ልጥፎች

መቼ ይሆን አሉታዊ ቁርቁሱ የሚያበቃው? ይንፍቀኛል ...

ምስል
„አማራነት መንፈስ ነው።“ „ብዙ ነገርን እንናገራለን፤ የነገሩ መጨረሻ እሱ ብቻ ነው፤ እንጂ ነገር ግን መጨረስ አንችልም።“ „መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፫ ቁጥር ፳፯“ ከሥርጉተ©ሥላሴ 04.09.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ ·        ግ ራሞተ ተሰሞናተ። የሰሞናቱ ትርምስ ግርም ይለኛል። አሁን ጠ/ሚር አብይ አህመድ እና ዶር ለማ መገርሳ መድረኩን እስቲ እንዳሻችሁ ሁኑበት ያሉ ይመስለኛል። ምክንያቱም የስሜን አሜሪካ የነበረው የመሰናዶ ውጣ ውረድ ብዙ እንዳሰተማራቸው አስባለሁኝ። በዝርዝር ሥም አቀማማጥ ሁሉ ቦክስ እንደነበር የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሪፖርት አስረድቶኛል። የሆነ ሆኖ በቤተመንግሥትም ደረጃ የአደባባይ ሥራ እንብዛም ኑሯቸው የማያውቀው ዶር ሙሉቱ ተሾም ሳይቀር ብዙ ጊዜ ብቅ እያሉ በቴሌቪዥን መስኮቶች እያዬናቸው ነው - አሁን አሁን። እንኳን ለዚህ አበቃቸው ያሰኛል። መቼስ መነቃነቅን የመሰለ ነገር ስሌለ …. ተነቃነቅ ስንፍናን ነቅንቅ ሞራልን አድምቅ ኢትዮጵያን አልቅ>>  አማራ ተጋድሎ እና ቄሮ ነፃ አውጥቷቸዋል ፕ/ ዶር ሙላቱ ተሾመን። የቀድሞውን ጠ/ ሚር ኃይለማርያም ደሳለኝንም ታጋድሎው ገላግሏቸዋል። ግንቦት ሰባቶችንም „የት ናችሁ? የት ደረሳችሁ? ምን ያዛችሁ“ ከሚለው ፈተና ገላግሏቸዋል። ተመሰገንም ሊሉት ይጋባል። ማጣፊያው ያጠረ መከራ ነበረ እና በዬጊዜው የመልስ ቀዳዳ ማጮለቅ…  በሌላ በኩል የአንዱ ሥም ላይ ለልዕለና የሌላው ደግሞ ታች ወድቆ ሲፈጠፈጥ፤ የሌላው ደግሞ „የእኔ የእኔ“ እዬተባለ ሽሚያ ላይ - ለወረት ከፍ እና ዝቅም ሲባልለት ይታያል። ሌላው ደግሞ ግራው እና ቀኙ ማህል ላይ ሰቅዘውት እንደ ገመድ ጉተታ  ሲጓተቱት መንፈሱን ሲቦጫጨቁት እምለከታ

