ወርቅም እርምጃ ነው።

ነገ ደግሞ ኢትዮጵያ በፕሬዚዳንታዊ ይሁን በጠ/ሚስትራዊ ትመራ ብቻ ሴት ሙሉ የፖለቲካ አንኳር መሪ ልትሆን የምትችልበት መሰመር ጠራጊ ነው ብዬ አስባለሁኝ።

አንድ ጊዜ የኢትዮጵያን ችግር ለመፍታት ሴት ጠ/ሚር ስትሆን ነው ብዬ ጽፌ ሃሳቤ እንደተንጠለጠለ ወዲያው ነበር ጉልበተኞች ያስነሱብኝ። ከዛም በመነሳት ሴቶች ብልህ አመከንዮ አላቸው ጊዜ እስኪሰጣቸው ድረስ ጠብቅው ያቆዩት ዘንድ እምከራለሁም ብዬ ምላሹን ጽፌ ነበር።
በኢትዮጵያ ጥቅም ላይ ያለዋለው ድንግል ሃብት የሴቶች ብልሃት ነው። በ እኛ ውስጥ ተነገረው ያማይልቁ ጥበባዊ ብቃቶች አሉን። ይህን በድፍረት ነው እኔ እማናገረው። 

ስለሆነም ለክብርት ርዕሰ ብሄሯ ሳህለወርቅ ዘውዴ-ኢትዮጵያ ከውስጤ ከትንፋሼ ከነፍሴም እንኳን ደስ አለዎት እላለሁኝ። ለመላ የኢትዮጵያ ሴቶችም እንኳን ደስ አለን እላለሁኝ። ምንም ይሁን ምን ሴቶች ስማቸው ጎልቶ ሲጣራ ለእኔ ደስታዬ ነው።

እኔ ሴታዊት ታገይም ነኝ። በሙያዬም የሴቶችም አደራጅ ነኝ እና ለመንፈሴ እጅግ ቅርብ የሆነ ውሳኔ ነው ወድጀዋለሁኝ። ሐሴትም አድርጌያለሁኝ።

በሰላም በፍቅር በምህርት በይቅርታ በተግባራዊ ሥራ መቼም አብዛኞቹ ሴቶች እንደማንታማ ይታወቃል። ሴቶች የተግባር እምቤቶች ናቸው። ሴቶችም የነፍስ ጥበቦች ናቸው።

በሌላ በኩል በዚህ ሹመት ዙሪያ ያሉ የተከደኑ ሲሳዮች አሉ። መንፈሱን ለማገናኘት አውሮፓን ቀኘት ማድረግ ብዙ ይጠቅማል። ታሪክን መለስ አድርጎ ማመሳጠርም ይጠይቃል። የኢትዮጵያን ግርማ ሞገስም ማህባዊ ያደርገዋል። ስለምን? በቀጠሮ...

ሴቶች እግጅ ድንቅ ዲፕሎማሲያዊም ናቸው። እኔ እውነት ለመናገር ዘብርሃነ ኢትዮጵያ እቴጌ ጣይቱ ዳግሚያ እንደ ተነሱ ነው የተሰማኝ። በዴፕሎማሲያዊ ሥር እቴጌ ሰብለወንጌልም ብርቱ ነበሩ፤ ቅድስት አማክዳም እንዲሁ። ዋው! ደስ ብሎኛል።

የክብርቷን የህይወት ታሪክ ቢቢሲ ስላቀረበው ከዛ ማንበብ ይቻልል። አንዱ ማንነቴ ሴትነቴ ስለሆነ ለዛም ብርቱ የሆነ የጸና አቋም አለኝ። እናም የእውነት ደስ ብሎኛል።

ሴቶች ጥበቦች ናቸው!
ሴቶች የተግባር እመቤቶች ናቸው!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መልካም ቀን።




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።