የመቀሌ የፖለቲካ ትኩሳት ደግሞ ወደዬት?
በዕለ አሸንዳ በትግራይ። „ ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ በእኔ ላይ ግን አንድ ነገር እንኳ አይሠለጥንብኝም። “ የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ መልዕከት ወደ ቆረንቶስ ምዕራፍ ፲፮ ቁጥር ፲፪ ከሥርጉተ© ሥላሴ 25.08.2018 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። መቀሌ እንደለመደባት ሞቅ ደመቅ ብላለች። በሁለተኛው ስታዲዮዋ ላይ ደግሞ ሁለተኛውን ባዕሏን እያከበረች ነው። የትግራይ ባልሥልጣናት በሙሉ በተገኙበት በዚሐው ባዕል ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው በባህላዊ ቀሚሱ ተውበው ተገኝተዋል። በዚህ ባዕል ላይ ከትግራይ ደም ያላቸው ተዋናዮችን እና ታዋቂ ሰዎችም አንደተገኙ መረጃው ይጠቁማል። ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤልም አብያዊ ለመሆን በተሸለ አቀራረብ በሚመሯቸው ወገኖች ማህል ሰላምታ በመለዋወጥ እና በማከበር ቀረቤት እንዳላቸው አንድ ያልተለመደ ነገር ሲሳዩ ተመልክቻለሁኝ። ይህም መልካም የሆነው ያልተለመደው ነገር በወያኔ ሃርነት ትግራይ ሥር የወደቁ ነፍሶችን ከእሥር በባዶ 6 ያሉትን ግፉዕና በማስለቀለቅ እና የወረሩትን መሬት በክብር በመመለስ አብነቱን ወደ ስልጣኔ ቢያሻግሩት ምንኛ ይህ ድርጊታቸው ከልባችን በገባ በነበረ። በዚህ የአሽነድዬ ባዕል ባህላዊ ውዝዋዜውንም ሲያኬዱት ተመልከተናል። ከውስጣቸው ይሁን አይሁን አይታወቅም ብቻ ደስ ብሏቸው ሲወዛወዙ አይቻለሁኝ። በዚህ ዓመት በነበረው የትግራይ ህዝባዊ ኮንፈረንስም ላይ እንዲሁ ልባቸው ጥፍት እሲክል ድርስ ሲጨፍሩ አይቻለሁኝ። ይህ መቼም ሰውኛ ነው። እንደ ሰውኛ ጭፈራው ደግሞ ሌሎችን የሸር ገመዶችን እና የሴራ ድሮችን ተወት ቢያደርጉት መልካም ...