ልጥፎች

የገማው ጭንቅላት እገዳ፤ መጨረሻውን ያሳምረው። አሜን!

ምስል
ወንዳታ ብአዴን። „አግዚአብሄርን ደጅ ጥና፣ መንገዱንም ጠብቅ፤ ምድርም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ሃጢያተኞች ሲጠፉ ታዬለህ።“ መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፴፬ ከሥርጉተ©ሥላሴ 24.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·      ልበ ገብ ውሳኔ። አሁን ነው የሰማሁት። ለአንድ ወርም ቢሆን ሳጅን በረከት ስምዖን ከማዕከላዊ ኮሜቴ ታግደዋል። እንዴት ወንድ ወጣው ብአዴን? ጉድ በል ጎንደርስ አሁን ነው።  እርግጥ ነው እገዳው ለአንድ ወር ነው እስከ ቀጣዩ ጉባኤ ድርስ ቢሆንም ይህንም ድፍረት ማግኘቱ ብአዴን በሁለት እግሩ መቆሙን ያመላክታል። እስከ እሪሞከርኬው ድረስም ነው።  ይህን አዝልቆ ከዚህ የመከራ ምንጭ፤ የሸር ፏፏቴ፤ የተንኮል ድንኳን ብአዴን ከተገላላገለ፤ ለዘለቄታ አይደለም ብአዴን ኢትዮጵያን ልኡል እግዚአብሄር ይወዳታል ማለት ነው። አንዱ ትልቁ የገማው ጭንቅላት ነበሩ አቶ በረከት ስምዖን። እስኪ መጨረሻውን ያሳምረው። እራሱ መደፈሩ፤ እራሱ መጀመሩ እራሱ መታሰቡ በራሱ የድል መንበር ነው። ስንት የአማራ ነፍስ በዚህ ሰው ሴራ ድራሹ ጠፍቷል። ስንት ቡቃያ መክኗል። ስንት መከራ አማራ ተሸክሞ ኗሯል። የኢትዮጵያ ፖለቲካስ ቢሆን በዚህ ሸረኛ ሰው ሀርድ ዌር፤ ሶፍት ዌር ስንት ፍዳውን ከፍሏል። እግዚአብሄር በቃችሁ የሚለው ይሄ ውሳኔ እውን ዘድቆ መሬት ሲረግጥ ነው።  ይህ ገና ውጥን ነው። ብአዴን መኖር ከፈለገ በውነትም ይህን የመከራ ጉጉት ማስወገድ ነው ለዘለቄታው። ኢትዮጵያም ኢትዮጵያዊነትም ቀን የሚወጣለት ይህ የሴራ ካንፓኒ ውልቅልቁ ወጥቶ ሥራ ፈት ሲሆን ብቻ ነው። ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር። የኔዎቹ ዝርዝር ዜናውን እዚኸው ታገኙታላችሁ ሌላም ሴ

