እሱን ስፈትነው // ሥነ ግጥም

እሱን ስፈትነው …„ማስተዋልስ ድምፆዋን አትሰጥምን?“
ምሳሌ ምዕራፍ ፰ ቁጥር ፪
ከሥርጉተ ሥላሴ
02.09.2018
ከገዳማዊቷ ሲወዚዬ።



ስንደቅ ሰንድቆ ሳቁን ቢልክልኝ
ምንአለ አላቢው እውነት ቢሆንልኝ?

ግራር እና ወይራ በአንድ ያለቃቅሳሉ
ዘመን እንዲያቸው ወቄት ያሰማሉ።

ዳመጦ ተዳምጦ እንዝርትስ የትስ ሲገኝ?
አለሎ በአላላ፤ አለባሶ ግርሞት እንዲህ ሲሆን ጠማኝ
ተጠማኝ በጠማኝ ውሎማደር ሆነ ባይታዋር ተለማኝ።

እሱ ለፈጠረው ለአንድዬ እፍታ
እሱ ለፈጣራት ለእንደዬ እፍታ
ለድንኳን ጥላ ያዥ ለሆነው ለአንድአፍታ
ቀን ይገኝ ከሆነ ስገደት ማታማታ።

ሱባኤ ላይ ሆኜ ተስፋን ሳማትረው
ሜትር ገዝቶ ላከ እሱን ልፈትነው።

  • ·       ጣፈ አሁን 20.22
  • ·       ስለምን ተጣፈ? ስለግራሞት ብቻ …




አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።