ቃ! ካላለስ?! // ሥነ - ግጥም

ምስል
ቃ ። „አሁንም ልጆቼ ሆይ ስሙኝ ከአፌ ቃል አትራቁ።“ መጽሐፈ ምሳሌ ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፯ ከሥርጉተ© ሥላሴ 03.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። በዝምታ ኳኳታ፤ በኳኳታ ዝምታ // ህምታ - ተተፍታታ? በሁካታ ጸጥታ፤ በጸጥታ ሁካታ //  እምታ - ተተፍታታ? ልቤ በዝንቅንቅ  በቅልቅል ሲምታታ - ድር ግ ምታ ቃ! እንዳይል በሎሆሳስታ...  ሆታ¡ ሲሆን እልልታ በቃና ዜማ ትክታ … በትክታ …  መቼ ባጅቼ ከንፌስ ለጫጫታ? ዞገቢስ ነኝ የለብኝም ውለታ! የሙሉ እድሜ ብክነት በከንቱነት አንደገብያ ለእፍታ ሲፈታ ተዬት ተገብይቶ ስክነታዊ ገበታ? ከዬትስ መጥቶ ጌታ ማስተዋል እርጋታ? ብቻ ቻቻ ቸበር ምታ፤ በቃ እስክስታ በስክስታ አንጓ - ተአንጓ የምንቶ ፍሪንባ አቤቱታ …፤ የሥም ወሽመጥ ፍስክታ፤ የህማማት ቋጠሮ ዕድምታ በቃ! ይኸው ሆነ የሞፈር ቀንበር መፍቻ?! ሰሚ ሳያገኝ ቤተ - ዋይታ?  በፌስታ ግብይት እንዲህ አንደ ‘ል ባሌ ይፈታ? ብቻ … ብቻ ያ መራር እንትን እንዲህ እንደዋዛ ተረታ?! ለካንስ ለዚህ ነው የድቅድቅ ግዞት ስንጥር ፈግግታ? እንዲህ ሲ ማ ታ፤ ሲያምታታ የህቅታ ቬ ሎ ወ በ ቅታ የቃል ፍልስ - ምልስ ቅልስ - ጠጠርማ -  ቃታ ህቅታ፤ የላቦት ዲሞ ግማዱ በቻ ቻ ቴ ሲፈታ … ግብዕት ሆነ ተይህ፤ ግብዕት ሆነ ተያ የእንቆቅልሹ ግርምታ፤ የዋንጫው ሩምታ! ሆ¡ በል አገር --- በትምክህትህ ቃ! በል ሲ ፈ ታ ኪዳን ሲ ያ ፋታ ወይንስ  ሊያፍታታ? ገብያ ተውሎ፤ ውሎ ሲፈርስ እንደዋዛ፤ እፍ ብር ሲልም ለአፍታ የጠብታ ቸርቸር ሳይሰናበት፤ የጅረት ምት አያ እንቶኔ ያ ከርታታ፤ የምትኃት ድርሳነ - ዘንግ ፈር ከ ክ ውሽክታ፤

አበጀ /// ሥነ ግጥም

ምስል
አበጀ። „ጥበብ ቤቷን ሠራች ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች።“ ምሳሌ ምዕራፍ ፱ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ ሥላሴ 02.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዝዬ። ተዬት መጣህ ብዬ ትዝታን ብጠይቅ? ወደዬት ነህ ብዬ ናፍቆትን ብጠይቅ? መልሶ ላከልኝ የዘመን ዝንቅንቅ። ቆልቁለት አውርጄ አሳፈሬዋለሁ ዳገቱን አግዤ መጪ … በል ብዬዋለሁ ማተብ ከተገኜ ሰጋር እልካለሁ። ዳጥ ለዳጥ ስማስን ቅንነት ሰብዤ ግራምጣ ተገኜ ተዚህ ከተከዜ። መተከዝ ሲሳነኝ ለጥርስ ተሟገትኩኝ ሳቅ መግዛትም ቻልኩኝ በቦንዳ ተኳልኩኝ። እቴ ሆይ! እናቴ አስቲ ልጠይቅሽ? ልጅሽ በ ክ ት ነው በዝርዝር መዛቅሽ። አንች ሆይ! የኔይቱ እምት እመቤት፤ ልባም ደማሚቱ የቱ ላይ ተሟላ ያነ አብነቱ? ሲሶ እርቦ ሲሉ ሟርተኞች፤ ሲያሟርቱ ዜግነት ክፋዩ የሂሳብ ስሌቱ፤ በዝቶ ቀረመቱ ተዛነፍ እንዳይሆን ገደለኝ ስጋቱ። ነገን አስባለሁ ሞጥሬ አጥንቼ፤ ተስፋ ስለሆነ እሱንም ሞግቼ፤ ነገን እንዲሰጠኝ ባክኖት‘ ረትቼ። ትውልደ - ድርሻዬ የእኔ መሆን በጀ፤ መታከት ለሁሉ እንዲህ እያባጀ፤ እያባጃ … የተዛነፍ ሚዛን  አይባል አበጀ፤ ትርፉ መልካምነት ሰውነን ያበጀ። ተጣፈ አሁን 20.46 ስለምን ተጣፈ /// ልብ ለልብ አሰኝቶኝ። ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር። ውዶቼ ክብረቶቼ ኑሩልኝ። ማለፊያ ጊዜ።  