የልብህን ማድረስ የምትችለው በራስህ ጥረት ውስጥ ነው።

ምስል
ሚዛን። „በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢያተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ አልሁ።“ መዝሙር ምዕራፍ ፴፰ ቁጥር ፩ ከሥርጉተ©ሥላሴ 24.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ። ·      ተ ያያዥ። ፈጽሞ ለውጥ የለም የሚሉ ወገኖች አሉ። ይህም መብት ነውና አከብራለሁኝ። ለውጥ ማለት ለእኔ ሰኔ 29 ወደ ሰኔ 30 ሲቀዬር ለውጥ ነው። መናገር በተዘጋበት ምድር መናገር ሲጀመር ለውጥ ነው። በዓዋጅ የታሠረን ብሔራዊ ሰንደቅዓላማ ሁለመናህ አድርገህ ካለ አጋጅ፤ ካለ ከልካይ ይዘህ ስትወጣ ለውጥ ነው።  እንደ ጠላት ይታዩ የነበሩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች ተፎካካሪ ይባሉ ተቀናቃኝ ኢትዮጵያ የእናንተም ናት እና የድርሻችሁን አበርክቱ ተብለው መጠዬቃቸው ይህ መጀመሩ በራሱ ለውጥ ነው። ለእነሱም አዲስ የተመክሮ ማሳ ነው፤ አዲስ የአስተዳደር እና የአማራር በር መከፈቻ ነው፤ አዲስ የአገልግሎት መስመር መከፈቱን ያበስራል። ህዝብ ከጠ/ ሚሩ ጋር ፊት ለፊት ጥያቄዎችን አቅርቦ ሲሞግት ማዬት ትልቅ ለውጥ ነው። ከጠረፍ እስከ ጠረፍ ያሉ ወገኖቼ ጋር የተደረገው ውይይት እኔ ኢትዮጵያ የገባሁ እስኪመስለኝ ድረስ በጥሞና ተከታትዬዋለሁ ብቻ ሳይሆን የትኛው ጥያቄ የትኛው ክልል ላይ ስለመሆኑ ሁሉ ልክ እንደ አንድ የትምህርት ክ/ ጊዜ አጥንቼዋለሁኝ። አልፎ አልፎም በእንባ ነበር የተከታተልኩት፤ ይሄም  ለውጥ ነው እንደ አንድ የህዝብ አደረጃነቴ ቁምነገሬ ነው። ህዝብና መንግስት በቀጥታ የተገናኘበት አንድ ሃዲድ ነው ለእኔ። ከውጭ አገር የፖለቲካ አሳታፊነት ይልቅ በተሸላ ሁኔታ በተቻለ መጠን ሴቶችን ቦታ ለማስያዝ የሚደረገው ጥረትም ከወንዶች የፖለቲካ ዓለም ለኖርንበት የድቅ

የፖለቲካ ሥልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው፤

ምስል
የመፍትሄ መቋሚያ። „የሥራው ሁሉና የነገር ግዳጅ መጀመሪያ ምክር ነው።“ መፅሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴፯ ቁጥር ፲፮ ከሥርጉተ©ሥላሴ 23.08.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ የፖለቲካ ሥልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው፤፡ የፖለቲካ ስልጣን ትርምስ በቃኝ ማለት ብልህነት ነው።  ራስንም የማሸነፍ ልዩ አቅም ነው። ስለሆነም  አመሰግነዎታለሁኝ።  ·      መነሻ። https://www.zehabesha.com/amharic/archives/93721 ‘ ለኢትዮጵያ ሕልውና አስጊ የሆኑ ድርጅቶች በመደመር ስም ያለ ቅድመ ሁኔታ መግባታቸው ያሰጋል ’ – ሻለቃ ዳዊት ወ / ጊዮርጊስ ·          ወግ! ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንዴት ናችሁ? ትናንት ማምሻ ላይ ይህን ቃለ ምልልስ አዳመጥኩተኝ። እርግጥ ነው ብዙም ደህና ስላልነበርኩኝ ምን እንደሚሰማኝ አልጻፍኩኝም። አሁን ትንሽ ልለት ፈለግኩኝ።  የለውጥ ተጋድሎ ሲጀመር VOA የአማርኛው ክፈለ ጊዜ ከሁለት የፖለቲካ ሊሂቃን ጋር ያደረገው ውይይት ነበር። ሦስት ተከታታይ ውይይት ነበረው። ተወያዮቹ ፕ/ ዳንኤል አበራ እና አቶ ያሬድ ጥበቡ ነበሩ። በውይይቱ ላይ ያልተመቹኝ ነገሮች ስለነበሩ „መቋሚያ“ በሚል እርስ ሃሳቤን ገልጬ ነበር። ከገለጽኩባቸው ነጥቦች አንዱ አቶ ያሬድ ጥበቡ በኢትዮጵያ ግጭት አያሰጋኝም ስላሉ ነበር። እኔ ደግሞ ዕድለኛ ነዎት እንቅልፍ ተኝተው ማደር ችለዋል፤ እኔ ግን እጅግ ያሰጋኛል ብዬ ሞግቻቸው ነበር። ያልኩትም አልቀረም እስከ 2 ሚሊዮን ወገኖቻችችን መፈናቀላቸው ብቻ ሳይሆን ከመፈናቅል ጋር ተያያዥ የሆኑ እጅግ አሰቃቂ የወገን ሰቆቃ ደርሷል። እንግዲህ ያን ጊዜ ነው። አሁን ደግሞ ባለው „የመደመር ፖለቲካ“