ልጥፎች

ከሴፕቴምበር 5, 2018 ልጥፎች በማሳየት ላይ

ጥያቄው የብትን አፈር የነፍስ ጉዳይ ነው!

ምስል
ኢትዮጵያ የቁጥር ተማሪ አይደለችም። ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። እንደምን አላችሁልኝ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ። በነገረ ጣይቱ ላይ ዛሬ ጥዋት እጅግ ከማከብረው ከአንድ የፖለቲካ ድርጅት በላይ በግሉ ስለ ኢትዮጵያኒዝም የተጋ እና ያታገለ የአክቲቢስት አቶ መስፍን ፈይሳን ምልከታ አዳመጥኩኝ። ባለፈው ሳምንትም የርዕዮት ሚዲያን ምልከታ ተከታትያለሁኝ።  የወዳጄን የመስፍኔን ከቅንነት ስለሆነም በትርጉም ባቃናው፤ ትንሽ ዘለግ አድርጌ እንደ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሴት ምልከታየን በሚል ነው እንዲህ ማለት ፈልግሁኝ።  እሱ ቅን ኢትዮጵያዊ ስለሆነ በሃሳብ ልዩነቱ ልናዝንበት የሚገባ አይሆንም። ምንግዜም በአንደኛው ሃሳብ ባንግባባ በሌላው ደግሞ እንስማማለን ወይንም በድምጽ ተዕቅቦ እንለያለን። ይህ የእውነተኛ ዴሞክራሲ ፈላጊው እውነት ነው። ግራው ዘመም መንፈስ ያደረበት ብቻ ነው ሞጋች ሃሳቦችን ወይንም ፈንጋጣ ሃሳቦችን የሚፈራው። ያው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አምላኩ ስለሆነ።  ·        የሆድ የሆድን።   ኢትዮጵያ የክት እና የዘወትር ልጅ የላትም። ኢትዮጵያ ስለ ልጆቿ ክፍልፋይ አሰናድታ አታውቅም። ኢትዮጵያ የቁጥር ተማሪ አይደለችም ። ኢትዮጵያ ላይ ያለው ንጹህ አዬር ኦክስጅን አንተ / አንቺ የእኔ አይደለህም /ሽም ብሎ ገድቦ አይዋቅም፤ ለይቶም አያውቅም። አንድ ተራራ ላይ ያለው ነፋሻ አየር እኩል ነው ለሁሉ ፍቅሩን የሚያዳርሰው፤ ዝናቡም ሲመጣ እንዲሁም መቻቻልን በእግሩ አንዲሄድ ያደርገዋል፤ የኢትዮጵያ ጸሐይም ስትመጣ ለሁሉም ብርሃነኗን በሐሤት ትለግሳለች። ስታኮርፍም ስትስቅም እኩል ነው።  ኢትዮጵያዊ ወቅታት ሲመጡ ጸደይ በጋ በልግ ክረምት ሲመጡም እንዲሁ ሁሉ ለሁሉ ተደራሽ ይሆናሉ