እሱን ስፈትነው // ሥነ ግጥም

ምስል
እሱን ስፈትነው … „ማስተዋልስ ድምፆዋን አትሰጥምን?“ ምሳሌ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፪ ከሥርጉተ ሥላሴ 02.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲወዚዬ። ስንደቅ ሰንድቆ ሳቁን ቢልክልኝ ምንአለ አላቢው እውነት ቢሆንልኝ? ግራር እና ወይራ በአንድ ያለቃቅሳሉ ዘመን እንዲያቸው ወቄት ያሰማሉ። ዳመጦ ተዳምጦ እንዝርትስ የትስ ሲገኝ? አለሎ በአላላ፤ አለባሶ ግርሞት እንዲህ ሲሆን ጠማኝ ተጠማኝ በጠማኝ ውሎማደር ሆነ ባይታዋር ተለማኝ። እሱ ለፈጠረው ለአንድዬ እፍታ እሱ ለፈጣራት ለእንደዬ እፍታ ለድንኳን ጥላ ያዥ ለሆነው ለአንድአፍታ ቀን ይገኝ ከሆነ ስገደት ማታማታ። ሱባኤ ላይ ሆኜ ተስፋን ሳማትረው ሜትር ገዝቶ ላከ እሱን ልፈትነው። ·        ተ ጣፈ አሁን 20.22 ·        ስለ ምን ተጣፈ? ስለግራሞት ብቻ …

ከሩቅ ይጠራኛል / ግጥም

ምስል
ከሩቅ ይጠራኛል። „በውኑ ጥብብ አትጮኽምን?“ ምሳሌ ምዕራፍ ፰ ቁጥር፩ ከሥርጉተ ሥላሴ 02.09.2018 ከገዳማዊቷ ሲወዚዬ። መም ረ ር ይመረኛል፤ ልዋ ጥ ህም ብለው እንብዬው ይለኛል። ጎምዝዞ ይዞኛል፤ ልፈትነው ስልም አይሆንም ይለኛል። ደማኖም ታ ጥ ቆኛል፤ ልቀቀኝም ስለው ል ሽ ሽ - ልሰልቅ ሽ እንዲህም ይለኛል። ይለኛል ይለኛል፤ መንሹን አስልፎ ክንደኛ ብሎኛል። ተረከዝ ተጎርዶ ራመድ ክዶኛል፤ መክዳቱ ክዳቱ ክዳኑ ጥፎኛል። በትርፈኛ ዘይቤ ዜማ ቀንጥ ቦ ኛል፤ ፈር ተገብ ስለሆንኩ ዓይነት ቀን ድ ቦኛል። ይሆናል አይሆንም „አይም“ ያምርብኛል „እሺ“ ቢቀርበት እንቆቆ ልኮ ኛ ል። ለእሷ ከሆነማ፤ ንጋትና ዕውነት ከሩቅ ይጠረኛል ለሚዛንም ቀኑ ናፍቆቱ ይዞኛል፤ ሸው እንዲያው ሽው እሱን ያሰኘኛል የእኩልነት ማ ዶ ት ሁሌም ይር በ ኛል። ተጣፈ አሁን 19.58። ስለምን ተጣፈ? ስለግራሞት ብቻ …